EYOB BOOKS

Directions

EYOB BOOKS READING REALLY MATTERS!

በመደብራችን ይገኛሉ
24/10/2026

በመደብራችን ይገኛሉ

23/10/2026

ሀዋሳ ያላችሁ በሙሉ አይቀርም።

በመደብራችን በቅናሽ ይገኛሉ
23/10/2026

በመደብራችን በቅናሽ ይገኛሉ

የጋራ ድካማችን ፍሬ እያፈራ ነዉ። የት? እነማን አገዙን? እነማን ይኖራሉ? ምን ይካሄዳል በሚለው ጉዳይ እመለሳለሁ።እስከዛው አጋሩት።HAWASSA READS!!!!ሌላም የምስራች በቅርቡ አለን።
19/10/2026

የጋራ ድካማችን ፍሬ እያፈራ ነዉ። የት? እነማን አገዙን? እነማን ይኖራሉ? ምን ይካሄዳል በሚለው ጉዳይ እመለሳለሁ።
እስከዛው አጋሩት።
HAWASSA READS!!!!
ሌላም የምስራች በቅርቡ አለን።

በመደብራችን በማበረታቻ ቅናሽ ይገኛሉ ።
17/10/2026

በመደብራችን በማበረታቻ ቅናሽ ይገኛሉ ።

16/10/2026

Browse local shops and order online.

ንባብ እና እንቅልፍ(ላነብ መጽሐፍ ስይዝ እንቅልፌ ይመጣል ምን ተሻለኝ?)የሚያነቡ ሰዎች በበጎ ያስቀኑህና ንባብ ልትጀምር ለራስህ ትወስናለህ፡፡ ከዚያም በዕረፍትህ ቀን ሰዓት አመቻችተህ ልታነ...
15/10/2026

ንባብ እና እንቅልፍ

(ላነብ መጽሐፍ ስይዝ እንቅልፌ ይመጣል ምን ተሻለኝ?)

የሚያነቡ ሰዎች በበጎ ያስቀኑህና ንባብ ልትጀምር ለራስህ ትወስናለህ፡፡ ከዚያም በዕረፍትህ ቀን ሰዓት አመቻችተህ ልታነብ ገና ከመቀመጥህ ከየት እንደ መጣ የማታውቀው ኃይለኛ እንቅልፍ በዓይንህ ዙሪያ ያንዣብባል፡፡ አንዴ ከመጽሐፉ አንዴ ከገዛ እጅህ ጋር እያጋጨ መከራህን ያሳይሃል፡፡ በመጨረሻም ትግሉ ሲሰለችህ ልታነብ ያነሣኸውን መጽሐፍ ተንተርሰኸው ለጥ ትላለህ፡፡ ቆይ ንባብና እንቅልፍን የሚያያይዛቸው ነገር ይኖር ይሆን?

ከሥራ ብዛት ወይም በኑሮ መክበድ ምክንያት የአእምሮ ውጥረት (Stress) ላጋጠማቸው ሰዎች ውጥረቱን ለመቀነስ በሥነ ልቡና ባለሙያዎች ከሚመሰጣቸው ምክሮች ውስጥ አንዱ ‹መጻሕፍትን አንብቡ› የሚል ነው፡፡ በዚህ ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች መጻሕፍትን በሚያነቡበት ጊዜ ከቆዩበት ጭንቀት ለመውጣት መጽሐፍቱ እንደ በር ስለሚያገለግሏቸው ተወጣጥሮ የነበረው ኅሊናቸው ነጻ የመሆን እድል ያገኛል፡፡ ሰውነትህ ደግሞ ከውጥረት ነጻ መሆኑን ከሚገልጽባቸው ምልክቶቹ ውስጥ አንዱ እንቅልፍ ነው፡፡ ስለዚህ ንባብ አንዳንድ ጊዜ ለአእምሮ ውጥረት መድኃኒት በመሆን ከእንቅልፍ ጋር ሊተሳሰር ይችላል፡፡

ይሁን እንጂ ከውጥረት ለመውጣትም ቢሆን መጀመሪያ መጽሐፉ ሊነበብ ይገባል፡፡ ሳታነብ እንቅልፍ የሚወስድህ ከሆነ ግን ይህ ንባብ ያልለመደ ሰውነት ምልክት ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ነገሮች በዝግታ አጢን

➢ ለመጻሕፍት ንባብ ገና ጀማሪ ከሆንክ የመጽሐፍ ምርጫህን አስተካክል፡፡ የምታነበው መጽሐፍ ብዙ ቁም ነገር ቢኖረውም አቀራረቡና ሥነ ጽሐፋዊ ውበቱ ብዙም ካልሆነ፣ ውስጥህ ጭል ጭል የሚለውን ትንሽ የንባብ ብርሃን እስከ መጨረሻው አጥፍቶ ከመጻሕፍት እንዳይለይህ ቶሎ እርምጃ ውሰድ፡፡ በአቀራረባቸው የተመሰገኑ መጻሕፍትን እንዲጠቁሙህ የንባብ ልምድ ያላቸውን ሰዎች አማክር፡፡ እነርሱንም አስቀድም፡፡

➢ ለንባብ የሚሆን ደመቅ ያለ ብርሃን ያለበትና ምቹ ቦታ መምረጥ ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን የተጋነነ ምቾት ወደ እንቅልፍ ሊወስድህስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ጋደም ከማለት ይልቅ ቁጭ ብለህ ማንበብ የበለጠ ንቁ ያደርግሃል፡፡ ደግሞ መንፈሳዊ መጻሕፍትን እንደ ታመመ ሰው ተኝተህ ማንበብ አግባብ አይደለም፡፡ በል ቶሎ ተነሥ፡፡

➢ ሰይጣን የሚጸልዩ ሰዎችን የሚፈትነውን ያህል የሚያነቡ ሰዎችንም ይዋጋል፡፡ ለጸሎት በቆመ ሰው ዓይኖች ላይ የእንቅልፍ ሽፋሽፍትን እንደሚያመጣ፣ መንፈሳዊ መጻሕፍትን ለማንበብ በተዘጋጁ ዓይኖች ላይም እንቅልፍ እንዲከብድ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ እንዲህ ስትሆን ፈጥነህ ለጸሎት ተነሥ፡፡ የሚቃወምህን ክፉ መንፈስ ‹‹እክህደከ ሰይጣን›› በማለት ገስጸው፤ አውግዘው፡፡ አንብበህ ተለውጠህ ፈጣሪህን እንዳታስደስት የሚቃወምህን ረቂቅ ባላጋራ ‹ንባብህን ትተህ በመተኛት› ደስ አታሰኘው፡፡ መላልሰህ እየተጋህ ተስፋ አስቆርጠው፡፡

ዲያቆን አቤል ካሣሁን
[email protected]

https://t.me/Dnabel

አስደናቂው የኢትዮጵያ ጥንታዊነትና ታላቅነት“የቀደመ ታሪኩን የማያውቅ ትውልድ፤ ስር እንደ ሌለው ዛፍ ነው፡፡”። ማርክስ ጋርቤይከጊዜው ቆይታና በሌሎችም የተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ በርካታ የ...
15/10/2026

አስደናቂው የኢትዮጵያ ጥንታዊነትና ታላቅነት

“የቀደመ ታሪኩን የማያውቅ ትውልድ፤ ስር እንደ ሌለው ዛፍ ነው፡፡”። ማርክስ ጋርቤይ

ከጊዜው ቆይታና በሌሎችም የተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ በርካታ የኢትዮጵያ ጥንታዊ መረጃዎችን ባለማግኘታችንና የተገኙትንም ጥቂት ክብር ሰጥተን ባለመመርመራችን፤ ስለኢትዮጵያ ጥንታዊ እውነታዎች ብዙ ነገር ማወቅ አልቻልንም፡፡ ለአሁኑ ትውልድ እጅግ የሚያስደንቁ፤ በእውነት እንደዚያ ነበርን እንዴ? የሚያሰኙና ታሪካችንን እንደገና እንድንጽፈው የሚያስገድዱ፣ እውነተኛ የሆኑ፤ የተጻፉ መረጃዎች አሉ፡፡ ታዳ ታዲያ እስከ ዛሬ ድረስ ለምን አላወቅናቸውም? _ ለሚለው ጥያቄ፤ በብዙ በተለያዩ ምክንያቶች አልሰማናቸውም ወይም አላየናቸውም እንጂ፤ በቂና የሚያስደምሙ እውነተኛ ምላሾች እንዳሉት ማረጋገጫዎቹ በርካቶች ናቸው፡፡

አንብባችሁ የምታተርፉበት መጽሃፍ ነው ።

Available
15/10/2026

Available

አና ካርሰን ካናዳዊት ገጣሚ፣ ደራሲ፣ የጥንታዊ ግሪክ ሥነ ጽሑፍ ተመራማሪና ተርጓሚ ናት። ግጥምን፣ ፍልስፍናን፣ ድርሰትንና ድራማን በልዩ መንገድ በማቀላቀል ትታወቃለች። የአና ካርሰንን ሥራዎ...
12/10/2026

አና ካርሰን ካናዳዊት ገጣሚ፣ ደራሲ፣ የጥንታዊ ግሪክ ሥነ ጽሑፍ ተመራማሪና ተርጓሚ ናት። ግጥምን፣ ፍልስፍናን፣ ድርሰትንና ድራማን በልዩ መንገድ በማቀላቀል ትታወቃለች። የአና ካርሰንን ሥራዎች የሚለያቸው ነገር ብዙ ቃላትን መጠቀም ሳይሆን፣ ግጥምን፣ ፍልስፍናንና የሰውን ውስጣዊ ስሜት በአዲስ መንገድ ማገናኘቷ ነው። የ2026 የስነጽሁፍ ኖቤል ተሸላሚ ስትሆን በዘመኗ አንድም እውቅናና ሽልማት ተቀብላ የማታውቅ ሲሆን የሆሜር ስራዎች አድናቂና ከ500 B.C በፊት ያሉ መጽሀፍት ማንበብ የሚያስደስታት መሆኑን ገልፃለች።

Address

Hawassa
1138

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EYOB BOOKS posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category