NUUR Al HUDAA.

30/07/2026

🚨 ፍትህ ለባቡ ረያን መስጂድ! 🚨

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 (በአዲስ አበባ መጅሊስ ቅጥር ግቢ ውስጥ) የሚገኘው ባቡ ረያን መስጂድ፣ የአካባቢው ማህበረሰብና አህለል ኸይሮች ደምና ላባቸውን አፍስሰው፣ ንብረታቸውን ሰውተው የገነቡት የኢባዳ ማዕከል ነው!

መስጂዱ ተገንብቶ እስኪጠናቀቀ ድረስ የአካባቢው ማህበረሰብ አንድነቱን ጠብቆ፣ በሰላም አብሮ የኖረ ቢሆንም፤ ዛሬ ግን የመስጂዱ መስራቾችና የአካባቢው ህዝብ የማያውቋቸው ጥቂት ወገኖች በህገ-ወጥ መንገድ ስልጣን ተቆጣጥረው የመስጂዱንና የአካባቢውን ሰላም እያደፈረሱ ይገኛሉ።

እየተፈጸሙ ያሉ አደገኛ ድርጊቶች፦

- ለረጅም ዓመታት ሲያስተምሩ የነበሩትን ኢማም ትምህርት በግፍ ማገድ፤

- የአካባቢው ማህበረሰብ በጋራ የመሰረተውን የህፃናት መድረሳ በህገ-ወጥ መንገድ መዝጋት፤

- በማህበረሰቡ መካከል ክፍፍልና ሁከት በመፍጠር የሃይማኖት ንቀለ-ተከላ ለማካሄድ መሞከር፤

ይህ ህገ-ወጥና ፀረ-ማህበረሰብ ድርጊት በአስቸኳይ ሊገታ ይገባል!

መላው አህለል ሱና ወልጀመዐ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም የሚመለከታቸው የህግ አካላት ይኸንን እኩይ ድርጊት በህግ አሰራር መስመር ለማስያዝ እና የመስጂዱን ሰላም ለማስመለስ ድምፃችሁን እንድታሰሙና የድርሻችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!

30/07/2026

የፍቅርና የአፍቃሪዎች መገለጫዎች አያሌ ቢሆኑም ከቃላትም ሆነ ከቋንቋ ከፍ ባለ መልኩ ፍቅር በተግባር ይገለጻል ፍቅር ላፈቀሩት ነገር በመኖር ይገለጻል። አፋቃሪ የተፈቃሪውን ደስታ ለማየት ቀን ከሌት ይታትራል። የፍቅር ዋነኛ ማሳያ ምን ሊሆን ይችላል ቢባል መከተል ከሚለው የተሻለ አጥጋቢ ምላሽ አይገኝም። አንድ አማኝ እምነቱን በማጽናት ላይ ይቆም ዘንድ ታዟል።

አሏህና መልዕክተኛውን በመውደድም ላይ ዘውታሪ መሆን ግዴታው ነው። ለዚህም ሲባል አሏሁ ተዓላ በተከበረው ቅዱስ ቁርአን እንዲህ ሲል ነግሮናል ፦
﴿ قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعُونِي يُحْبِبْكُمُ اللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ﴾
[ آل عمران: 31]
በላቸው፡- «አሏህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አሏህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡ አሏህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡»

በርግጥም የልቅና ባለቤት የሆነው ጌታችን አሏህ እውነት ተናገረ ፤ ከመከተል በላይ ፍቅር የለም። አሏህን እወዳለሁ ጌታዬን እታዘዛለሁ ለሕግጋቶቹ ተገዥ ነኝ የሚል አማኝ በየትኛውም የሕይዎት ዑደቱ ከመልዕክተኛው ትዕዛዝ ዘንፈል አይልም። አርዓያነትም በመልዕክተኛው ሙሐመድ ﷺ ይብቃኝ ብሎ ለመጡበት መለኮታዊ ጥሪ እጅ ይሰጣል። ያዘዙትን በመፈጸም የከለከሉትን በመራቅ ላይ ይፀናል። መልዕክተኛውን መውደድ በርሳቸው መንገድ ላይ መፅናት አሏህ የሚወደው ተግባር አሏህንም ከመውደድ የሚቆጠር ተግባር ነው ይህንኑ ጉዳይ አሏህ እንዲህ ሲል ነግሮናል ፦
﴿ مَّن يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ ۖ وَمَن تَوَلَّىٰ فَمَا أَرْسَلْنَاكَ عَلَيْهِمْ حَفِيظًا﴾
[ النساء: 80]
"መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አሏህን ታዘዘ ፤ ከትዕዛዝም የሸሸ ሰው (አያሳስብህ) በነሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አላክንህምና" አል-ኒሳእ 80

ነብያችን ሙሐመድﷺ መውደድ ለእምነት መሙላት መስፈርትም ጭምር ነው። በአሏህ ያመኑ ሁሉ በሙሐመድ ﷺ መልዕክተኛነት የማመን ግዴታ አለባቸው ። ከዛም አልፎ ኢማኑ ሙሉ ይሆን ዘንድ መልዕክተኛውን ከራሱ ከቤተሰቡ ከንብረቱና ከሰው ልጆች ሁሉ አስበልጦ ሊወዳቸው እንደሚገባ ውዱ ነብያችን ﷺ በሐዲሳቸው እንዲህ ሲሉ ነግረውናል ፡-
روى البخاري ومسلم من حديث أنس بن مالك رضي الله عنه أن رسولَ الله ﷺ قال: " لا يُؤْمِنُ أحدُكم حتى أكونَ أحبَّ إليه من ولدِهِ ، ووالدِهِ ، والناسِ أجمعينَ "
"ከናንተ አንዳችሁ ኢማኑ ሙሉ አይሆንም ! እርሱ ዘንድ ከልጆቹ ከወላጆቹ ከሰው ልጆች ሁሉ በበለጠ እኔ ተወዳጅ እስካልሆንኩ ድረስ" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

አሏህ ነብያትን ለሰው ልጆች አብሳሪና አስጠንቃቂ አድርጎ ሲልክ በየትኛውም ሁኔታ ላይ የሰው ልጆች አይነታ አድርጎ ነውና የኛም ነብይ የመልካምነት ተምሳሌት የፍትህ ማሳያ የታላቅነት ቁንጮ መሆናቸው ወድጅ ሳይሆን ጠላይ የሚመሰክረው ሐቅ ነው የነብያችንን ሙሐመድ ﷺ መንገድ ማስቀጠል ለኢስላም ዋጋ መክፈል አሏህን መውደድ ነው ለጀነት ስንቅ መሰነቅ ነው። አሏህና መልዕክተኛውን መታዘዝ ዛሬ በዱኒያ ላይ መዳኛ ነገም በዕለተ ትንሳኤ ትልቅ ሽልማትን የሚያጎናጽፍ የነፃነት መንገድ ነው ጌታችን አሏህም እንዲህ ብሏል ፦

قال الله تعالى: {وَمَن يُطِعِ اللهَ وَالرَّسُولَ فَأُوْلَئِكَ مَعَ الَّذِينَ أَنْعَمَ اللهُ عَلَيْهِم مِّنَ النَّبِيِّينَ وَالصِّدِّيقِينَ وَالشُّهَدَاء وَالصَّالِحِينَ وَحَسُنَ أُولَئِكَ رَفِيقًا}

በየትኛውም የዘመን ቀመር ያለፉ ታሪኮችን ከታሪክ መዛግበት ስንመለከት ፤ ከታላላቆችም የሕይወት ፈለግ እንደምንማረው ከሶሃባዎች ገድል እስከ ታላላቅ ዑለማዎችና የዲን ወራሾች ፤ ከቋንቋ ሊቃምንት እስከ ታሪክ ተመራማሪዎች ፤ ከጠቢባን እስከ ታላላቅ ሙፈሲሮች አንዲሁም ከመዝሃብ ባለቤቶች ፋና ስንረዳው የስኬታቸው ሚስጥር በኢስላም ታሪካቸው ከፍ ብሎ የመወሳቱ ዋነኛ ምክንያት በዲናቸው ጸንተው አሏህና መልዕክተኛውን ﷺ አጥብቀው መውደዳቸው ነው። አፍቃሪ ላፈቀረው ፤ ወዳጅ ለወዳጁ የማይከፍለው ዋጋ አይኖርም ለምን ቢባል አፍቃሪያን የሚገጥማቸው መከራም ይሁን የችግር ዶፍ መጨረሻው በወደዱት ልክና በከፈሉት መስዋዕትነት መጠን ክፍያቸው ያማረ መሆኑን ማወቃቸው ነው።

ያለንባት ዱኒያ በበርካታ የልብን አቅጣጫ በሚሰልቡ የስሜትና አብለጭላጭ ነገራቶች የታጠረች ከመሆኗ ጋር በዲን ላይ መጽናት ስሜትን አሸንፎ ቀጥተኛውን ጎዳና መከተል እጂግ ፈተኛ ቢሆንም ዱኒያ ቅርብ ወራጅ ነችና እሷን አውቆ በርሷና በውስጧ ካሉ አያሌ ፈተናዎች መራቅ አማራጭ የሌለው መሆኑን ተገንዝበን ፍቅራችን ዛሬ ላይ ለነገ የምንሰንቅበት ይሆን ዘንድ አደራ እላችኋለሁ።

لَّقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ وَذَكَرَ اللَّهَ كَثِيرًا

"ለእናንተ አሏህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው ፤ አሏህንም በብዙ ለሚያወሳ በአሏህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ፡፡" አል-አሕዛብ 21

🍂
ሸይኽ ዑመር ኢማም /Sheikh Umar Imam

30/07/2026

Address

AbdulkaderMulat29@gmail. Com
Gondar

Telephone

+251984247073

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when NUUR Al HUDAA. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to NUUR Al HUDAA.:

Shortcuts

Share