Y And G Trading

Y And G Trading Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Y And G Trading, Shopping & retail, Megenagna, Addis Ababa.

፪ 📽️«ሰላም የባለፈውን ኢንተርቪው ብዙ ሰዎች ጠልተውታል። ከምን አንፃር ይመስልሃል?»-ግድ አይሰጠኝም አለም ሁሉ እኔን የጠላ ቢመስለው ይህንን ያውቅ ዘንድ የግድ ነው፤ እኔ ይህን አለም የ...
24/05/2026

፪ 📽️
«ሰላም የባለፈውን ኢንተርቪው ብዙ ሰዎች ጠልተውታል። ከምን አንፃር ይመስልሃል?»

-ግድ አይሰጠኝም አለም ሁሉ እኔን የጠላ ቢመስለው ይህንን ያውቅ ዘንድ የግድ ነው፤ እኔ ይህን አለም የጠላውት ጥንት ነው።

«እስቲ ስለጓደኞችህ ነግረኸኝ አታውቅም። የእኔ የምትላቸው ጓደኞች አሉ?»

-እኛ እራሳችን የእኛ አይደለንም። ልጅነታችን በጉጉት፣ ወጣትነታችን በምኞት፣ እርጅናችንን ደግሞ በጸጸት አሳልፈን እንሞታለን። እኛ የምንረግጠው አፈር ባለዕዳ ነን፤ ቀኑ ሲደርስ እንከፍላለን!።

«ስለዚህ ጓደኞች የሉህም?»

-አንድ አብሮ አደግ ጓደኛ አለኝ። ብዙ ነገሮችን አብረን አሳልፈናል። ስሙ ከአፌ አይጠፋም። የእኔ childhood memory በእሱ መኖር ላይ የተመሰረተ ነው። ብዙ የዩንቨርስቲ አስተማሪዎች እና ታላላቅ የሃይማኖት አባቶች ጋር ተገናኝቼ አውቃለሁ። የጓደኛዬ ምክር ግን ከእነዚህ ታላላቆች የሚበልጥና ልብ ውስጥ የሚቀር ቃል ነው።

«ዋው ዋጋ ያለው ጓደኝነት ነው ያላችሁ!»

-ተሳስተሻል ይልቅስ ዋጋ የሌላቸውን ነገር ትርጉም ሰጥተን የኖርነው እኔ እና እሱ ብቻ ነን!።

«እሺ ከብዙ የዩንቨርስቲ አስተማሪዎች በላይ ብሎም ከታላላቅ የዩንቨርስቲ አስተማሪዎች በላይ የእሱ ምክር ለእኔ ዋጋ ነበረው ብለኸኝ ነበር። ምን ብሎ ቢመክርህ ነው?»

-ኦው እስከዛሬም አልረሳውም። ምን አለኝ መሰለሽ፦አተ..! ምሳ እንደምትበላ ሳታረጋግጥ ቁርስህን ቶሎ እንዳታራው። ካራኸው ግን ሞኛሞኝ ብዳታም ነህ!።

«ይቅርታ ለሰው ክብር ስትል እንደዚህ አይነት ቃላት እዚህ ባትጠቀም።»

-ለየትኛው ሰው? ይሄ ቀብር ስንት ሰዓት ነው ተባብሎ ቀብሮ ለሚረሳኝ።

«ይሄን ጥያቄ እንለፈውና ለፍቅር ያለህን አመለካከት ብትነግረን?»

-እኔ ለፍቅር ያለኝ አመለካከት እንዲህ ነው፦በልባችን ውስጥ ያለው አንበሳ ተኝቷል፤ መቼ ነው የሚነቃው አህያው?።

«ባለፈው ፍቅረኛ እንደሌለህ ነገረኸን ነበር። ዛሬስ?»

-ስለአፍቃሪ ወይም ስለአድናቂ በመወያየት ግዜዬን አላቃጥልም። ምክንያቱም የመጀመሪያው ልቡ የታወረ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ አዕምሮው የተዘጋ ነው።

«ነገር ግን ትዳር ደስ የሚል ነገር ነው። በዚህ ምክንያት ብዙ ሀዘንተኛ ሰው በደስታ ተለውጧል»

-በነገራችን ላይ ለማውራት ያሰብሽው ነገር በደንብ ገብቶኛል። ነገር ግን ደስተኛ ትዳር ማለት በሰማይ ለመብረር አንድ ክንፍ ማግኘት ነው። ሌላኛው ክንፍ ባለቤታችን ጋር ነው።

«እሺ ከእንስሳት ድመት እንደምትወድ ነግረኸኝ ነበር። ለምንድነው ድመት የምትወደው?»

-ስለድመት ማውራት ከጀመርኩ ሌላኛው ምዕራፍ ቢከፈት እራሱ አይበቃንም። ቢሆንም ግን ድመት እያደገች ስትመጣ በብልጭልጭ ነገር መጫወት ታቆማለች። ይህ የህይወት ትምህርት ነው።

«ይሁን እሺ ፍቅር ይዞህ ያውቃል?»

-አዎ። በነገራችን ላይ ወንድ አያቴ ከልጅነቴ ጀምሮ ሴቶችን እንድጠላ እየመከረ ነው ያሳደገኝ። ነገር ግን እሷን ሳገኛት አያቴን ጠላውት።

«እና አሁን ከእሷ ጋር አብራችሁ ናችሁ?»

-ተለያይተናል

«መጠየቅ ከተቻለ በምን ምክንያት ነው የተላላያችሁት?»

-አጥብቀን ስንፈልጋቸው እንደማናገኛቸው ማወቅ አለብን፤ የማወራው ስለካልሲ ነው ሰዎችን በተመለከተ ከረጅም ጊዜ በፊት ያወቅነው እውነታ ነው።

«የምጠይቅህና የምትመልሰው አይገናኝም። እሷን ከካልሲ ጋር እያመዛዘንክ ነው?»

-ኸረ በፍጹም!። ካልሲ የበለጠ ዋጋ አለው። በምፈልገው ሰዓት አገኘዋለሁ።

«እሺ በአንተ እድሜ ላይ ላሉ ወንዶች ምን ትመክራለህ?»

-የማትጋልበውን ፈረስ በጭራሽ አትቀልበው!።

«እሺ። አብዛኛውን ግዜ የአንተን ጽሁፍ የሚተቹ ሰዎች በሶሻል ሚድያ ላይ በዝተዋል ለዛ የሚሆን ምን መልስ አለ?»

-አህያ በፈረሶች እሩጫ ላይ አይሳተፍም። ነገር ግን ሁሌም በጠፋው ፈረስ ላይ መሳቅ ይወዳል።

«መልካም። ተስፋ ስለቆረጡ የአገራችን ወጣቶች ምን መልዕክት ማስተላለፍ ትፈልጋለህ?»

-ለእኔ ትውልድ የምናገረው አንድ ነገር ብቻ ነው። እሱም ነገ የሚባል ነገር የለም ይልቅስ ዛሬህን እንዳትለቅ። ምክንያቱም ነገ የተሻለ እንደሚሆን በማመን ደረጃ የአስር አመት ልምድ አለኝ።

«በመጨረሻ ምን ማስተላለፍ ትፈልጋለህ?»

-በመጨረሻ ማስተላለፍ የምፈልገው ይህ ነው፦ አዳኝ ሁኑ ወይም አደን ሁኑ። ነገር ግን ለአዳኙ ሰለባ የሆነውን ውሻ አትሁኑ!።
©ሞገስ ዘአምድ

ሄዝቦላህ እስራኤልን እየፈተናት ነውየፋይብፕር ኦፕቲክስ ድሮኖች የተዋወቁት በዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ላይ ነበር። አሁን ደግሞ በሊባኖስ በስፋት እየተሰራበት ነው። ዘመናዊው የእስራኤል ጦር ...
30/04/2026

ሄዝቦላህ እስራኤልን እየፈተናት ነው

የፋይብፕር ኦፕቲክስ ድሮኖች የተዋወቁት በዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ላይ ነበር። አሁን ደግሞ በሊባኖስ በስፋት እየተሰራበት ነው። ዘመናዊው የእስራኤል ጦር ሰራዊት በቴክኖሎጂ ባልበለጸጉ ድሮኖች ቁም ስቅሉን እያየ ይገኛል። በቴክኖሎጂ ባይበለጽጉም "ብልህነት የተሞላባቸው" የተባሉት እነዚህ ድሮኖች የሚመሩት በፋይበር "ገመድ" ነው።

👌 በኤሌክትሮኒክ መዝጊያ (Jamming) የማይበገሩ እና በራዳር የማይታዩት እነዚህ ዝቅተኛ ዋጋ ያላቸው ድሮኖች፣ የእስራኤልን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የወጣባቸውን የመከላከያ ስርዓቶች ሰብረው እየገቡ ነው።

👌 እንደ ተለመዱት ድሮኖች በሬዲዮ ሞገድ ወይም በሳተላይት ምልክት የማይመሩት እነዚህ ድሮኖች በቀጭን የፋይበር ኦፕቲክ ገመድ በቀጥታ ከኦፕሬተሩ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ጋር የተገናኙ ናቸው።

ገመዱ ከ10 እስከ 30 ኪሎ ሜትር ሊረዝም የሚችል ሲሆን፣ ይህም ድሮኑ ርቀት ላይ የሚገኙ ኢላማዎችን እንዲመታ ያስችለዋል። በመሆኑም ድሮኖቹ የእስራኤልን ዘመናዊ ራዳሮች ፈተና ሆነዋል።

👌 ድሮኑ ምንም ዓይነት የገመድ አልባ ምልክት (Wireless signal) ስለማይጠቀም፣ የእስራኤል የኤሌክትሮኒክስ ጦርነት መዝጊያ መሳሪያዎች (Jamming systems) ሊያቆሙት አልቻሉም። በተጨማሪም ድሮኖቹ ከቀላል ክብደት "ፋይበር ግላስ" የተሰሩ በመሆናቸው በራዳር ለመታየት በጣም አስቸጋሪ ሆነዋል።

👌 እነዚህ ድሮኖች የእስራኤልን ሜርካቫ ታንኮች የሚጠብቀውን "ትሮፊ" (Trophy) የተሰኘ የመከላከያ ስርዓት ሰብረው ማለፍ ችለዋል። ኦፕሬተሮቹ በገመዱ በኩል በሚመጣው ጥራት ያለው ምስል በመታገዝ፣ ድሮኑ የታንኩ ደካማ ክፍል ላይ እንዲያርፍ ማድረግ ይችላሉ።

👌 እስራኤል ወታደሮች ድሮኖቹን በቴክኖሎጂ ማቆም ስላልቻሉ፣ በአይን ሲያዩዋቸው በጠመንጃ ለመተኮስ ወይም በቤቶች እና በመከላከያ ቀጠናዎች ላይ መረቦችን በመዘርጋት ድሮኖቹ ተጠልፈው እንዲፈነዱ ለማድረግ እየሞከሩ ይገኛሉ።

ያም ሆኖ ድሮኖቹ ከቀላል ፋይበር ግላስ የተሰሩ በመሆናቸው ለከባድ ዝናብና ለኃይለኛ ንፋስ ተጋላጭ መሆናቸው እንደደካማ ጎናቸው እየተገለፀ ይገኛል። ቀጭኑ የፋይበር ኦፕቲክ ገመድ ከዛፍ ወይም ከሌሎች መሰናክሎች ጋር ከተጋጨ ሊበጠስ መቻሉም ሌላው የድሮኖቹ ችግር እንደሆነ ተገልጿል።

ምንጭ፦ AlJazeera

ከ 40 ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች ጠቃሚ ምክሮች 1. የደም ግፊት: 120/80 2. ምት፡ 60 - 100 3. የሙቀት መጠን: 36.8 - 37 4. መተንፈሻ፡ 12-16 5. ሄሞግሎቢን: ወንዶች ...
05/02/2026

ከ 40 ዓመት በላይ ለሆኑ ሰዎች ጠቃሚ ምክሮች

1. የደም ግፊት: 120/80
2. ምት፡ 60 - 100
3. የሙቀት መጠን: 36.8 - 37
4. መተንፈሻ፡ 12-16
5. ሄሞግሎቢን: ወንዶች (13.50-18)
ሴቶች (11.50 - 16)
6. ኮሌስትሮል: 130 - 200
7. ፖታስየም: 3.50 - 5
8. ሶዲየም: 135 - 145
9. ትራይግሊሪየስ፡ 220
10. በሰውነት ውስጥ ያለው የደም መጠን: 5-6 ሊትር
11. ስኳር: ለልጆች (70-130)
አዋቂዎች: 70 - 115
12. ብረት: 8-15 ሚ.ግ
13. ነጭ የደም ሴሎች: 4000 - 11000
14. ፕሌትሌትስ: 150,000 - 400,000
15. ቀይ የደም ሴሎች: 4.50 - 6 ሚሊዮን.
16. ካልሲየም: 8.6 - 10.3 mg/dL
17. ቫይታሚን D3፡ 20 - 50 ng/ml (nanograms per milliliter)
18. ቫይታሚን B12;
200 - 900 pg / ml
🔷እድሜ 40 50 60 እና ከዚያ በላይ ለደረሱት ጠቃሚ ምክሮች፡-

✅የመጀመሪያ ምክር

ምንም እንኳን ህመም ባይሰማዎትም ወይም ምንም ህመም ባይኖርብዎትም በየዓመቱ ቼክ ማድረግ አለብዎት ።

✅ሁለተኛው ምክር

ውሃ ባይጠማም ወይም ባትፈልግም ሁል ጊዜ ጠጣ...ትልቁ የጤና ችግሮች እና አብዛኛዎቹ በሰውነት ውስጥ ባለው የውሃ እጥረት ነው።

✅ሶስተኛ ምክር

ጭንቀት በአጋጠመዎት ጊዜ እንኳን ስፖርት መስራት አያቁሙ ።

✅አራተኛ ምክር

ምግብን ይቀንሱ፣
ከመጠን በላይ የምግብ ፍላጎትን ይተዉት ምክንያቱም መቼም ቢሆን ምግብ ማብዛት ጥሩ አይሆንም።ይመገቡ ነገር ግን መጠኑን ይቀንሱ።

✅አምስተኛ ምክር

በተቻለ መጠን መኪናውን በፍጹም አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር አይጠቀሙ የፈለጉበት ቦታ በእግርዎ ለመድረስ ይሞክሩ።

✅ስድስተኛው ምክር
አይናደዱ

ጭንቀትን ይቀንሱ ... ነገሮችን ለመተው ሞክሩ
በሚረብሽ ሁኔታዎች ውስጥ እራስዎን አያካትቱ ።

የእኛን ጤና መረጃውን ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ!

ጤናና ሰላም ከናንተ ጋር ይሁን
©ጎኅ መረጃ

አሻም ቴሌቪዥን ሲጀመር ጀምሮ እንደነበረ (ቴሌቪዥን ለመከፈት የምትፈልጉ ሰዎች ባታደርጉት)ለምን ተዘጋ ብዬ ሳስብ።።።።።ቴሌቪዥን ለመጀመር ስታስቡአላማችሁ ላይ         1:- በግል ከሆነ...
16/12/2025

አሻም ቴሌቪዥን ሲጀመር ጀምሮ እንደነበረ
(ቴሌቪዥን ለመከፈት የምትፈልጉ ሰዎች ባታደርጉት)
ለምን ተዘጋ ብዬ ሳስብ
።።።።።
ቴሌቪዥን ለመጀመር ስታስቡ
አላማችሁ ላይ
1:- በግል ከሆነ የምትጀምሩት ቴሌቪዥን ዋና አላማው ንግድ ሆኖ ብር ማስገኝት እንደሆነ ብትረዱ። ስለዚህ ሰርታችሁ ለማትረፍ እንጂ ለማስተማር፣ ማህበረሰብን ለመለወጥ፣ ድህነትን ወይም ጭቆናን ለመታገያ ወዘተ የሚሉ እቅዶችን ከአይምሯችሁ ብታወጡት። አላማችሁ ትርፍ ለማግኝት ሲባል መሃበረሰብን መጥቀም ቢሆን።
2:- ትኩረታችሁ በዚህ ሃገር ተጨባጭ ሁኔታ ማህበራዊ ወይንም ፖለቲካዊ ጉዳይ በፍጹም ባይሆን እና መዝናኛውን ብቻ እጅግ በጣም አጠንክራችሁ ለመስራት ብትነሱ።
3:- ትኩረታቸውን አንድ ሁለት ሶስት ጉዳይ ላይ ብቻ ያደረጉ ሚዲያዎች ቢኖራችሁ። ለምሳሌ አዝናኝ የሆነ ድራማ እና ከድራማ ጋር የተያያዙ ጉዳዬች ብቻ፣ አዝናኝ የሆኑ ሪያሊቲ የስፖርት ኮምፒቲሽን ብቻ፣ አዝናኝ የሆኑ የጤና ሪያሊቲ ሾዎች ብቻ፣ አዝናኝ የሆኑ የምግብ ኮምፒቲሽን ሾዎች ብቻ ወዘተ ቢሆን። እስካሁን በኢትዮጵያ እንዲህ አይነት ቲቪ ስለሌለ።
።።።።
ፕሮግራሞችን በተመለከተ።
።።።።
1:- ቀድማችሁ መነሻ የሚሆኑ በቂ ፕሮግራም ሳይኖራችሁ ለቢሮ እና ለሰው ሃይል ከፍተኛ ብር ባታወጡ።
2:- ፕሮግራም ከያዛችሁ በሁዋላም ትንሽ ቢሮ ይዛችሁ እቃ እና ቦታ በተውሶም በኪራይም ቢሆን ፈልጋችሁ ከየፕሮግራማችሁ አንዳንድ ክፍል ቀርጻችሁ ፕሮግራማችሁን ብታዩት። እና ቅርጽን፣ ይዘቱን፣ ሆስቱን፣ ፕሮዳክሽኑን ወዘተ ላይ ብትወስኑ። እዚህ ላይ በዛ ያለ ጊዜ ሰጥታችሁ ብትሰሩ።
3:- የፕሮግራም ቅርጻችሁ ላይ ከወሰናችሁ በሁላም። በአነስተኛ የሰው ሃይል ቢያንስ የሁለት ወር ፕሮግራም ብትሰሩ። ከሁለት ወር ፕሮግራም በላይም ባይሄድ። ምክኒያቱም አይር ላይ ከዋለ በሁዋላ ደግሞ የሰውን ግብረ መልስ እያያችሁ ብታሻሽሉት።
4:- በቂ ፕሮግራም ከያዛችሁ በሁዋላም በሙከራ እና በዝግጅት ከአንድ ወይም ከሁለት ወር በላይ ባትቆዩ። ወዲያው ኤር ብታደርጉ።
።።።
ስቱዲዬ በተመለከተ
።።።
1:- ቲቪ የእይታ ሚዲየም ነው ስለዚህ ለብረሃን፣ ለቀለም ለቁሳቁስ ውበት ትልቅ ቦታ ብተሰጡ
2:- እስቱዲዬው ውስጥ ምንም ቋሚ ነገር ባይኖር። ግድግዳውን ጨምሮ ሁሉንም ተንቀሳቃሽ በማድረግ ለየፕሮግራሙ መለዋወጥ ቢቻል።
3:- እያንዳንዱ የስቱዱዩ እቃ ከአንድ በላይ ጥቅም ቢኖረው። ለምሳሌ እንዱ ግድግዳ ከፊት እና ከሁዋላ የተለያየ ቀለም ቢኖረው ለሁለት ፕሮግራሞች የተለያዩ ባክ ግራውንድ ማግኝት ያስችላል።
3:- የሱቱዲዩ ስፋት እና የጣሪያ ሁኔታን በደም ብታስቡበት። ሰፊ አዳራሽ እና ጣሪያው እረጅም ቢሆን።
4:- የቀረጻ እና የብረሃን የድምጽ እቃዎች መረጣ ብትጠነቀቁ።
5:- ከማስታወቂያ ጋር የተያያዘ ካልሆነ አብዛኛው ፕሮግራም እስቱዲዬ ውስጥ ቢሆን።
6:- ለየት ያለ ነገር ከሌለ ፕራይመሪ እና ሰከንደሪ ቀለሞችን ብታበዙ።
።።።።
ባለሞያን በተመለከተ
።።።
1:- የምትቀጥሯቸው ባለሞያዎች በተለይ በስራ አስኪያጅነት በፕሮግራም ፈጣሪነት ወዘተ ከራዲዩ እና ከመንግስት ቴሌቪዥኖች የመጡ ባይሆኑ። በተለይ ቴሌቪዥኑ የፕሮግራም እና የቢሮ አስተዳደር መሰረቱን እስከሚይዝ ድረስ።
2:- የፊልም እና የድራማ ተሞክሮ ያላቸውንም ለማማከር ካልሆነ በብዛት ባትጠቀሙ። ቴሌቪዥናችሁ የድራማ ካልሆነ በቀር።
3:- በተቻለ ትንሽ ሰው ይዛችሁ ጥሩ ክፍያ ክፍሉ። እረጅም ሰአት የሚሰሩ ቢሆኑ።
:::
ወጪን በተመለከተ
::::
1:- ቢቻላችሁ ገንዘብ ወጪ የሚደረግበትን ሁኔታ አንዴ መስመር እስከሚይዝና ብር የሚወጣባችው ሁኔታዎች ምን ምን እንድሆኑ ዋጋቸውም ምን ያህል እንደሆነ እስክታውቁ ድረስ እራሳችሁ ብትቆጣጠሩ ለሌላ ሰው ባትሰጡ።
2:-
እመለሳለሁ።
©ቴዲ አበራ

ለንግዱ ማህበረሰብ  እና አዲስ ንግድ ፍቃድ ለማውጣት  ለምትፈልጉ  ዜጎች ።  በቀጣይ የምሰጠው  መረጃ ገንዘብ ከፍላችሁ  የማታገኙን ስለሆነ በደንብ ከታዩት  መልካም ነው።ትላንት  አንድ የ...
13/11/2025

ለንግዱ ማህበረሰብ እና አዲስ ንግድ ፍቃድ ለማውጣት ለምትፈልጉ ዜጎች ። በቀጣይ የምሰጠው መረጃ ገንዘብ ከፍላችሁ የማታገኙን ስለሆነ በደንብ ከታዩት መልካም ነው።

ትላንት አንድ የአ.አ ገቢዎች ቢሮ የታዘብኩት ነገር ቢኖር ከ5እና 6 ያለነሱ ግብር ከፋዮች በአጥር ጥግ እየሆኑ ለብቻ ለብቻ እንባ አውጥተው ሲያለቅሱ ተመልክቼ ምክንያታቸውን ስጠይቅ የመጣብኝ ግብር በፍፁም ልከፍለው አልችልም ቤተሰቤ ሊበተን ነው አንዴት መክፈል እችላለሁ ? እንዴት ንግድ ፍቃድ መመለስ እችላለሁ የሚሉ ድምፆችን አስምተውኛል። በእውነቱ ዜጎች እንደዚህ ሲጨነቁ መመልከት እጅጉን አሳሳቢ ነው።

የእኔ ምክር

የሂሳብ መዝገብ ለምትይዙ ነጋዴዎች።

1 የባንክ አካወታችሁ ላይ በፍፁም ከሽያጭ ውጭ ምንም ገንዘብ እንዳይገባ መጠንቀቅ አለባችሁ ተሳስቶ እንኳን ሰው ብር ቢልክላችሁ ከባድ ነው ነው የብሩን ምንጭ ትጠያቃላችሁ + ለተገዛው እቃ በሙሉ ከሂሳባችሁ መከፈል አለበት።

ለምሳሌ በባንክ አካውንታችሁ 100,000 ብር ቢገባ ገቢዎች 100,000*35% =35,000 ብር ግብር ይጠይቃሉ ።

2 ሽያጫችሁ በትንሹ 21% ትርፍ ሊኖረው ይገባል ።

ለምሳሌ አንድን ዕቃ በ100 ገዝታችሁ ከሆነ በትንሹ በ121 ብር መሸጥ ይኖርባችኋል ይህ ሳይሆን ቀርቶ በ100 ብር ገዝታችሁ በ110 ብር ብትሸጡ ገቢዎች 121_110=10*35% 3.5 እያንዳንዱ ሽያጭ ላይ ግብር ይጠይቃል ።

3 ብድር ከሌላ ሰው ስትበደሩ በውልና ማስረጃ መሆን አለበት አንድ ሰው በሰፈር ውል 1ሚሊዮን ብር ቢበደር መንግስት 1,000,000*35%=350,000 ብር ግብር ይጠይቃል ።

4 ዓመታዊ ጠቅላላ ሽያጭ ላይ የሚጣለው ትንሹ ግብር 2.5% መሆኑን አውቃችሁ እራሳችሁን ማዘጋጀት ይኖርባችኋል በኢትዮጵያ ንግድ ህግ መክሰር ያስቀጣል ።

ለምሳሌ ድርጅታችሁ አመታዊ ሽያጭ 2ሚሊዮን ሆኖ 100,000 ብር ቢከስር 2,000,000*2.5%=50,000 ብር ግብር ትከፍላለችሁ።

5 ለንግዱ ከአወጣችሁት አስተዳደር ወጪዎች ውስጥ ኦዲተሮች 35% ውድቅ ማድረግ ይችላሉ ።

ለምሳሌ በአመት ውስጥ ለንግዱ የወጣው ወጪ 100,000 ቢሆን ምንም እንኳን ደረሰኝ ቢኖረውም 35,000 ብሩን ውድቅ በማድረግ 35,000*35%=12,500 ተጨማሪ ግብር መጠየቅ ይችላል ።

6 ከሰው የተበደራችሁት ብድር ቢኖር ለአበዳሪው ግለሰብ ስትከፍሉ በስሙ በባንክ መክፈል ይኖርባችኋል ።
ምሳሌ
አንድ ነጋዴ ከቤተሰቡ ወይም ከወዳጆቹ 1ሚሊዮን ተበድሮ ከሆነ እና በዓመቱ 600,000 ቢከፍል 600,000 በባንክ መሆን አለበት ከአልሆነ ግን በተለያየ ጊዜ በካሽ ቢከፍል ውድቅ ተደርጎ በ600,000*35%=210,000 ብር ግብር ይከፍላል ።

6 አንድ ነጋዴ ከራሱ ሂሳብ ገንዘብ በዓመቱ ማውጣት የሚችለው የትርፉን መጠን ብቻ ነው።

ምሳሌ አንድ ነጋዴ በዚህ ዓመት የተጣራ ተርፍ 400,000 ቢኖራው እና በሂሳቡ ላይ ከሽያጭ የተገኘ ገንዘብ 1,000,000 ቢኖረው አስቻኳይ ነገር ቢያጋጥመው 400,000 ብር ብቻ ማውጣት ይችላል 500,000 ብር ቢያወጣ 500,000_400,000=100,000*35%=35,000 ግብር ይከፍላል ።
7 outstanding inventory =( beginning + total purchase ) _ total sales ከአልሆነ እያንዳንዱን inventory ዝርዝር ማቅረብ ግዴታችሁ ነው።

8 አንዳዴ አልፎ አልፎ Lifo Fifo Average የሚባሉትም ልትጠየቁ ትችላላችሁ ነገር ግን አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ነጋዴዎች Average ስለሚጠቀሙ እረኛው ብዙ አሳሳቢ አይደለም።

Via Eliana Firew

የኮርፖሬት ውድቀት ዋጋ እና የራስን የማደስ ድልኮዳክ፡ የራሱን ፈጠራ የገደለው ግዙፍ ኩባንያኮዳክ በ1975 ዓ.ም. የዲጂታል ካሜራን የፈለሰፈው ኩባንያ ሆኖ፣ በ1996 ዓ.ም. የፊልም ገበያ ...
20/10/2025

የኮርፖሬት ውድቀት ዋጋ እና የራስን የማደስ ድል

ኮዳክ፡ የራሱን ፈጠራ የገደለው ግዙፍ ኩባንያ

ኮዳክ በ1975 ዓ.ም. የዲጂታል ካሜራን የፈለሰፈው ኩባንያ ሆኖ፣ በ1996 ዓ.ም. የፊልም ገበያ ውስጥ 80% ድርሻ እና 28 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ የነበረው ግዙፍ ነበር። ይሁን እንጂ አስተዳዳሪዎቹ በወቅቱ እጅግ ትርፋማ የነበረውን የፊልም ንግዳቸውን እንዳይጎዳ በመስጋት፣ ይህንን አብዮታዊ ፈጠራ ሸፋፈኑት። ለውጦችን ችላ በማለት እና አዲስ ቴክኖሎጂን ከማስፋፋት ይልቅ በቀድሞ ስኬቱ ላይ በመጣበቅ፣ የገበያውን ፍላጎት በትክክል መገመት ተስኖታል። ይህ ስህተት ደግሞ ኮዳክን አሳዛኝ ዕጣ እንዲገጥመው አድርጎታል።

በ2000ዎቹ. ዲጂታል ፎቶግራፍ የፊልም ቴክኖሎጂን ሙሉ በሙሉ ሲቆጣጠረው፣ የኮዳክ የዘገየ ምላሽ ኩባንያውን አደጋ ላይ ጣለው። በ2012 ዓ.ም. ኮዳክ ኪሳራውን ለማወጅ ተገዶ ከገበያ ውጪ ሆኗል። ይህ ታሪክ የሚያስተምረው ቁልፍ ትምህርት፡ ራስህን ፈር ቀዳጅ ለማድረግ መፍራት ሌሎች እንደቀድሙህ ይጋብዛል የሚል ነው። ችላ የተባለ ፈጠራ ያመለጠ እድል ሲሆን፣ መሪዎች የገዛ ስኬታቸውን ምናልባትም ችግር ላይ ይርሚጥል ነገር ቢሆንም እንኳ በአዲስ ቴክኖሎጂ ላይ ኢንቨስት ማድረግ እንዳለባቸው ያረጋግጣል።

ብሎክበስተር፡ የኩራትና የቸልተኝነት ውድቀት

በ2000 ዓ.ም. የፊልም ኪራይ ገበያ ንጉሥ የነበረው ብሎክበስተር፣ የኔትፍሊክስ ባለቤት ሬድ ሃስቲንግስ ኩባንያውን በ50 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ለመሸጥ ያቀረበለትን ጥያቄ በማናናቅ ውድቅ አደረገው። በወቅቱ ብሎክበስተር በዓለም ዙሪያ 9,000 የሚሆኑ መደብሮች የነበሩትና በራሱ የበላይነት የተማመነ ግዙፍ ኩባንያ ነበር። መሪዎቹ የኔትፍሊክስን የዲቪዲ በፖስታ መላክ አገልግሎት "የገበያ ስጋት" አድርገው አልቆጠሩትም፤ በተለይም ደግሞ በቅርቡ የሚመጣው የOnline ስርጭት አገልግሎት የፊዚካል ቪዲዮ ኪራይ ስርዓትን ሙሉ በሙሉ እንደሚያጠፋው መገመት ተስኗቸው ነበር።

የብሎክበስተር ውድቀት ያሳየው፣ ኩራት መሪዎችን ዕውር አድርጎ ለአደጋ እንደሚያጋልጥ ነው። ዛሬ ትንሽ የሚመስል የገበያ ለውጥ ነገ ስርዐቱን ተክቶ ሊያጠፋው የሚችል መሆኑን ማወቅ አልቻለም። በ2010 ዓ.ም. የOnline ስርጭት አገልግሎት በሰፊው መስፋፋት ሲጀምር፣ ብሎክበስተር የገበያ አዝማሚያውን በመከተል ለመላመድ ባለመቻሉ ምክንያት ኪሳራውን ለማወጅ ተገደደ። ይህም ለውጦችን በቸልታ የማየት ዋጋ እንደሆነ በታሪክ ተመዝግቧል።

ኖኪያ፡ በቴክኖሎጂ አብዮት የተረሳው ንጉሥ

ኖኪያ በ2000ዎቹ መጀመሪያ ላይ በዓለም የሞባይል ስልኮች ገበያ ላይ ከ50% በላይ የበላይነት የነበረው ኩባንያ ነበር። ስኬቱም እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ በገበያው ውስጥ እንደማይደፈርስ ንጉሥ ይታይ ነበር። ይሁን እንጂ፣ አፕል አይፎንን በ2007 ዓ.ም. ሲያስተዋውቅ፣ ኖኪያ ይህን አዲስ ፈጠራ ቸል በማለት የገበያውን አቅጣጫ በትክክል መገመት ተሳነው። ኩባንያው የንክኪ ማያ ገጽ እና የመተግበሪያዎች ስርዓት የሚፈጥሩትን አብዮታዊ ኃይልና የተጠቃሚዎችን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ አቃለለው።

ይህ ቸልተኝነትና ለመላመድ አለመፈለግ አስከፊ መዘዝ አስከተለ። ኖኪያ በገበያው ውስጥ ድርሻውን በፍጥነት እያጣ ሄዶ፣ በ2013 ዓ.ም. የስልክ ንግዱ እንዲፈርስ እና ለማይክሮሶፍት እንዲሸጥ ተገደደ። የገበያ ድርሻውም ከ50% በላይ የነበረው ሆኖ ሳለ ከ5% በታች ወረደ። ይህ ታሪክ እንደሚያሳየው፣ ዛሬ ቀዳሚ መሆን ነገም እንደምትቀጥል ዋስትና አይሆንም፤ ዘላቂ ስኬት የሚመጣው በፈጠራና በገበያ ለውጥ ለመላመድ በሚወሰደው ፍጥነት ነው።

ከውድቀት ወደ ዓለም አቀፍ የበላይነት

አፕል – ራሱን እንደገና የፈጠረው ፊኒክስ ወፍ

አፕል በ1997 ዓ.ም. ኪሳራ ሊገጥመው ተቃርቦ ከነበረበት አስቸጋሪ ሁኔታ መውጣት የቻለው ስቲቭ ጆብስ ከተመለሰ በኋላ በወሰዳቸው ደፋር እርምጃዎች ነው። ጆብስ ትኩረቱን በንድፍ፣ በቅለትና በተጠቃሚ ተሞክሮ ላይ በማድረግ የኩባንያውን ማንነት በድጋሚ ገነባ። ከዚያም በኋላ አብዮታዊ ምርቶች የሆኑትን አይፓድ (2001)፣ አይቱንስ (2003) እና በተለይም አይፎን (2007) በማስተዋወቅ እያንዳንዱ ምርት ቀዳሚ ኢንዱስትሪዎችን በራሱ እንዲቆጣጠር አደረገ። ይህ ስትራቴጂ ራስን በራስ የማደስ ጽንሰ-ሀሳብን በተግባር በማሳየት፣ አፕል በታሪክ ውስጥ የ3 ትሪሊዮን ዶላር የገበያ ዋጋ የደረሰ የመጀመሪያው ኩባንያ እንዲሆን አድርጎታል።

ማይክሮሶፍት

ማይክሮሶፍት ቀደም ሲል አሮጌና ቢሮክራሲያዊ እንደሆነ እንዲሁም በዊንዶውስ ላይ ብቻ የተመካ እንደሆነ ይተች ነበር። ነገር ግን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሳትያ ናዴላ ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ ኩባንያውን በመምራት ወደ ክላውድ ኮምፒዩቲንግ፣ የጋራ መሳሪያዎች እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በፍጥነት አሸጋገሩት። ይህ ስትራቴጂያዊ ሽግግርና የባህል ለውጥ ማይክሮሶፍት በAI እና በክላውድ አገልግሎት ዘርፍ መሪ እንዲሆን አድርጓል። በ2023 ዓ.ም. ደግሞ አፕልን በማለፍ በዓለም በጣም ውድ ኩባንያ ሆኗል።

ሳምሰንግ – ወደ ዓለም አቀፍ መሪ የተለወጠ ተጫዋች

ሳምሰንግ በአንድ ወቅት የጃፓን ምርቶች ርካሽ ምትክ ተብሎ ይታይ የነበረ ቢሆንም፣ ከዚህ ማንነት ለመውጣት በምርምርና ልማት፣ በዲዛይን እና በዓለም አቀፍ የገበያ ማስተዋወቂያ ላይ ከፍተኛ ኢንቨስት አደረገ። ሳምሰንግ በዚህም ምክንያት በስማርትፎን (የጋላክሲ ተከታታይ)፣ በሴሚኮንዳክተሮች እና በዲስፕሌይ ማያ ገጾች ዘርፍ ቀዳሚ በመሆን ስር ነቀል ለውጦችን አመጣ። ይህ በፈጠራ ላይ ያለማቋረጥ ኢንቨስት የማድረግ ስትራቴጂ ኩባንያውን ከተከታይነት ወደ ዓለም አቀፍ መሪነት ቀይሮታል።

ውድቀት በዋነኛነት የሚመጣው ከውስጣዊ ችግሮች ነው፤ እነዚህም፡- ቸልተኝነት፣ ራዕይን የሚያውር ኩራት ፣ ለውጥን መፍራት እና አዳዲስ ፈጠራዎችን ወደትግበራ ከመቀየር ይልቅ መደበቅ ናቸው።

በተቃራኒው፣ ዘላቂ ስኬት የሚገኘው በራስን እንደገና በማደስ፣ ደፋር ስትራቴጂያዊ ሽግግሮችን በመውሰድ፣ በፈጠራ ላይ ያለማቋረጥ ኢንቨስት በማድረግ እና በባህላዊ ቅልጥፍናና መላመድ ነው።

የእርስዎ የቱ ነው?🧼 Obsessive-Compulsive Disorder OCD ማለት አዕምሮ ደግመህ አድርግ ካልሆነ ዓለም ያበቃል እያለ ሲያስጨንቅ ነው!🧼 Types of OCD 1️⃣Washing...
08/10/2025

የእርስዎ የቱ ነው?

🧼 Obsessive-Compulsive Disorder
OCD ማለት አዕምሮ ደግመህ አድርግ ካልሆነ ዓለም ያበቃል እያለ ሲያስጨንቅ ነው!

🧼 Types of OCD
1️⃣Washing & Cleaning(መታጠብ እና ማጽዳት) ላይ - እንደገና ካላጸዳሁ/ካልታጠብኩ አንድ መጥፎ ነገር ይከሰታል ብሎ መጨነቅ.

2️⃣ checking( በመፈተሽ ) - በሩን መዝጋቴን check ላድርግ again and again.

3️⃣ Ordering & Symmetry - ነገሮች perfect (ፍፁም) ካልሆነ ሊቋቋሙት የማይችሉት ጭንቀት ዉስጥ መግባት::

4️⃣ Intrusive Thoughts (አስጨናቂ ሀሳቦች)
- እውነተኛ የሚመስሉ አስፈሪ እና አላስፈላጊ በየሆኑ ሀሳቦች መወጠር ::🫤

5️⃣ Hording (መሰብሰብ /ማጠራቀም) - ይህ አንድ ቀን ሊያስፈልገኝ ይችላል፣ መጣል አልችልም ብሎ ሰባራ ዕቃና የተቀደደ ወረቀት ሳይቀር ለማስቀመጥ መገደድ

6️⃣ Mental Rituals - ደህንነት እንዲሰማን በጭንቅላት ውስጥ Repeating prayers፣ መቁጠር ወይም ቃላትን መድገም። [ ፈትያ ]

የናንተ የቱ ነው?

 …ወሬ አላበዛብኝም ፤ ብዙዎቹ ደምበኞቼ እንደ እሱ ናቸው፡፡ በዝምታ ወደመጡበት ጉዳይ መግባት ነው ምርጫቸው፡፡ እኔም ደስ የሚለኝ እንደዚያ ሲሆን ነው፡፡ እዚህ የመጣነው ልንጠናና እና ስለ ...
28/09/2025

…
ወሬ አላበዛብኝም ፤ ብዙዎቹ ደምበኞቼ እንደ እሱ ናቸው፡፡ በዝምታ ወደመጡበት ጉዳይ መግባት ነው ምርጫቸው፡፡

እኔም ደስ የሚለኝ እንደዚያ ሲሆን ነው፡፡

እዚህ የመጣነው ልንጠናና እና ስለ የወደፊት ሕይወታችን ልናወጋ አይደለም፡፡

ያልሆንነውን ነገር በመምሰል የሚጠፋ ጊዜ የለንም፡፡ ስራ ነው የያዝነው፡፡ የንግድ ልውውጥ፡፡ መብራት ይጥፋ ወይ ይብራ የእሱ ምርጫ ነው፡፡

ከዚያ የሚሆነው ዓለም ሲፈጠር ጀምሮ እኛን ላገናኘን ጉዳይ የተገናኙ ወንድና ሴት መሃል የሆነው ፣ የሚሆነው ነው፡፡ ስጋ ከስጋ ይገናኛል፡፡

በቅጽበት ተጠልዞ የጋለ ስሜት በአፍታ ተፈጥፍጦ ወዲያው ይበርዳል፡፡ የልቡን ካደረሰ በኋላ ፍጥጥ ብሎ እያየኝ በረጅሙ ተነፈሰ፡፡

አተነፋፈሱ ከእርካታ ይልቅ የመሰላቸት ይመስላል፡፡ ከሚገባኝ በላይ ቦታ የወሰድኩበት፣የሚተነፍሰውን አየር የተሻማሁት አይነት፡፡

እንድሄድለት ፈልጓል፡፡ ቀልጠፍጠፍ ብዬ ልብሶቼን ለበስኩ፡፡ ገንዘቤን ቆጠርኩ፡፡

ብዙ ሰዎች እንጀራዬ የወሲብ ንግድ ፣ ስራዬ ገላዬን መቸርቸር ብቻ ይመስላቸዋል ፤ በአንድ በኩል ልክ ናቸው፡፡

ይህንን ስራ ስሰራ በዋነኝነት ለሽያጭ የማቀርበውን ነገር ባለማወቃቸው ግን ተሳስተዋል፡፡

ገላን ሸጦ እንጀራ መግዛት ፊት ለፊት የሚታየውና ቀላሉ የስራዬ ክፍል ነው፡፡

ማንም ሴት እየተደናገረች ፣ እየተደናበረችም ቢሆን ልትወጣው የምትችለው የስራዬ ክፍል፡፡

ወንዶች የእኔን አገልግሎት ለመግዛት የሚራኮቱት ከተርታ ሴት የተለየ ሴትነት ወይም አንዳች ምትሃት ኖሮኝ አይደለም፡፡

ከሌሎች ሴቶች የምመረጠው ‹‹ነይ›› ስባል ሳልግደረደር በመምጣቴ ፣ ‹‹ከፊቴ ጥፊ›› ስባል ደግሞ ሳላንገራግር በመጥፋቴ ነው፡፡

የከጀለኝን ወንድ ሻይ ቡና በለኝ ፣ ምሳ ጋብዘኝ ፣ እራት ውሰደኝ ፣ አንሸራሽረኝ ብዬ ደጅ አላስጠናም ፣ ማገዶ አልፈጅም፡፡

የእኔ ዋጋ ከደቂቃዎች በፊት እንዳሻው በፈነጨብኝ ወንድ አፍ ‹‹በይ ሂጂልኝ›› ስባል ሳላኮርፍ መሄዴ ላይ ነው፡፡

ነገ ስንት ሰአት እንገናኝ?

ቅዳሜና እሁድ እንጦጦ ወይ ደብረዘይት አትወስደኝም?

ይህንን ሂውማን ሄር ( ያኛውን ሱሪ )ይሄኛውን ጫማ አትገዛልኝም?

እስቲ የጥፍር መሰሪያዬን ( በናትህ የማሳጄን) ተው ግን የቤት ኪራዬን ክፈልልኝ? ስለማልል ነው፡፡

መወደዴ የሚመነጨው እኔን ብሎ የመጣ ወንድ የሚፈልገውን ካደረገ በኋላ ባሻው ሰአት እንደ ዶሮ ‹‹እሽ›› እንደ ድመት ‹‹ክፍ›› ብሎ ማባረሩን አሜን ብዬ ከመቀበሌ ነው፡፡

_ጆሮ ያለው ሁሉ ይስማ፣ማንበብ የቻለ ሁሉ ያንብብ!!አንብበው ሲጨርሱ ሼር ማድረግ አይርሱ _በተለይ ወጣቶች ወጣትነታችሁን ያለ አግባብ አትግደሉት.. አንብባችሁ ተጠቀሙበት...1. የወሲብ ስሜ...
22/09/2025

_ጆሮ ያለው ሁሉ ይስማ፣ማንበብ የቻለ ሁሉ ያንብብ!!
አንብበው ሲጨርሱ ሼር ማድረግ አይርሱ

_በተለይ ወጣቶች ወጣትነታችሁን ያለ አግባብ አትግደሉት.. አንብባችሁ ተጠቀሙበት...

1. የወሲብ ስሜታችሁን መቆጣጠራችሁ የስኬታችሁ ወይም የውድቀታችሁ ምክንያት ይሆናል።
2. ፖርኖግራፊና ግለ ወሲብ የስኬት ትልቁ ጠላቶች ናቸው፡፡ አእምሯችሁን ያኮስሳሉ፣ ያጠፋሉ።
3. ልክ ግመል ውሃ እንደሚጠጣው አልኮል ከመጠጣት ተቆጠቡ፡፡ ህሊናችሁን ስታችሁ ሞኞች ከመሆን የከፋ ነገርየለም።
4. ደረጃችሁን ከፍ አድርጉ፤ ዝም ብሎ ስለተገኘ ብቻ ዝቅ ባለ ነገር አትርኩ፡፡
5. ከእናንተ የበለጠ ብልህ ሰው ካገኛችሁ፣ ከእነሱ ጋር ስሩ እንጂ ሩሳችሁን አታወዳደሩ።
6. ችግሮቻችሁን ሊፈታላችሁ የሚመጣ ማንም የለም፡፡ የህይወታችሁ 100% የራሳችሁ ኃላፊነት ነው፡፡
7. በህይወት መድረስ ከምትፈልጉበት ደረጃ ካልደረሱ ሰዎች ምክር አትቀበሉ።ከፍላጎታችሁና ከአላማችሁበጋርበየሚሄድ አስተማሪ ገፆችን መርጣችሁ ተከተሉ።
8. የገንዘብ፣የጊዜ እና የእምነት ነፃነታችሁ ጠብቁ።ገንዘብ የምታገኙበት አዳዲስ መንገዶችን ፈልጉ። ገንዘብ ስሩ፤ በሚያሾፉባችሁና በሚቀልዱባችሁ ፌዘኞች ጊዜ አታጥፉ/ችላ በሏቸው፡፡
9. ለመለወጥ ብዙ መፅሀፍ ማንበብ ወይም መርጃ መጻሕፍት ማገላበጥ አያስፈልጓችሁም፤ የሚያስፈልጋችሁ ተግባርና ራስን መገዛት ብቻ ነው። ራሳችሁን ግዙ!
10. አደንዛዥ እጾችን አስወግዱ። በተለይ እንደ ጫትና ሀሺሽ ‚አልኮል መጠጥና ሲጋራ ያሉትን አስወግዱ።
11. በኔትፍሊክስ የማይረባ ይዘት እየተመለከታችሁ ጊዜያችሁን ከምታጠፉ፣ ከዩቲዩብ ክህሎቶችን ተማሩ፣ከGoogle scientifical research ২৬০০:
12.ማንም ስለእናንተ ግድ የለውም። ስለዚህ ዓይን አፋርመሆናችሁን አቁሙና ወጥታችሁ እድሎቻችሁን ፍጠሩ።
13. ምቾት ከሁሉ የከፋ ሱስና ወደ ድብርት/ጭንቀት የሚወስድ ርካሽ ትኬት ነውና አምልጡ።
14. ለቤተሰባችሁ ቅድሚያ ስጡ። መጥፎ ቢሆኑም ወይም ሞኞች ቢሆኑም እንኳ ተከላከሉላቸው፤ ነውራቸውን ሸፍኑ፣ታዘዙ፣ተንከባለቡ፣አክብሯቸውም!
15. አዳዲስ እድሎችን ፈልጉ፤ ከእናንተ የቀደሙ ሰዎችን ተሞክሮ በመውሰድ ተማሩ።
16. መታመናችሁን ቀጥሉበት ሰውን ማመናችሁን ግን አስቡበት፣ማንንም አትመኑ።አንድም ሰው ቢሆን፣ ምንም ያህል ብትፈተኑ እንኳ። በራሳችሁ እመኑ።
17. ተአምራትን አትጠብቁ፤ እንዲፈጠሩ አድርጉ። አዎ፣ ሁልጊዜ ብቻችሁን ላታደርጉት ትችላላችሁ፤ ነገር ግን የሰዎችን አስተያየት አትስሙ።
18. ጠንክሮ መሥራትና ጽናት ማንኛውንም ነገር እንድታሳኩ ያስችሏችኋል። ራስን ዝቅ ማድረግ ከፍ ያደርጋችኋል።
19. ራሳችሁን እስክታገኙ/እስክታውቁ ድረስ መጠበቅ አቁሙ። ይልቁንስ ራሳችሁን ፍጠሩ።
20. ዓለም ለእናንተ ስትል ፍጥነቷን አትቀንስም/አትዘገይምና አታማሩ።በምትችሉትና በአቅማችሁ ተንቀሳቀሱ
21. ማንም ሰው ስለ እናንተ ምንም ዕዳ የለበትም።ለራሳችሁ ራሳችሁን ተጠያቂ አድርጉ።
22. ህይወት የአንድ ተጫዋች ጨዋታ ናት። ብቻችሁን ትወለዳላችሁ፤ ብቻችሁን ትሞታላችሁ። ሁሉም ትርጓሜዎቻችሁ የራሳችሁ ብቻ ናቸው፡፡ በሶስት ትውልድ ውስጥ ትረሳላችሁ ማንምም ለእናንተ ግድ አይሰጠውም። ከመምጣታችሁ በፊትም ማንም ግድ አልሰጠውም ነበር። ሁሉም ነገር የአንድ ተጫዋች ነው፡፡
23. የህይወታችሁ መንገድ ሁልጊዜ ጥገኛ፣ የተጨነቃችሁና ደካማ እንድትሆኑ በሚያደርግ መልኩ የተነደፈ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን መውጫው አንድ ብቻ ነው፤ እሱም ለመውጣት መወሰን። ከራሳችሁ በቀር ማንም እናንተንም ሆነ የምትወዷቸውን ሰዎች አያድንም።
24. ሁሉም ሰው እንደናንተ አይነት ልብ የለውም። ሁሉ

የዓለም የመኪና ምርት በአሁኑ ወቅት በዓመት 75 ሚሊዮን አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 17 ሚሊዮን የሚሆኑት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ናቸው። ይህ አሃዝ እያደገ ሲሆን፣ የም...
17/09/2025

የዓለም የመኪና ምርት በአሁኑ ወቅት በዓመት 75 ሚሊዮን አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 17 ሚሊዮን የሚሆኑት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ናቸው። ይህ አሃዝ እያደገ ሲሆን፣ የምድርን የወደፊት እጣ ፈንታ በተመለከተ ትልቅ ጥያቄ ያስነሳል።

• በ1950፣ የመኪና ምርት 3 ሚሊዮን ሲሆን፣ የዓለም የሕዝብ ብዛት 2.5 ቢሊዮን ነበር።
• በ2000፣ የዓለም የሕዝብ ብዛት 6.1 ቢሊዮን በሆነበት ወቅት፣ 58 ሚሊዮን መኪኖች ተመርተዋል።
• በ2024 ደግሞ፣ የዓለም የሕዝብ ብዛት 8.16 ቢሊዮን ሲሆን፣ 75 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎች ተመርተዋል።

ቴስላ “Clean Cars” የሚለውን አብዮት እየመራ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፤ ነገር ግን እየጨመረ ያለው የምርት መጠን የራሱ የሆነ ፈተና ይዞ ይመጣል።
የተገኙ እውነታዎች እና የወደፊት ተግዳሮቶች
• የሕዝብ ዕድገት: እስከ 2050 ድረስ የሰው ልጅ ቁጥር 15 ቢሊዮን ወይም ከዚያ በላይ ሊሆን ይችላል።
• የምርት ዕድገት: የተሽከርካሪዎች ምርትም 100 ሚሊዮን ወይም ከዚያ በላይ ሊደርስ ይችላል።
• የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መብዛት: አብዛኛዎቹ ተሽከርካሪዎች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ።
• የጥሬ ዕቃ ፍላጎት: ለመኪና ባትሪ የሚያስፈልጉ እንደ መዳብ እና ሊቲየም ያሉ ብረታ ብረቶች ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል።
• የቆሻሻ ክምችት: በምርት እና ፍጆታ ምክንያት የሚፈጠረው የቆሻሻ መጠን ይበራከታል።

ጥያቄው ይህ ነው: ይህ ሁሉ ለውጥ እና ዕድገት የምድርን ዘላቂነት እንዴት ሊጎዳው ይችላል?

ምድር ንፁህ እንድትሆን፣ የቆሻሻ ምርትን በመቀነስ እና ሀብትን እንደገና ጥቅም ላይ በማዋል ላይ የተመሰረተ circular economy መጎልበት አለበት። ይህንን ችግር ለመፍታት እና ዘላቂ የወደፊት ሁኔታን ለመፍጠር ሁላችንም የበኩላችንን መወጣት አለብን።

(ግሎባል ኢኮኖሚ)

15/09/2025

I got over 10 reactions on one of my posts last week! Thanks everyone for your support! 🎉

Address

Megenagna
Addis Ababa
1000

Telephone

+251930439441

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Y And G Trading posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share