22/08/2024
ምንም ብታደርጉ ሰዎች ከማውራት ስለማይመለሱ ዝም /ጋሽ ስብሀት ገ/እግዛቢሂር/
:
♥ ደሀ ብትሆን የመናጢ ልጅ ፤
♥ ሀብታም ብትሆን ዶላር
ያሳበጠው ይሉሀል።
♥ ከሴት ጋር ብትሄድ ሴሰኛ ፤
♥ብቻህን ብትሆን ወፈፌ ይሉሀል
።
☞ ብትፈጥን ቀዥቃዣ ፥ ብትዘገይ ዘገምተኛ ።
☞ ብታወራ ለፍላፊ ፥ ዝምብትል ዝጋታም ።
☞ ብትራመድ አርፎ አይቀመጥም ፥ አርፈህ ብትቀመጥ ዝፍዝፍ
☞ ብትማር አወቅሁ ባይ ፥ ባትማር የአቡጊዳ ሽፍታ ።
☞ ብትወፍር ጠብደል ፥ ብትከሳ በልቶ ማይጠረቃ ።
☞ ብትይዝ ቋጣሪ ፥ ብትለቅ መንዛሪ ። ...
እንደውም አንድ የሀገራችን ተረት አለ"ባልና ሚስት አህያ እየነዱ
ሲሄዱ ተቺዎች አገኙዋቸውና ፦"እንከፎች አህያዋ ሳለች እንዴት
አይሳፈሩባትም" ሲሉ ባል ሰማና ሚስቱን " በይ ፍጠኚና
አህያዋ ላይ ተሳፈሪ" - አላት።
ትንሽ እንደሄዱ ሌሎች ተቺዎች ፦ "ይች ባለጌ ፥ ባል በእግር
እየሄደ ሚስት በጋማ ከብት" ብለው ወረፏቸው።ባል ሚስቱን
አስወርዶ አህያዋ ወገብ ላይ ቂብ አለ ፤ትንሽ እንደተጋዙ ሌሎች
ተቺዎች አገኝዋቸው ፦ "የተረገመ ሚስቱን በእግር እያስኬደ
እሱ በአህያዋ ብለው ወረዱባቸው ።
ባልና ሚስት ድንገት ቢተዉን ብለው አህያዋ ላይ ሲፈናጠጡ
ሌሎች ተቺዎች ደም አገኙዋቸውና "ምን እንስሳ ብትሆን
ለሁለት ይከመሩባታል ግፈኞች ..." የስድብ ናዳ ለቀቁባቸው ።
እንግዲህ ወዳጆቼ ፦ አህያዋን ቢሸከሙ ኖሮ ከዚህ
አይብስምን ?
ስለዚህ ሰዎች ያሉትን ይበሉ አንተ አንተነትህን ሁንና ህሊናህ
አውጥቶና አውርዶ ከተቀበለው ሀሳብ ጋር ተስማማ።
:
ለጮኸ ውሻ ሁላ ድንጋይ መወርወር ጊዜን ማባከን ነው፡፡
#ሼር ማድረግዎን አይርሱ
♥ጋሽ ስብሀት♥
ቶሎ ቶሎ እንዲደርስወ ሼር ያርጉ