AG GkfbHm

06/03/2022
28/11/2021

Peace

28/10/2021

እግዚአብሔር ዓሣን ሲፈጥር "ሕይወት ያላቸውን አስገኝ" ብሎ ባሕርን ተናገረው

እግዚአብሔር ዛፎችን ሲፈጥር ደግሞ ዛፍ እንድታበቅል መሬትን ተናገራት

ሰውን ሲፈጥር ግን የተናገረው ለራሱ ነበር

እግዚአብሔርም አለ "ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር"

ልብ አድርጉ :-

ዓሣ ከባሕር ከወጣ ወዲያውኑ ይሞታል
ዛፍም ከምድር ላይ ከተነቀለም ይሞታል

ሰውም ከእግዚአብሔር ከተለየ ይሞታል:: ባሕር ለዓሣ መሬት ለዛፍ ተፈጥሮአዊ መጠለያቸው እንደሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ መጠጊያችንም እግዚአብሔር ነው:: የተፈጠርነው ከእርሱ ጋር ልንኖር ነው:: ሕይወት ያለን ከእርሱ ጋር ነውና መኖር የምንችለው በእርሱ ብቻ ነው::

ይህንንም እናስታውስ

ዓሣ ያለ ባሕር ምንም ነው:: ባሕር ግን ያለ ዓሣ ያው ባሕር ነው:: ዛፍ ያለ መሬት ምንም ነው መሬት ግን ያለ ዛፍ ያው መሬት ነው:: ሰው ያለ እግዚአብሔር ምንም ነው:: እግዚአብሔር ግን ያለ ሰው ያው እግዚአብሔር ነው::

ቅዱስ ባስልዮስ እንዲህ እንዳለ :-

"ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ኅዳር 23 2013 ዓ ም
Translated from Mighty arrows publications

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ! በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :-

የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
የቴሌግራም ቻናል : https://t.me/deaconhenokhaile
የዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g

04/08/2021

የድንግል ማርያምን ሞትና ትንሣኤ የምናስብባት ጾመ ፍልሰታ ልትገባ ነው:: "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ብላ የእኛን ድኅነት ያስጀመረች ድንግል የምትሞትበት ጊዜ ሲደርስም "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ብላ የሞትን ጽዋዕ የተቀበለችበት : ሰው እንደመሆንዋ ጥቂት የሞት ፍርሃት በከበባት ጊዜ እነ ቅዱስ ገብርኤል እንደ ልማዳቸው "ማርያም ሆይ አትፍሪ" ያሉበት በልጅነቱ አቅፋ ደግፋ ያስተኛችው ልጅዋ እናቱን በሞት እንቅልፍ ሊያስተኛ የወረደበትን ታላቅ ክስተት የምናስብባት ጾመ ፍልሰታ ከፊታችን ቀርባለች::

ዘንድሮስ ከእመቤታችን ትንሣኤ ጋር የሀገራችንንም ትንሣኤ ለማየት እንማጸናለን:: እመቤታችን ሆይ ዘንድሮ ብቻሽን አትነሺ:: በስምሽ የምትምል ሀገራችንን ይዘሽ ተነሺ:: በጦርነት እሳት እየተለበለበ በልጅሽ ማመኑን ያላቆመ ሕዝብሽን ይዘሽ ተነሺ:: ለእርዳታ የሚሠጣቸውን ብስኩት "የጾም ነው ወይስ የፍስክ" ብለው የሚጠይቁ ባለ ማዕተብ ልጆችሽን ይዘሽ ተነሺ::

አበው ስለ ዕረፍትዋ እንዲህ ብለዋል :-

‹ሌሎች በድንግልና የኖሩ ሴቶች 'ለሞት የሚሆኑ ልጆችን አንሰጥህም" በማለት ሞትን ተቃወሙት፡፡ ድንግል ማርያም ግን አንድ ልጅ በመውለድ በልጅዋ ሞት ራሱ እንዲሞት አደረገችው፡፡ ከዐለት ጋር እንደተጋጨ የተፈረካከሰው በማሕፀንዋ ፍሬ ነውና ሞት ወደ እርስዋ ሲቀርብ ተብረከረከ›› ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

‹‹ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ ደስ አላቸው … በዚህች ቀን ታላቁ ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው … በዚህች ቀን ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ሥፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው … በዚህች ቀን ብርሃን ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ ከመቃብራቸው ራሳቸውን ቀና አደረጉ … አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ ፣ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች፡፡ ሙታንም ሕያዋንም ትርጉሙን ሊገልጹት በማይችሉት [የተለያየ] ዜማ ሰውና መላእክት በዚያች ዕለት አብረው ጮኹ›› ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ (Homily on the Dormition)

"ከወለደችም በኁዋላ ድንግልናዋን ላልፈረሰ ለእርስዋ ከሞተች በኁዋላም ሥጋዋ ሊፈርስ አይገባውም:: ፈጣሪን በደረትዋ ያሳረፈች እርስዋ በመለኮታዊ ድንኳን ውስጥ ማረፍ ይገባታል::

የአምላክ እናት ሆይ ጌታን በመውለድሽ ምክንያት ድንግልናሽን እንዳልተውሽ በመሞትሽም ይህንን ዓለም አልተውሽውም:: የሕይወት እናት ነሽና ዛሬ ወደ ሕይወት ተሻገርሽ:: በአማላጅነትሽም ነፍሳችንን በኃጢአት ከመሞት ታደጊ" " ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ

"በእርሱ ምክንያት ሰማይ ተብላ የተጠራችበት የሚመስለው የሌለ የማሕፀንዋ ፍሬ ለመሞትና ለመቀበር ፈቃደኛ ከሆነ ያለ ዘር የወለደችው እናቱ እንዴት ሞትን ትፈራለች?" ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ
(The life of Virgin Mary)

‹‹የቃሉ አገልጋዮችና ምስክሮች የነበሩት ሐዋርያት በሥጋ የወለደችውን የእናቱን ዕረፍትና እርስዋን የሚመለከቱ የመጨረሻዎቹን ምሥጢራትም ማየት ነበረባቸው፡፡ ይህም የሆነው የክርስቶስ የዕርገቱ የዓይን ምስክሮች እንደሆኑ ሁሉ የወለደችውም እናቱ ወደዚያኛው ዓለም ለሸጋገርዋ ምስክሮች መሆን ስላለባቸው ነው›› ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ (aka Doctor of Dormition)

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
በፍልሰታ ዋዜማ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ! በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :-

የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
የቴሌግራም ቻናል : https://t.me/deaconhenokhaile
የዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g

02/08/2021

+ ኢየሱስ ሆይ ከሀገራችን ሒድልን +

ሰዎች ኢየሱስን በብዙ ምክንያት ለምነውታል:: "ማረኝ" "ዓይኔን አብራልኝ" "ልጄን ፈውስልኝ" "ሙት አስነሣልኝ" ብለው የጮኹ ብዙዎች ናቸው:: የጌርጌሴኖን ሰዎች ግን ጌታን በአንድ ላይ ተሰብስበው "ከሀገራቸው እንዲሔድላቸው ለመኑት" ማቴ. 8:34

"ኢየሱስ ሆይ ውጣልን ! : ኢየሱስ ሆይ ሒድልን : ኢየሱስ ሆይ አትድረስብን : ኢየሱስ ሆይ አትምጣብን ! " የሚል ድምፅ እያሰሙ ተረባረቡበት::

ውጣልን ያሰኛቸው ሁለት ጋኔን የያዛቸውን ሰዎች ከላያቸው አጋንንቱን አውጥቶ ወደ አሳማ መንጋ እንዲገቡ በፈቀደ ጊዜ አጋንንቱ አሳማዎቹን ወደ ገደል እንዲገቡ ስላደረጉ ነበር::

ጌታችን አጋንንቱ ወደ አሳማ መንጋ እንዲገቡና ገደልም እንዲሰዱአቸው በመተዉ ትልቅ መልእክትን ለሰው ልጅ አስተላልፎ ነበር::

አጋንንቱ ወደ አሳማው ከመሔዳቸው በፊት ሁለት ሰዎች ላይ ነበሩ:: እነዚያን ሰዎች ላይ ቢቆዩም ግን ሰዎቹን ወደ ገደል አልከተቱአቸውም:: ልክ አሳማዎቹ ላይ እንደሰፈሩ ግን ወደ ገደል ጨመሩአቸው:: ክርስቶስ በዚህ ያስረዳን "እኔ በቸርነቴ ባልከለክለው ሰይጣን በእያንዳንዳችሁ ላይ ያለው ዕቅድ በቅጽበት ወደ ገደል እስከ መጨመር የጨከነ ነው" የሚል ነው:: ሰዎቹን ገደል እንዳይሰድ የከለከለው እሱ ነበር:: ዛሬም እኛን ከአፋፉ ላይ ሆነን ወደ ገደል ያልወረድነው "ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው" በተጨማሪም ሰይጣንም እንኳን በሰው ልጅ ላይ ቀርቶ በአሳማ ላይ እንኳን እንደፈለገ የመስፈር ሥልጣን እንደሌለውም በዚህ ታሪክ ተረዳን::

የጌርጌሴኖን ሰዎች ግማሾቹ ጌታችንን ስለኃይሉ በትሕትና ፈርተውት ግማሾቹ ደግሞ በአሳማዎቹ መሞት ተበሳጭተው ክርስቶስን ውጣልን አሉት:: ክርስቶስ የሰው ልጅ ከሚሰቃይ ጊዜያዊው ንብረት ቢጠፋ ይሻላል ብሎ ቅድሚያ ሲሠጥ ሰዎቹ ደግሞ ንብረታችን ከሚወድም ሁለቱ ሰዎች ጋኔን ቢጫወትባቸው እንመርጣለን ብለው ውጣልን አሉት::

አሣማ ቆሻሻ እንስሳ ነው:: በግእዝ ሕሱም ሐሳማ ማለት አስቀያሚ ማለት ነው:: ቆሻሻ ወዳዱ ሰይጣን ወደ ማደሪያው ገብቶ ሕዝቡንም በጌታ ላይ አሳመፀ:: ሕዝቡም ኢየሱስ ሆይ ሒድልን አሉት::
ጌታ ሆይ ከእኛ ጋር እደር ጌታ ሆይ ቶሎ ና ተብሎ ለሚዘመርለት ጌታ ሒድልንን አዜሙለት::

አፍ አውጥተን አንበለው እንጂ እኛም ጌታችንን ብዙ ጊዜ "ሒድልን" ብለነው እናውቃለን::

ወዳጄ አንተስ “ክርስትና በአፍንጫዬ ይውጣ" ብለህ አታውቅም? ያም ባይሆን መንፈሳዊ ነገር ማሰብ ወይም መዝሙር መስማት የማትፈልግበት ቀን ወይም ቃሉን ማዳመጥ የምትሸሽበት ቀን የለም? ዛሬስ ይቅርብኝ ብለህ ከልብህ ሀገር ኢየሱስን እንዲሔድልህ የለመንክበት ቀን : በቂም በቀል ልብህ ቆስሎ አኩርፈህ የይቅር ባዩን ጌታ ስሙን መስማት የጠላህበት ዕለት የለም?

ነጋዴው ከንግዱ ላይ ኢየሱስ ዘወር ቢልለት አይጠላም:: ኢየሱስ ከመጣ ገደል የሚጨምራቸው ብዙ ቆሻሻ ሥራዎች ያሉበት ሰው ጌታን ከሥራው ቦታ ዞር በልልኝ ይለዋል:: ሌብነት ማሟረት ጥንቆላ ዝሙት ሙስና የሚባሉ አሳማዎችን ገደል እንዳይገቡ ለመንከባከብ ስንል የናዝሬቱን መድኃኒት ዘወር በልልን ብለን የተማጸንን ብዙዎች ነን::

እንደፈለግን ለመኖር ከቆሸሸ አሳማ ጋር ለመዋል መርጠን በሀገራችን ላይ አጋንንት ሲጨፍሩ ሳያስከፋን የጌታችንን መምጣት ግን ያልፈለግን ብዙዎች ነን:: ከእኛ መካከል እንደ አሳማ የከፋ ልማዱ እና ሱሱ ወደ ጥልቅ እንዳይወረወርበት ፈርቶ የሚሸሽ ስንት አለ? የጌታችንን ቃል ለመስማት የማንፈልግ መንፈሳዊ ነገር ስንሰማ ጆሮአችንን የምንደፍን "ሒድልን እባክህ" ብለን የምንለምን ስንቶች ነን::

ጌታ ሆይ ክፋትን መርጠን ከሀገራችን ሒድልን ከቀዬያችን ውጣልን ስላልንህ አትቀየመን:: በሽተኛ ሲነጫነጭ ክፉ የሚያናግረው በሽታው ነው እንደሚባለው ክፉ የሚያናግረን ኃጢአታችን ነውና አትቀየመን:: የኃጢአት ፍቅር እንደ አሣማ ፍቅር ከባድ ነው:: ሽታው ቢከረፋም እኛ ግን ለምደነዋልና በቀላሉ መላቀቅ አቅቶናል::

አንተ ግን ሒድልን ብንልህም አትስማን:: አሳማ ኃጢአታችንን ከሚፈትኑን አጋንንት ጋር ወደ ጥልቁ ጣልልን:: ያን ጊዜ ነቢዩ የተናገረው ቃል ይፈጸማል:-

"ተመልሶ ይምረናል፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል፥ ኃጢአታችንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል"
ሚክ 7:19
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት 20 2013 ዓ ም

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ! በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

23/07/2021
23/07/2021

ዕርቃንህን እንደመጣህ ዕርቃንህን ትሔዳለህ::
ደካማ ሆነህ እንደመጣህ
ደካማ ሆነህ ትሔዳለህ::
ያለ ገንዘብና ያለ ንብረት መጥሃል ያለ ገንዘብና ያለ ንብረት ትሔዳለህ::
ለመጀመሪያ ጊዜ ሰውነትህን ያጠበህ ሌላ ሰው ነበር
ለመጨረሻ ጊዜም ሌላ ሰው ያጥብሃል::
ሕይወት እንዲህ ናት:: ስለዚህ ብዙ ክፋት ማብዛት ምን ይጠቅማል? የበዛ ቅናት : የበዛ ግፍ : የበዛ ራስን መወደድና የበዛ ትዕቢት ምን ይጠቅማል? ባዶ እጃችንን ለምንሔደው ለምን እንዲህ እንሆናለን?
በምድር ያለን ጊዜ በጣም ጥቂት ነውና በማይጠቅም ነገር አናባክነው::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
Translated from :- icopticorthodox

23/07/2021

Address

Aghatha Street
Giyani

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AG posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share