Ethiopian Market Place

Ethiopian Market Place business for all!

የሲሚንቶ ነገር የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ግብ ይኖረው ይሆን?--------እስከ ትላንትነዋ ዕኩለ ቀን ድረስ የሲሚንቶ ዋጋ በኩንታል እሰከ 2,000ብር እየተሸጠም እየተገዛም ነው። ለዛውም በደላ...
26/10/2022

የሲሚንቶ ነገር የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ግብ ይኖረው ይሆን?
--------

እስከ ትላንትነዋ ዕኩለ ቀን ድረስ የሲሚንቶ ዋጋ በኩንታል እሰከ 2,000ብር እየተሸጠም እየተገዛም ነው። ለዛውም በደላላና በዘመድ በኩል ተፈልጎ ተፈልጎ ነው። አቶ (የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር) ከወር በፊት እንዳሉት ከሆነ፦
ደርባ ሲሚንቶ =590᎐59
ዳንጎቴ ሲሚንቶ =549.49
ኢትዮ ሲሚንቶ =595.66
ሙገር ሲሚንቶ =643.95
ሐበሻ ሲሚንቶ =683.44
ናሽናል ሲሚንቶ =561.39
ካፒታል ሲሚንቶ =633.38
ኩዩ ሲሚንቶ =628.10
ኢስት ሲሚንቶ =595.66
ፒዮኒር ሲሚንቶ =510᎐04 ብር
እንዲሸጥ መወሰኑን አብስረውልን ነበር ምናልባት #ዋሽተውን ካልሆነ በስተቀር።

የፖለቲካው ጀርባ አጥንት ኢኮኖሚው ነው ወይም የኢኮኖሚ ጡንቻ የመጨረሻው መዳረሻ የፖለቲካ ሰፈሩ ነው ይባላል። በዘመነ ሕወሓት አገዛዝ ይህንን እውነታ በተግባር አሳይተውናል። #የራሴ ናቸው ያሏቸውን ዘግናኝ ቱጃር አድርገው #ሌሎች ያሏቸውን በእስር እንድማቀቁና ከአናት አናት እየኮረኮሙ አንቀው መያዛቸውን ሳስብ ብዙ፣ብዙ ጥያቄዎች ወደ አእምሮዬ መፍሰስ ጀምረዋል።

በዚህም በቀዳማዊ ኢህአዴግ ዘመን በተዘረጋው ኢ-ፍትሐዊ ግብይት ዕድል በግንባታ ማቴሪያል (ብረት፣ ሲሚንቶ፣ የኤለክትሪክ፣ የሳኒቴሪ ወዘተ) ግብይት የደለቡ ሺዎች እንዳሉ ይታወቃል። ዛሬም ታሪክ ራሱን እየደገመ እንዳይሆን ፈራሁ። አሁን ለማንሳት የፈለኩት ስለ ሲሚንቶ ነው። ሲሚንቶ ከጥቁር ገበያው ዶላር ግቢይት ጋር ይመሳሰልብኛል። በኩንታል ከ10 እስከ 100 ብር መጨመር በአንድ ጀምበር ሚሊየነር የሚያደርግ ነው፤ የወደድከውን ባለሀብት የጠላሄውን የሚታደህይበት፣ ለሥራም፣ ለዝርፍያም የተመቻቸ የምርትና የግብይት ዘርፍ መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን?

የዚህን ምክንያት ያለ ፍርሃት ድምጻችን ከፍ አድርገን መጠየቅ አለብን። የፍትሕ ጥያቄ ነውና። በመጨረሻም #ሶስት ጥያቄዎች አንስቼ ላብቃ።

፩. ዛሬ እንደ ሰሜኑ ክፍለ-ሀገራችን ጦርነት ሀገሪቷን እየናጣት ያለውና በግንባታው ዘርፍ የተሰማሩንም ሆነ ችርቻሮ ፈላጊዎችን በጠራራ ፀኃይ እንዲዘረፉ የተተወው ለምን ይሁን?

፪. መንግሥት ይህንን ግብይት ለማስተካከል ያልፈለገው ወይም በዚህ ልክ አቅመቢስ የሆነው ለምን ይሁን?

፫. በርግጥም አቅም ከድቶት ነው ወይ? ግብይቱ እንዲወሳሰብ ለምን ተፈለገ?
ወይስ ሌላ ምስጢር አለው?
.. ተጨማሪ ጥያቄ ካላችሁ እናንተ ጠይቁ።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Market Place posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian Market Place:

Share