Ethio Wolaita

Ethio Wolaita yellaaga

‎‎ምርጫው ሲመጣ እንደ እስስት የሚቀያየርና የራሱ ጎሳ በማደራጀት ወላይታን ለመከፋፈል እየጣረ ያለ ጎሰኛውና ጽንፈኛው ወ/ማሪያም ልሳኑ‎‎ጎሰኛውና ጽንፈኛውን ወ/ማሪያም ልሳኑ ተለዋዋጭ ባህሪ...
03/05/2026


‎ምርጫው ሲመጣ እንደ እስስት የሚቀያየርና የራሱ ጎሳ በማደራጀት ወላይታን ለመከፋፈል እየጣረ ያለ ጎሰኛውና ጽንፈኛው ወ/ማሪያም ልሳኑ

‎ጎሰኛውና ጽንፈኛውን ወ/ማሪያም ልሳኑ ተለዋዋጭ ባህሪ ያለዉና ለአላማ ፅኑ ያለሆነ ጥቅመኛ ሰው ነው። ለአብነትም ምርጫ 2002 ጊዜ ኢሕአዴግ፣ ምርጫ 2013 ጊዜ እናት ፓርቲና ምርጫ 2018 ዎሕነን ይዞ የመጣ የአቋምና አላማ ፅናት ችግር ያለበት ወላዋይ ሰው የምንለው በምክንያት ነው። ቀጣይ 2022 በለላ አድስ ፓርቲ ይዞ እንደሚመጣ ጥርጥር የለውም።

‎ግለሰቡ በዚህ በሰለጠነ ዘመን ዘዉዳዊ የሆነ የጎሳ ዳይናሲቲ ለማቋቋም በዳሞት ጋሌና መላዉ ወላይታ የሱ ጎሳ በስፋት ባለባቸዉ ቀጠና ጭምር ዞሮ በመቀስቀስ እና ማደረጃት እኔን ፓርላማ አስገቡኝ ብሎ እየለመነ ይገኛል።

‎በለላ በኩል ማላና ዶጎላ ሳይሆን "የእኛ ብቻ ነው መንግስት መሆን ያለብን" በሚል ሴራ ህቡእ ቡድን ሰብሳቢ፣ ም/ስብሳቢ እና ዳባዋ ሰይሟል። ይህ አደገኛ ስለሆነ መላው የወላይታ ህዝብ መታገል አለበት።

በ2010 ዓ.ም የአገርቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የደረሰብንን አደጋ ለማፅናናት በመጡ ጊዜ ከወላይታ ህዝብ ባህልና እሴት ወጣ ባለ መልኩ የተከበረዉን መሪ የሰደበ ሥነምግባር የጎደለውና ለሰውም ክብር የሌለው ሰው ነው።

ሌላው አደገኛው ጉዳይ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት(አባ መላኩ) ጀምሮ ጥንታዊት ወላይታ ኦርቶዶክስ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለማከፋፈል፣ ወላይታ ብቻዋን ሲኖዶስ ልኖር ይገባል፣ ከአዉደ ምህረት፣ ከማህሌትና ቅዳሴ የለሎች አከባቢ ሰዎች ማባረርና ሀብትን እኛ እንጠቀም በማለት የፅንፈኛ ቡድን መስርቶ እየተንቀሳቀሰ መገኘቱና ለዕጩና የቅስቀሳ ስራ እንኳን የአንድ ሀይማኖት አባላት ብቻ ያነጣጠረና የሀይማኖት እኩልነትን የማያምን ፓርቲ ያደራጀ መሆኑን ህዝቡ ማወቅ አለበት።

ሌላው ከጽንፈኛው ከህወሃት ጋራ በመሆን ተልዕኮውን በመቀበል ወላይታንና ሀገራችንን ለማተራመስ ገንዘብ ተመድቦ ለተ ቀን የሚሰራና የወደቀ የጁንታ አስተሳሰብ ተሸካሚ መሆኑና እንድሁም ምልክታቸዉም ጭምር የህወሓት ነዳፊ ንብ መሆኑንም ማሳያ ነው።

አንድ ሚልዩን መራጫ በወላይታ የለም የተባለው መላው የወላይታ ህዝብ በመሰማቱ በቁጭት በመውጣት ለመምረጥ መዘጋጀቱ ተሰማ_______ምርጫ ቦርዱ የወላይታ ህዝብ ቁጥር አንድ ሚሊዮን አይደርስም ...
29/05/2023

አንድ ሚልዩን መራጫ በወላይታ የለም የተባለው መላው የወላይታ ህዝብ በመሰማቱ በቁጭት በመውጣት ለመምረጥ መዘጋጀቱ ተሰማ
_______
ምርጫ ቦርዱ የወላይታ ህዝብ ቁጥር አንድ ሚሊዮን አይደርስም በቁጥር አናሳ ነው ያለው መላው የወላይታ ህዝብ ሰኔ 12/2015 ዓ.ም በነቂስ ወጥተው ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ታማኝ የመረጃ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

ሰኔ 12 ዳግም የሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ለወላይታ ህዝብ ብዙ ትርጉም ያለው በመሆኑ ህዝቡ የማንነት ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ በነቂስ ወጥተው ነጭ ርግብን ለመምረጥ ተዘጋጅቷል፡፡

የወላይታ ህዝብ በነቂስ ወጥተው ነጭ ርግብን በመምረጥ በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ታሪካዊ ኃላፊነትን ማውጣት ያስፈልጋል፡፡

አንዳንድ ጽንፈኞችና ጨለምተኞች ምርጫው ገና ሳይጠናቀቅ ማዕከል አንዴ ወላይታ አንዴ ደግሞ አርባምንጭ እያሉ ህዝቡን በውሸት መረጃ እያደናገሩ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ ህዝቡ መንግስት የህዝብ ፍላጎትን ያማከለ ትክክለኛውን መረጃ ይፋ እስከሚያደርግ ድረስ በትግስት መጠበቅ አለበት፡፡

የግል ፍላጓታቸውን ለማሳካት የሚሯሯጡ ግለሰቦች ከማዕከል ጋር ተያይዞ እየተሰራጨ ያለ መረጃ ያልተረጋገጠና ውሸት መሆኑም ታወቋል፡፡

22/01/2023
17/10/2021

የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አድማሱ አወቀ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1496ኛው የመውሊድ በዓል አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፦

የተከበረችሁ በሀገራችንና በዞናችን የምትገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1496ኛው የነቢዩ መሀመድ የልደት በዓል (መውሊድ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

በዓለም አቀፍ ደረጃ በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ዘንድ ትኩረት የሚሰጠው የነቢዩ መሀመድ የልደት በዓል (መውሊድ) ነው።

በመውሊድ በዓል መላው የሙስሊሙ ህዝብ በመደጋገፍ፣ በመጠያየቅ፣ በፍቅርና በትህትና እያከበራችሁ ሀገራችን የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ እውን እንዲሆን የበኩላችሁን ሚና በመጫወት አርአያነታችሁን እንድትወጡ በዚህ አጋጣሚ አደራ እላለሁ።

መላው የዞናችን ህዝቦች ለውጡ ያመጣውን ትሩፋቶችን ተጠቅማችሁ ከመሪዉ ፓርቲና መንግስት ጎን ቆማችሁ ለሠላማችን፣ ለአንድነታችን፣ ተግተን በመስራት ድህነትን አሽቀንጥረን በመጣል ሁለተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ሌት ቀን መትጋት ያሰፈልጋል።

ሀገራችንን ኢትዮጵያን ለማዳከምና ለማፈራረስ አልመው እየሰሩ ያሉ የውስጥና የውጭ ሀይሎችን ሴራ በማክሸፍ የሚጠበቅባችሁን ሁሉ እንድትወጡ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡

የተከበራችሁ በዞናችን የምትገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች በአዲሱ ምዕራፍ በሀገራችን የተጀመረችውን የልማትና የሰላም ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከሌሎች እምነት ተከታይ ወንድሞች እና እህቶች ጋር ጠንክራችሁ እንድትቀጥሉ በዚህ አጋጣሚ ላሳስብ እወዳለሁ።

ፓርቲያችን ለህዝብ ሰላም ቅድሚያ የሚሰጥና በመጪዉ ጊዚያት የህዝባችንን ጥያቄዎች ለመመለስ አቅዶ ለመሰራት የተዘጋጀ ፓርቲ እንደሆነም በዚህ አጋጣሚ አረጋግጣለሁ፡፡

በመጨረሻም የተከበራችሁ የእስልምና እምነት ተከታይ ወንድሞቼና እህቶቼ ለ1496ኛ ጊዜ በሚከበረው የነቢዩ መሀመድ የልደት በዓል (መውሊድ) ስናከብር የእስልምና ሀይማኖት መገለጫ የሆነውን የመተባበርና የመደጋገፍ መንፈስ ሙሉ በሙሉ አጠናክሮ እንዲቀጥልና ዛሬም የኮረና ቫይረስ ስጋት ነፃ መሆን እስኪቻል ድረስ ጥንቃቄ እንዳይለየን ጥሪየን አቀርባለሁ።

በድጋሚ መልካም የመውሊድ በዓል እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ።

መልካም በዓል!

08/10/2021
10/09/2021

የ2014 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን አስመልክቶ ከወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አድማሱ አወቀ የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፡-

የተወደዳችሁ መላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች!!

የተወደዳችሁ መላው የወላይታ ህዝቦች!

እንኳን ለ2014 አዲሱ ዓመት (እንቁጣጣሽ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!!

አዲሱ ዓመት የብርሃን ወጋገን፣ የአዲስ ተስፋ ጅማሮ፣ የሰላም፣የፍቅር፣ከአሮጌው ወደ አዲሱ የምንሻገርበት፣ አዲስ ተስፋ ሰንቀን ወደ ብልጽግና ጉዞ የሚናጠናክርበት በመሆኑ በመላው ኢትዮጲያውያን ዘንድ በየዓመቱ በታላቅ ስሜት የሚከበር ተወዳጁን የዘመን መለወጫ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ስል ላቅ ያለ ደስታ ይሰማኛል፡፡

በአድሱ ዓመት ያቀድነው የሚሳካው ተባብረን በአንድ መንፈስ በወንድማማችነት ስንሰራ ብቻ ነው፡፡ ህዝባችንን ማሻገር የምንችለውም እውነት ላይ ቆመን በፍቅር፣በመተሳሰብ ፣በመተጋገዝ ስንሠራ ነው፡፡

እንደምናውቀው አዲስ ዓመት ሲመጣ ሰው ሁሉ በአዲስ ተስፋ ተሞልቶ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ከወዳጅ ዘመዱ ጋር መልካም ምኞቱን ይለዋወጣል።

ምክንያቱም ወርሃ መስከረም የዓመቱ መጀመሪያ የተስፋ ብስራት መንገሪያ ነውና። እኔም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ መላው ሕዝባችን አዲስ ተስፋን ሰንቆ ዓመቱን በሠላም እንዲጀምር፤ የጀመረውም እንድሰምርለት ዘንድ ምኞቴን ስገልጽ አሁንም በድጋሚ በራሴና በዞኑ ብልጽግና ፓርቲው ስም ኩራት ይሰማኛል፡፡

ጥላቻን ነቅለን ፍቅርን እየተከልን የጀመርነውን የለውጥና የዕድገት ጉዞ እንድናስቀጥል ብሎም የሕዝባችንን ችግር ደረጃ በደረጃ እየለየን እንድንፈታ ከምንግዜውም በተለየ መልኩ የለውጥ ሀሳብን በማመንጨትና በመተግበር አጠቃላዩ የዞናችን ማህበረሰብ እንዲንቀሳቀስ፣ ተግቶም እንዲሰራ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የሀገራችን የጸጥታ ሀይሎች የሚያደርጉት የሀገራችን ሉአላዊነትና ነጻነት የህልውና ዘመቻ ስኬታማ እንዲሆን የህዝባችን ድጋፍ ተጠናክሮ ድል የምናደርግበት እና የትህነግ ወራሪ ሰራዊት ግብአት-መሬት የሚፈፀሚበት ዓመት ይሁንልን።

ለዚህም መላው የዞናችን ህዝቦች ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን ደጀንነትን ለመግለጽና አሸባሪው ህወሓት ጁንታ ቡድንና ሸኔን ለማውገዝ ብርድ፤ ፀሐይና ዝናብ ሳይበግራችሁ ሀገርን ለማስቀጠል ታርካዊ ህዝባዊ ድጋፍ ሰልፍና አቅማችሁ የቻለውን ሁሉ አቀፍ ድጋፍ አድርጋቸዋልና ልዩ ክብር አለኝ።

ደካማ ኢትዮጵያን ማየት ዓላማቸው ያደረጉት ምዕራባዊያን ፥ ህወሓት ህጻናትን በጦር ሲያማግድ፣ የመንግስትን የተናጠል የተኩስ አቁም እርምጃ በመጣስ ቡድኑ ወረራውን በማስፋፋት ንጹሀንን ሲጨፈጭፍና ሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ሲፈጽም፥ አለማውገዛቸው ብቻ ሳይሆን ለትግራይ ህዝብ የተላከላቸውን ሰብአዊ እርዳታ ለእብሪተኛው የትህነግ ሠራዊት በማደል ህዝቡን ለከፋ ጉዳት እየዳረጉ መሆናቸውን እያዩ ይገኛሉ፡፡ይህም ለኢትዮጵያ ያላቸውን ጥላቻ ያሳዬ ነው።

ድል ያለመስዋዕትነት አይገኝምና ኢትዮጵያ የውስጥና የውጪ ጠላቶች የደቀኑብን ጫና ተቋቁማና ተቻችላ በቅርቡ በድል ትወጣለች።

የምንጽፋቸው፣ የምንናገራቸውና በሌሎች የተግባቦት ዘዴዎች የምናሰራጫቸው መረጃዎች ከአሉባልታ ይልቅ ጀግንነታችንን፣ ልማታችንን፣ የሐገራችንን ሉአላዊነት፣ የህዝባችንን አንድነትና ብሩህ ተስፋችንን የሚያጎሉ ሊሆኑ ይገባል፡፡

ሰላም ወዳድና ለውጥ ናፋቂው ህዝብ ፓርቲያችን ለመሰራት ያቀዳቸው በኢኮኖሚያዊ፤ በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች ላይ የጀመራቸዉን የብልጽግና ጉዞ አጠናክሮ እንዲሰራ በዚሁ አጋጣሚ አሳስባለሁ፡፡

6ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሰኔ 14 የተካሄደውን ምንም ሰው ሳያስገድዳችሁ በራሳችሁ ፊቃድ የተጀመረው ሀገራዊ ለውጥና ሀገር እንዲቀጥል አድርጋችኋልና ቀሪ በመስከረም 20 ላይ የሚካሄደው ምርጫ በንቂስ ወጥታችሁ ብልጽግና ፓርቲን እንዲትመርጡ በዚህ አጋጣሚ ላሳስብ እወዳለሁ።

መላው የዞናችንን ሕዝቦች ራሳቸውንንና ወገኖቻችንን ከኮሮና በሽታ እየተከላከልን ባለን ነገር ሁሉ በኢኮኖሚ አቅመ ደካማ የሆኑ ግለሰቦችን በመርዳት፣ በፍጹም ወንድማማችነትም ካለን ላይ በማካፈል በኢትዮጵያዊነት መተሳሰበን በዓሉን እንድናከብር ወንድማዊ ጥሪዬን እያቀረብኩ፣ በዓሉ የሠላም፣የፍቅር፣ የደስታ እንዲሆንላቹ እመኛለሁ፡፡

በድጋሚ ለመላው የሀገራችንና የወላይታ ህዝብ አዲሱ አመት የሰላም፤ የጤና፤ የብልጽግና አመት እንዲሆንላችሁ ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡

እንኳን በሠላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ!!
መልካም አዲስ ዓመት!!

ከዬላጋ ቃታ የተሰጠ ምስክርነት አሸባሪዎቹ ጥጋቡ ማርቆስ፤ መንግስቱ ኦናሼና ተሰማ ባልቻ በጀግናው ተስፋዬ ይገዙ ላይ ያነጣጠሩት ውሸት ዜና ተቀባይነት የሌለው መረጃ ስለሆነ መቀበል እንደማይቻ...
06/09/2021

ከዬላጋ ቃታ የተሰጠ ምስክርነት

አሸባሪዎቹ ጥጋቡ ማርቆስ፤ መንግስቱ ኦናሼና ተሰማ ባልቻ በጀግናው ተስፋዬ ይገዙ ላይ ያነጣጠሩት ውሸት ዜና ተቀባይነት የሌለው መረጃ ስለሆነ መቀበል እንደማይቻል ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ያደረገው የወላይታ ዬላጋ አደረጃጄት አሳውቋል::

እኛ የወላይታ ዬላጋ ቃታ ስብስቦች ከጀግናው ወንድማችን ተስፋዬ ይገዙ ጎን ሆነን ትግላችን አሸባርውን የህወሓትና ሼኔ የውሼት ፕሮፓጋንዳን እንቃወማለን::

#ተስፋዬ ማነው??

ተስፋዬ ፈጣሪን የምፈራ ለእውነት የቆመ ለሕዝባችን ከፈጣሪ የተሰጠን ልዩ የወላይታ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ስጦታ ጀግና የወላይታ ሙሁር ነው::

አቶ ተስፋዬ ይገዙ ለወላይታ ህዝብ ልዩ ክብር ያለዉ ጀግና የወላይታ ልጅ ነዉ፡፡

አቶ ተስፋዬ ይገዙ ፀሐይ የሞቀዉ ሀገሩ ያወቀዉ ብዙ ምሁራኖች የተመሰከሩለት ጀግና የወላይታ ልጅ ነዉ፡፡

እሱ ስወለድም ጀግና ነዉ፣ ሙስና እና ህገ ወጥ ድርጊቶችን ስቃወም የነበረ ለህዘብ ስል ለስራዉ ልዩ ክብር የሚሰጥ የህዝብ ልጅ ነዉ። በርግጥም ለብዙዎች የሚያስጨንቃቸዉ የእሱ ጀግንነትና ማንነት ነዉ፡፡

አንዳንድ አልባልታ ወሬን የሚሰራጩ ግለሰቦች እንደሚሉት ሳይሆን አቶ ተስፋዬ የወላይታ ህዝብ ጉዳይ ያገበኛል ብሎ የተለያዩ መድረኮችን ረግጦ የወጣ ጀግና አመራር ነዉ፡፡

አሁንም ብሆን ለወላይታ ብሎም ለሀገር ህዝቦች ደከመኛ ሰለቸን ሳይል ያለእረፍት እየሰራ ይገኛል፡፡

ተስፋዬን ስንደግፊና ስንወድስ ለማጋነን ሳይሆን በምክንያት ነዉ፡፡ ወላይታ ባለፉት ሁለት ዓመታት በፖለቲካና በፀጥታ በሌሎች ህዝቦች ዘንድ በመጥፎ ስም ስትጠራ ከነበረበች ጊዜ በብዙ ትግል ቡኃላ አሁን የነበረችዉ ሠላምና ጣዕም ያለዉ የዱሮ የወላይታ ማንነቷን አምጥተዋል፡፡ይህ ደግሞ የሆነዉ ፋና ወግ የሆነዉ ታላቅ ከወላይታ ህዝብ ጋር በመተባበር ነዉ፡፡

አቶ ተስፋዬ ለወላይታ ህዝብ ልዩ ክብርና አከብሮት ያለዉ፤ ከኔ ክብር የህዝብ ክብር ይበልጠኛል ብሎ በተለያዩ መድረኮች ትግል ስያደረግ የቆየ አሁንም ብሆንም የወላይታ ህዝብ ጥያቄን ለማስመለስ ልዩ ትኩረት እያደረገ ይገኛል፡፡

ማንም ይሁን ምን በወላይታ ህዝብ ላይ የሚደረሰዉን በደልና ጭቆናን እቃወማለሁ ብሎ ደረቱን አዉጥተዉ የሚታገል ጀግና የወላይታ ልጅ ነዉ፡፡ ይህ ነዉ እዉነቱ

“ሆታ ማደናጌ ኬታ አሳ ከጣ ጌስ” እንደሚባለዉ አንዳንድ የFacebook አርበኞች ሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሬ ወለደ አጀንዳ ቀርጾ ቁጭ በል ተነስ እያሉ ይጮሃሉ፡፡

ይህ ጩኸት ደግሞ ለእሱ ጀግንነትንና ጥንካሬን የሚገለጽ እንጅ ክብር የሚቀነስ አይደለም ምክንያቱም በዚህች ሀገር መልካም፤ ደግ እና ጀግና ሰዎችን በሌቦችና ፀረ-ሰላም ሀይሎች አይወዱትም፡፡

በመጨረሻም ወላይታ ብሎም ሀገርን ለማሸበር ሆን ብሎ Fake Account ከፍተዉ የተለያዩ አጀንዳዎችን ቀርጾ በሬ ወለደ መረጃ የሚያሰራጩ ግለሰቦች ከድርግታችሁ እንድቆጠቡ እናሳስባለን!!

ሰሰለዚህ ስለ ተስፋዬ ሰፋ ያለ ፁሑፍ ይዤ እመለሳለሁ ጀግና ይወደሳል ይከበራል ስለ ተስፋዬ ያሳልፍነው ሀያ ሰባት ዓመታቶች ይመሰከራሉ::ስለዚህ እኛ ደሞ ከታርክ ማህደር የገለበጠን ጀግናችን ማወደስ እንቀጥላለን።

Address

Wolaita
Azezo

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Wolaita posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share