Nuredin Asemo

Nuredin Asemo Watr

ሳውዲ አረቢያ የነዳጅ ምርቷን መቀነስ ጀመረች።ለዚህ ዋነኛው ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለነዳጅ ዝውውር እጅግ ወሳኝ የሆነው የሆርሙዝ ሰርጥ በጦርነት ምክንያት ለመርከብ ጉዞ አስቸጋሪና ፈታ...
09/03/2026

ሳውዲ አረቢያ የነዳጅ ምርቷን መቀነስ ጀመረች።

ለዚህ ዋነኛው ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለነዳጅ ዝውውር እጅግ ወሳኝ የሆነው የሆርሙዝ ሰርጥ በጦርነት ምክንያት ለመርከብ ጉዞ አስቸጋሪና ፈታኝ በመሆኑ ነው።

መካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ጦርነት የሆርሙዝ ሰርጥ ለንግድ መርከቦች ፈታኝ እንዲሆን አድርጎታል።

ሳውዲ አረቢያ በቀን ከ7 ሚሊዮን በርሜል በላይ ነዳጅ ለዓለም ገበያ የምትልከው በዚህ መስመር ቢሆንም አሁን ግን መርከቦች ማለፍ ባለመቻላቸው ነዳጁ ሳይላክ ተከማችቷል።

የተመረተ ነዳጅ ሚቀመጥባቸው ታንከሮች በፍጥነት እየሞሉ በመሆናቸው ምክንያት አዲስ የሚመረት ነዳጅ የሚቀመጥበት ቦታ ስለጠፋ ምርቱን ለመቀነስ ተገዳለች።

° ኩዌት፣
° የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣
° ኢራቅም በተመሳሳይ ምክንያት ምርታቸውን ቀንሰዋል።

ሳውዲ በሆርሙዝ ሰርጥ ምትክ ነዳጇን በየብስ በኩል ወደ ቀይ ባሕር / ያንቡ ወደብ በመውሰድ ለመላክ እየሞከረች ነው ተብሏል።

ነገር ግን በዚህ በኩል ያለው የማስተላለፊያ መስመር በሰርጡ በኩል የሚላከውን ያህል ከፍተኛ መጠን የመሸከም አቅም የለውም። በዚህም ምክንያት አሁንም ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ ለገበያ መቅረብ አልቻለም።

ይህ ክስተት በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ መናወጥ እያስከተለ ነው።

የነዳጅ ዋጋ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ ዘሏል።

የG7 አገራት የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት የራሳቸውን የአደጋ ጊዜ ክምችት ወደ ገበያ ለማውጣት እየመከሩ ነው።

የሆርሙዝ ሰርጥ በዓለም ላይ ካለው የነዳጅ ዝውውር 20% የሚስተናገድበት ወሳኝ መስመር በመሆኑ መዘጋቱ ለረጅም ጊዜ ከቀጠለ የዓለም አቀፍ የነዳጅ እጥረት ሊባባስ ይችላል።

መረጃው የብሉምበርግ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ/ም

እውነተኛ የማን.ዩናይትድ ደጋፊ ይህን ፎቶ ዝም ብሎት አያልፍም!
25/01/2026

እውነተኛ የማን.ዩናይትድ ደጋፊ ይህን ፎቶ ዝም ብሎት አያልፍም!

21/01/2026

ለውድ የሀገሬ ልጆችና ለታላቅ የደግነት ልብ ባለቤቶች፣
ትናንት በእኛ ሚዲያ በተለቀቀው የቪዲዮ መልዕክት መሠረት ስትጸልዩልኝ ለነበራችሁ ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ።

አሁንም ባለሁበት ሆስፒታል ህክምናዬን እያደረግሁ መሆኔን ልገልጽ እወዳለሁ። ትናንት የነበረኝ የመጀመሪያው ዙር ሰርጀሪ በሰላም ተጠናቅቆ ወጥቻለሁ።

ህክምናዬ አሁንም ይቀጥላል፤ እንደወትሮው ሁሉ ጸሎታችሁ እንዳይለየኝ አሁንም አደራ እላለሁ። ስለ ድጋፋችሁ እና ወረት ለሌለበት ፍቅራችሁ ከልብ አመሰግናለሁ።

ደሰ ቡሎን ነል
21/01/2026

ደሰ ቡሎን ነል

የምስራች፦ ወገናችን ደንነት በላቸው ከነበረችበት አስቸጋሪ ሁኔታ በሰላም ወጥታለች!

* ቆይ ይሄ ፔጅ ና ተከታታዬችን እንዲሁም ድምፅ የሚሆኑትን የፊስቡክ አካውንቶች ግን አታመስግኑም ?

በሳውዲ አረቢያ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ለደንነት በላቸው ጉዳይ ስትጨነቁ ለነበራችሁ ወገኖች በሙሉ የተሰማ ደስ የሚል ዜና!

ሰሞኑን ወይዘሮ ደንነት በላቸው የተባሉ ዜጋችን በሳውዲ አረቢያ በከፍተኛ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የሚገልጽ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ መሰራጨቱ ይታወሳል።

ይህ መረጃ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ በደረሰው መሰረት፣ ኤምባሲው ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ ባደረገው ከፍተኛ ጥረት ወገናችንን ከነበረችበት አስቸጋሪ ሁኔታ መታደግ ተችሏል።

ኤምባሲው በሥራ ኮንትራት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ገብተው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ ዜጎች ሁሉ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፏል፦

ችግር ሲያጋጥማችሁ እና ለኤምባሲው መረጃ ስታመለክቱ፣ እርዳታው በፍጥነት እንዲደርሳችሁ እነዚህን መረጃዎች ማያያዝ እንዳትረሱ፦

* የወቅቱ ስልክ ቁጥራችሁ
* የፓስፖርት ቁጥራችሁ
* ያሰቀጠራችሁ ኤጀንሲ ስም እና ስልክ ቁጥር

Via Ethiopia Embassy in Rayadh /የኢትዮጵያ ኢምባሲ-ሪያድ

ወገናችን ደንነት በሰላም ስለተረፈች ለደከማችሁ እና ድምፅ ለሆናችሁ ሁሉ ምስጋና ይገባችኋል!

ኤምባሲያችንም ለሰጠው ፈጣን ምላሽ ምስጋናችን የላቀ ነው።

ሼር ያደረጋችሁ የተጨነቃችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ልትመሰግኑ ይገባል::

እናመሰግናለን::

ጉርሻ page

🌴🌴🌴

21/01/2026

ኡስታዝ ያሲን ኑሩ :- አልሃምዱሊላህ! "በጣም በጥሩ ጤንነት ላይ እገኛለሁ"

ባለፉት ቀናት የኡስታዝ ያሲን ኑሩን የጤና ሁኔታ አስመልክቶ ስትጨነቁና ዱዓ ስታደርጉ ለነበራችሁ ተከታዮች በሙሉ አጥጋቢና የሚያስደስት መረጃ ደርሶናል።

ኡስታዝ ያሲን ኑሩ ባስተላለፉት አጭር መልዕክት "በጣም በጥሩ ጤንነት ላይ እገኛለሁ። አልሃምዱሊላህ!" በማለት መላው የኡማውን ስጋት አስወግደዋል።

ኡስታዙ ለገጠማቸው መጠነኛ የጤና ህመም በዱዓ ከአጠገባቸው ለነበራችሁ ወዳጆቻቸው ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ በደህና ሁኔታ ላይ መሆናቸውንና ወደ መደበኛ ስራቸው እንደሚመለሱም ታውቋል።

ምስጋና ለአለማቱ ጌታ ለአላህ ይሁን ሲሉም ምስጋና አቅርበዋል::

አላህ ኡስታዛችንን ይጠብቅልን፤ እድሜና ጤና ሰጥቶ ለኡማው የሚሰጡትን ብርሃን ያብዛላቸው።

🙏🙏🙏

ጉርሻ page

🌴🌴🌴

ምርጥ ልጅ ነው
21/01/2026

ምርጥ ልጅ ነው

"ዳሎል ኢንተርቴይመንት" የተሰኘው የዩቲዩብ ቻናል ባለቤት ኑቲ ዳሎል፣ ከአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ህልፈት ጋር በተያያዘ የሰራው የ11 ደቂቃ ቪዲዮ 93 ሺህ ብር (ወደ $700 ዶላር) እንደሰራለት መግለጹ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል። ኑቲ ይህንን ገንዘብ በነፃነት ስም ለበጎ አድራጎት እንደሚያውለው ቢገልጽም፣ የቪዲዮው በቲክቶክ ከ2 ሚሊዮን በላይ እይታ ማግኘት ግን የኢትዮ ሊድን ትኩረት ስቧል። ኑቲ በሀገራችን የዩቲዩብ አጠቃቀምንና ገንዘብ አሰራርን ከሚያስተምሩ ሰዎች አንዱ በመሆኑ፣ ይህ አሃዝ ለትምህርት ኮርሶቹ መሸጫነት የዋለ የ"ማርኬቲንግ" ዘዴ ይሆን? የሚል ጥርጣሬ ፈጥሯል።
​በእርግጥ ከአንድ ቪዲዮ $700 ዶላር መስራት ይቻላል፤ ነገር ግን አብዛኛው ተመልካች ከኢትዮጵያ በሆነበትና የዩቲዩብ ማስታወቂያዎች በሀገር ውስጥ በማይሰሩበት ሁኔታ፣ ከ300 ሺህ በታች እይታ ባለው ቪዲዮ ይህን ያህል ገንዘብ ተገኘ ማለት ከቴክኒካዊ እውነታው ጋር ይጋጫል። ኑቲ ሰዎችን በማጓጓት ኮርሶችን ለመሸጥ ካልሆነ በቀር፣ በመደበኛ የRPM ስሌት ይህ አሃዝ እንዴት ሊመጣ እንደቻለ ግልጽ አይደለም። ስለዚህም ኢትዮ ሊድ ኑቲ ይህንን ገቢ በቪዲዮ የተደገፈ ማረጋገጫ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ በግልጽ ይጠይቃል።
​ቀደም ሲል አርቲስት ገነት የነፃነትን ህልፈት ለገቢ ማግኛ ተጠቅማባታለች በሚል እንደጠየቅነው ሁሉ፣ ኑቲም ይህን አጋጣሚ ኮርስ ለመሸጫነት ከተጠቀመበት ከትዝብትና ከተጠያቂነት አያመልጥም። እውነትም በበጎ አድራጎት ስም የታሰበ ከሆነ፣ ግልጽ ማረጋገጫው ለራሱ ለኑቲም ሆነ ለተከታታዮቹ ተዓማኒነት እጅግ አስፈላጊ ነው። ኢትዮ ሊድ የኑቲ ዳሎልን ምላሽ እየጠበቀ ይህን ጉዳይ በቅርበት መከታተሉን ይቀጥላል።
​ኢትዮ ሊድ Exclusive

ይገምቱ ይሸለሙ❗️ማሳሰቢያ❗️(ፎሎ 👉 ሼር 👉 ላይክ 👉 3 ጓደኛ ሜንሽን)🚩ኮመንት ኤዲት ማድረግ፣ በተለያየ አካውንት ወይም በተመሳሳይ መለያ ቁጥር ምላሽ መስጠት ከጨዋታ ውጪ ያደርጋል!🙌ተሸላ...
29/11/2025

ይገምቱ ይሸለሙ

❗️ማሳሰቢያ❗️(ፎሎ 👉 ሼር 👉 ላይክ 👉 3 ጓደኛ ሜንሽን)
🚩ኮመንት ኤዲት ማድረግ፣ በተለያየ አካውንት ወይም በተመሳሳይ መለያ ቁጥር ምላሽ መስጠት ከጨዋታ ውጪ ያደርጋል!

🙌ተሸላሚ ለመሆን፣

(ትክክለኛውን ስቴፕ ያሟሉ ተወዳዳሪዎች ብቻ ተሸላሚ ይሆናሉ!)
1, ወደ ፌስቡክ ገጻችን በመሄድ ገጹን ላይክ (ፎሎ) ማድረግ -

2, ኮመንት ላይ ከግምታችሁ ጋር የኤሌፋንት ቤት User ID'ችሁን ማስቀመጥ

3, አብራችሁ ሶስት ጓደኛችሁን ታግ ማድረግ እና ሼር ማድርግ አትርሱ!

💵ይሄን ጨዋታ ውጤት በትክክል የሚገምቱ 15 ተከታዮቻችን የ 3000 ብር ተሸላሚ ይሆናሉ።

👉🏾 ልብ ይበሉ ተሸላሚ ለመሆን ኮመንት ላይ ከግምታችሁ ጋር የኤሌፋንት ቤት User ID'ችሁን ማስቀመጥ አይርሱ!
በአንድ አካውንትም ሆነ በ አንድ User Id ከአንድ በላይ ግምት መስጠት ከጨዋታ ውጭ ያደርጋል!

ለመመዝገብ - 🌐 https://elephantbet.et

ለማንኛዉም እገዛ - Elephant Bet Ethiopia

📱 TikTok | Instagram | Facebook 📱

Eindrk waw ❤️❤️🌹🇪🇹
19/09/2024

Eindrk waw ❤️❤️🌹🇪🇹

06/08/2024
01/03/2024
01/03/2024

Address

Jijiga
Laftu

Telephone

+251953560337

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nuredin Asemo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share