Change your life

Change your life ለውጥ ይፈልጋሉ የራስዋን ቢዝነስ እንዲኖረው ይፈልጋሉ

Permanently closed.
23/11/2023

ግቦችን ለማሳካት የሚረዱ ተግባራዊ ነጥቦች

አንዳንዶቻችን የሆነ ግብ ይኖረንና እንዴት ወደ ተግባር መቀየር እንዳለብን ግራ ተጋብተን ግባችንን በአእምሯችን እያመላለስን ተቀምጠን ይሆናል፡፡ ሌሎቻችን ደግሞ ዓላማችን ከግብ እንዲደርስ የተሳሳቱ ሙከራዎች አድርገን ስኬት እርቆን እየኖርን ይሆናል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በመቀጠል ግቦችን ለመተግበር የሚረዱ ጠቃሚ ነጥቦች፣ ምክሮች እንዳስሳለን፡፡

እነዚህ ቀጥሎ የምንዘረዝራቸዉ 9 ነጥቦች ግብን ለማሳካት እንደሚረዱ በስነ-አዕምሮ ተመራማሪዎች፣ ራስን ማሻሻል ላይ በሚሰሩ ጠበብት የተመሰከረላቸዉ ናቸዉ፡፡ነጥቦቹ በተግባር ተፈትነዉ ዉጤታማ የሆኑም ናቸዉ፡፡

ወደ ስኬት የሚያደርሱ ዘጠኝ ደረጃዎች

1. በህይወት ዉስጥ ዓላማን ጠንቅቆ ማወቅ፡- ወደምንሄድበት/ ወደምንደርስበት መዳረሻ ጉዞ ከመጀመራችን በፊት ጠንቅቀን ልናዉቀዉ የሚፈባ ነገር አለ፤ እሱም ዓላማ ነዉ፡፡ " ወደየት እንደምትሄድ የማታዉቅ መርከብ ንፋሱም አያግዛትም " እንደሚባለዉ ሁሉ እኛም ዓላማችንን ጠንቅቀን ማወቅ ቁልፍ ነገር ነዉ፡፡

2. የራስ የሆነ የህይወት ፍልስፍና/መመሪያን/መያዝ፡- ከፈረሱ ጋሪዉ እንዲሉ እንዳይሆንብን ስለስኬት ከማብሰልሰላችን በፊት ስለራሳችን የህይወት ፍልስፍና ማወቅ ትልቅ ሚና አለዉ፤3. የቅርብ ፣የመካከለኛ እና የወደፊት/የሩቅ/ ጊዜ ዕቅድ ማዉጣት፡- የሰዉ ልጅ ሁሉን ነገር በአንድ ጊዜ ማከናወን አይችልም እንደደረሰበት እድገት ደረጃ መጠን እና ክህሎቱ ይወሰናል፡፡ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ መጠን ቅደም ተከተል በመስጠት ሊከናወን በሚችል መልኩ ዕቅድ ማዉጣት ይገባል፡፡

4. ለእያንዳንዱ ዕቅድ /ድርጊት/ግልፅና ሊደረስበት የሚችል ግብ ማስፈር፡- በጥናት የተደገፉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የዓለማችን አስር በመቶዉ ያህሉ ግልፅ የሆነ ግብ ሲኖራቸዉ ያንኑ ለመተግበር ደፋ ቀና ሲሉ ቀሪዉ የዓለማችን ዘጠና በመቶ አቅጣጫ የሌለዉና ዝም ብሎ ወጥቶ የሚገባ ነዉ ማለት ነዉ፡፡ እንግዲህ ዓለማችን እየተመራች ያለችዉ በእነዚህ ጥቂት ሰዎች ዓለማ/ግብ (ጥረት/ተስፋ) / አለበለዚያም ከመነሻዉ የላቀ መዳረሻ ነዉ ማለት ነዉ፡፡

5. ዉጤቱን ለማሳካትም የጋለ ስሜትን ማዳበር፡- ከሁሉም በላይ ስኬታማ ለመሆን የማከናወን እና ስራን በስኬት ለማጠናቀቅ የጋለ ስሜት አስፈላጊ ነዉ፡፡

6. ግቦችን ለማሳካት የጊዜ መርሃግብር መንደፍ፡- ተፈጥሮ እንኳን ቀን እና ሌሊት ፣ክረምት እና በጋ፣ ጠዋት እና ከሰዓት … በሚል የተከፈለ ነዉ ይህ የየራሱ መተግበሪያ አለዉ፤ እንዲሁ የሰዉ ልጅ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ግቦቹን ለማሳካት መርሃግብር መንደፍ ይጠበቅበታል፡፡ኣመትን ለአስራሁለት ወራት መክፈል፣ በስድስት ወር ለሁለት በመክፈል፣ በሶስት ወር ለአራት በመክፈል መርሃግብር መንደፍ፡፡ ሳምንትን ቀናትን ሰዓታትን በመከፋፈል መርሃግብር መንደፍ ይኖርብናል፡፡ መርሃግብር መንደፍ የራሱ የሆነ ጥቅም አለዉ (ለምሳሌ ከጭንቀት ራስን መጠበቅ)

7. ለማከናወን በተነሱት ድርጊት የማይናወፅ እምነት እና በራስ መተማመን ማጎልበት፡- እዚህ ጋር ከአሜሪካዉ ፕሬዘዳንት አብርሃም ሊንከን የህይት ተሞክሮ ብዙ ነገር እንማራለን፤ አብርሃም ሊንከን ለአገሩ ህይወቱን ለመስጠት የወሰነዉ በወጣትነቱ ነበር፡፡ ነገር ግን ካጋጠመዉ መዉደቅ መነሳት አንፃር አገሩ አፍ አዉጥታ የአንተን ግልጋሎት አልፈልግም ያለችዉ እስኪመስል ድረስ ተፈትኗል፡፡ለህግ አዉጪነት / አርቃቂነት ተወዳድሮ ነበር አላለፈም፣ ወደ ኮንገረንስ ዉስጥ ለመግባት ሞከረ አልተሳካለትም፣ የመሬት አስተዳደር ቢሮ ዉስጥም ለመግባት ያደረገዉ ሙከራ አልተሳካም ፣ ሁ

23/10/2021
19/07/2021

ህይወት መጀመሪያዋና መጨረሻዋ አንድ ነው።
፨፨፨፨፨፨፨///////////፨፨፨፨፨፨፨፨
ልብ በል! ባለ ማወቅ ትጀምራለህ በመዘንጋት ትጨርሳለህ።
እውቀት አላመጣህም ይዘህም አትሄድም።
በለቅሶ ትጀምራለህ በጭንቀት ትጨርሳለህ።
በሰው እቅፍ ትጀምራለህ በሰው ሸክም ትጨርሳለህ፤ ልደትህና ሞትህ በምን ይለያያል? ሞትህስ ከልደትህ በምን ይከፋል።
ህይወት መጀመሪያዋና መጨረሻዋ አንድ ነው። በዚህ የተነሳ ጠቢቡ እንዳለው ሁሉም የከንቱ ከንቱ ነው። ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም።
ልብ በል! የአለም ውበት ግን ከንቱነት ነው። አለም አዲስ ነገር ቢኖራት እኛን እንዴት በፀፀተን። ሞት የእወነት መጨረሻ ቢሆን እንዴት በተቆጨን።
/ከመርበብት ገፆች/
ስለዚህ ጀግናዬ....! ዘውትር ህያው የሚደርግህን፣ ከትውልድ ትውልድ የሚያሻግርህን ነገር ከውን። አዎ! ሁሌም መልካሙን፣ በጎውን ነገር አድርግ።
አዎ! በእርግጥም፦
እርሱ ነውና ሞትህን በህያውነት የሚተካልህ፤
እርሱ ነውና ማለፍህን የሚያስቀርልህ።
ሰናይ ቀን ይሁንልን

ዶክተር ወ/ሮ አበበች ጎበና አረፉ😢😭🚢🚢🚢ከ30 ዓመታት በፊት የክብር ዶክተር ወ/ሮ አበበች ጎበና ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ያቀናሉ። እናም ያኔ ወቅቱ በሀገሪቱ የረሃብ አደጋ ያጠላበት ጊዜ ነበርና...
04/07/2021

ዶክተር ወ/ሮ አበበች ጎበና አረፉ😢😭
🚢🚢🚢
ከ30 ዓመታት በፊት የክብር ዶክተር ወ/ሮ አበበች ጎበና ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ያቀናሉ። እናም ያኔ ወቅቱ በሀገሪቱ የረሃብ አደጋ ያጠላበት ጊዜ ነበርና አንዲት ሕፃን የእናቷ አስክሬን እቅፍ ስር ሆና ጡት ለመጥባት ትሞክራለች። ይህ ትዕይንት እጅግ ከፍተኛ ሐዘን ውስጥ ይከታቸዋል።ሕፃኗን ከሌላ አንዲት ሕፃን ጋር ይዘውም ለማሳደግ ይወስዳሉ። እናም ወዲያው 21 ሕፃናትን ለመርዳት ያሰባስባሉ። ሆኖም ባለቤታቸው እና
የሥራ አለቃቸው ከሕፃናቱ ወይ ከእኔ አለያም ከሥራዎ የሚል ከባድ አጣብቂን ውስጥ ይከቷቸዋል። ሆኖም እሳቸው ለሕፃናቱ ይወስናሉ።
🚢🚢🚢
በአሁኑ ወቅት ዶክተር ወ/ሮ አበበች ጎበና
በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች ከ12 ሺህ በላይ ሕፃናትን ይረዳሉ። በእሳቸው የርዳታ ድርጅት ሥር ከ1,5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተጠቃሚ መሆናቸው ይነገራል። በሰብአዊ ርዳታ ለጋሽ ድርጅታቸው 265 ቋሚ እንዲሁም 400 ሌሎች ሠራተኞችን ቀጥረዋል።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ነፍስዎ በሰላም ትረፍ🙏🏾🙏🏾🙏🏾

03/07/2021

በህይወት ውስጥ ትልቁ የስኬት ሚስጥር ምቾትን ማዘግየት ነው። ቶሎ እንዲመችህ ከፈለግክ ስኬትህን ትገድበዋለህ ።

የሀብታም እና የድሀ ልዩነትም ያ ነው ቶሎ ቤት መግዛት ፣ መኪና መግዛት ፣ ከአቅም በላይ መዝናናት (ከልኩ ላያልፍ በሚል) ። እንዲ አይነት ሀሳብ ካለህ ቆም ብለህ አስብ ። የስኬት ህግም ምቾትን ማቆየት ነው ።

የተባረከ ቀን ተመኘንላችሁ🙏

 #የረቀቁ ሀሳቦች🔱ምን ይዞ እንደሚመጣ ለማይታወቀው መጪው ጊዜ መፈንጠዝና በምኞት ፈረስ መጋለብ ካላቆማችሁና፣ ትናንትናንና ነገን ትታችሁ ዛሬን መኖር ካልጀመራችሁ ነፃ አትወጡም። ነፃነት አሁ...
30/06/2021

#የረቀቁ ሀሳቦች

🔱ምን ይዞ እንደሚመጣ ለማይታወቀው መጪው ጊዜ መፈንጠዝና በምኞት ፈረስ መጋለብ ካላቆማችሁና፣ ትናንትናንና ነገን ትታችሁ ዛሬን መኖር ካልጀመራችሁ ነፃ አትወጡም። ነፃነት አሁን እዚህ ናት።
ያለህበት ጊዜ ብቻ ናት እውነት ህልውና ያላት። መጪው ጊዜ ምኞትህ፣ ያለፈውም ጊዜ ትዝታህ ነው። ህልውና የላቸውም። የአሁኑን ጊዜ በንቃት ማሳለፍ ንቃተ ሂሊናህና ካለፈውና ከመጪው ጊዜ ሰብስበህ በአሁኑ ጊዜ ላይ ማትኮር ማለት የነፃነትን ጣዕም ማወቅ ነው።

🔱ፍቅር በራችሁን አንኳኩቶ ያውቃል? በጭራሽ! ምክንያቱም ገና ፍቅር መስጠት አልቻላችሁም። ማስታወስ ያለባችሁ የሰጠነው ሁሉ ወደ እኛው ተመልሶ እንደሚመጣ ነው። ይህም ከህይወት ህጎች አንዱ ነው።መላው ዓለም ከገደል ማሚቶ የተሻለ አይደለም። ጥላቻ እንሰጣለን፣ ጥላቻም ወደኛው ተመልሶ ይመጣል። ሌሎችን እንሳደባለን ከዛም ስድብ ወደኛ ተመልሶ ይመጣል። እሾህ ስንሰጥ እሾህ ወደኛው ተመልሶ ይመጣል፡፡ የምንሰጠው ሁሉ በተለያዩ መንገዶች ወደኛ ተመልሶ ይመጣል። ፍቅርን ካካፈልንም እንደዚሁ በተለያዪ መንገዶች ተመልሶ ወደኛው ይመጣል። ስፍር ቁጥር በሌላቸው መንገዶች ፍቅር ወደ እኛ ተመልሶ ካልመጣ ፍቅር እንዳልሰጠን ማወቅ አለብን፡፡ፍቅር የምትሰጠው እንጂ የምትቀበለው አይደለም።

🔱ጨለማን ማጥፋት አትችሉም!!ጨለማ ጋር በቀጥታ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?ጨለማን በቀጥታ ልታስወግዱት አትችሉም፡፡ ጨለማን ወርውራችሁ መጣል አትችሉም፡፡ ጨለማንም መፍጠርም ሆነ ከሌላ ቦታ ማምጣት አትችሉም፡፡ ጨለማ ጋር አንድ ነገር ለማድረግ የሚቻለው በብርሃን ውስጥ ብቻ ነው፡፡ጨለማውን ለማጥፋት ብቸኛው አማራጭ ብርሀኑን መፍጠር ብቻ ነው።ጨለማ ማለት የብርሀን አለመኖር ነው ጨለማው በራሱ ትርጉም ያለው ነገር አይደለም። ጨለማው እንዲውጣችሁ ካልፈለጋችሁ ብርሃኑን አብሩት፡፡እንደዚሁ ሁሉ ጥላቻችሁ የተፈጠረው በፍቅር አለመኖር ምክንያት ነው። ጥላቻችሁንና ክፋታችሁን ከራሳችሁ ለማራቅ ያላችሁ አማራጭ ማፍቀር ብቻ ነው።

🔱ሰው ሌሎች ሰዎች ስለሱ መጥፎ ነገር ሊናገሩ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ይፈራል። እሱን በተመለከተ ሰዎች ጥሩ ሲናገሩ ይደሰታል፤ ምክንያቱም ስለ ራሱ ያለው እውቀት ሌሎች ስለሱ በሚሰጡት አስተያየት ላይ የተመሰረተ ነው። ስለራሱ ቅጽበታዊ የሆነ እውቀት የለውም፤ ራሱን የሚያውቅበት ቀጥተኛ ተሞክሮ የለውም። ራስን በቀጥታ የማወቅ ተሞክሮ ሊከሰት የሚችል ቢሆንም ከራሳችን_ለማምለጥ ስለምንሞክር ግን አይከሰትም። አይምሮን ለመጋፈጥ የመጀመርያው ዘዴ ሌሎች ስለሚሉት ወይም ለሌሎች እንዴት ሆነን መታየት እንደሚኖርብን አለመጨነቅ ነው። አንድ ሰው መሰረታዊ እሱነቱን በቀጥታ መጋፈጥ አለበት። ለብቻው ሆኖ አይምሮውን በመክፈት ውስጡ ያለውን ነገር መመልከት አለበት። ይህ የድፍረት ተግባር ነው። ከውስጥ ወዳለው ሲዖል ለመግባት የሚያስችል የድፍረት ተግባር....። እርቃን ማንነትን ለመመልከት የሚወሰድ የድፍረት እርምጃ ነው። ታላቅ ድፍረት ያስፈልጋል።

🔱".....ከኢጎ በመነጨ ፍቅር ከተፈቀራችሁ ከትንሽ ጊዜያት በኋላ በአፍቃሪ እጆች እንደታቀፋችሁ ሳይሆን በብረት ሰንሰለት እንደተጠፈራችሁ ይሰማችኋል። ከትንሽ ጊዜያት በኋላ ውብ ንግግሮችን ሲናገር፣ ውብ ዘፈኖችን ሲዘፍንላችሁ የነበረው ፍቅር፣ በውብ ዘፈኖቹና ንግግሮቹ ውስጥ መርዝ ደብቆ እንደነበር ታውቃላችሁ። የአበቦችን መልክ ተላብሶ የሚመጣው ፍቅር ምንጩ ኢጎ ከሆነ አበቦችን በዳሰሳችሁ ጊዜ እጆቻችሁን የሚወጉ እሾሆችን ታገኛላችሁ......"

#ፌስቡክን ለመታወቅ ሳይሆን ያወቅነውን ለማሳወቅ እንጠቀም፡፡ ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም

ጣሪያህን ንቀለው!ጣሪያህ ምንድን ነው? ጣሪያህ ሁኔታዎች የወሰኑልህና እንዳንተ አይነት ሰው የትም አይደርስም ብለው የደመደሙብህ እይታ ነው ፡፡ ጣሪያህ ምንድን ነው ? በአንተ ሁኔታ የተወለደ...
29/06/2021

ጣሪያህን ንቀለው!

ጣሪያህ ምንድን ነው?
ጣሪያህ ሁኔታዎች የወሰኑልህና እንዳንተ አይነት ሰው የትም አይደርስም ብለው የደመደሙብህ እይታ ነው ፡፡

ጣሪያህ ምንድን ነው ?

በአንተ ሁኔታ የተወለደና ያደገ ሰው በፍጹም ከዚህ ከፍታ በላይ ሊሄድ አይችልም ብሎ ሕብረተሰቡ የደመደመው ገደብ ነው ፡፡

ጣሪያህ ምንድን ነው?

ሰዎች የገቢህን ሁኔታ ፣ የትውልድህን አመጣጥና የትምርት ደረጃህን ከደመሩና ከቀነሱ በኋላ የራሳቸው ድምዳሜ ላይ በመድረስና መስመርን በማስመር በላይህ ላይ የከደኑት ክዳን ነው ፡፡

አየህ ፣ ሕብረተሰቡ ይህንን የማድረግና “ከዚህ አታልፍም” ብሎ መስመር የማስመር መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡ አንተም በበኩልህ ያንን መስመር #አልፈህ የመሄድ ሙሉ መብት አለህ ፡፡

ያለፈው ትውልድ ያቆመበት ላይ መቆም የለብህም ፣ #አዲስ ፈር ልትቀድድና ወደ አዲስ አቅጣጫ ልትዘልቅ ይገባሃል ፡፡

ይህ እንዲሆን ግን “ባለሁበትና ሰዎች ነህ ብለው በወሰኑልኝ ሁኔታ አልወሰንም” የሚል ቁርጥ #ውሳኔ ከአንተ ይጠበቃል ፡፡

ይህንን አትዘንጋ ብርታቶችህ ፣ የሚሳኩልህ ፣ የሚያጓጉህና ብታሳድጋቸው ለስኬት የሚያበቁህ ናቸው ፡፡

ድካሞችህ ደግሞ ብዙም የማያጓጉህ፣ ለማድረግ ስትሞክራቸው እጅግም የማይሳኩልህና የሚያታግሉህ ነገሮች ናቸው ፡፡ የዚህን እውነታ ከመቀበል በላይ ምንም ምርጫ የለህም ፡፡

አብዛኛው የሕብረተሰቡ ክፍል ካለማቋረጥ ድካምህንና ውስንነትህን ነው የሚያሳይህ ፡፡ ያንንም ድካምህን ከጠቆመህ በኋላ ከዚያ ነገር የተነሳ የትም መድረስ እንደማትችል ይነግርሃል ፡፡

በድካምህና በማትችለው ነገር ተጠቅመሀ ውስንነትህን አልፈህ መሄድና ማደግ አትችልም ፡፡

ማተኮር ያለብህ #ብርታትህ ላይ ነው ፡፡ አእምሮህ የተከፈተለትንና ብርቱ ጎንህን በማዳበር ካለህበት ስፍራና የውልደት ሁኔታ አልፈህ ለመሆን ወደተፈጠርክለት ማንነት ማደግ ትችላለህ ፡፡

ጣሪያህን ንቀለው!

28/06/2021

🔹ቃላት የማይገልጿቸው ስሜቶች አሉ፤ ከቃላት በላይ ግን ድርጊት ይገልፃቸዋል። ህልምህን፣ ፍቅርህን እና ማንነትህ ከቃላት በላይ ተግባር እንዲገልፃቸው ከጣርክ ትክክለኛው መስመር ላይ ነህ።

አስተሳሰብህን ህይወትህን ቀይርchange your thinking change your life   ↪️አንድ ነገር ለማድረግ አስብ ያሰብከውን ለማሳካት አልችለውም የምትለውን ነጥብ አስተወል።ወደ ተ...
28/06/2021

አስተሳሰብህን ህይወትህን ቀይር

change your thinking change your life

↪️አንድ ነገር ለማድረግ አስብ ያሰብከውን ለማሳካት አልችለውም የምትለውን ነጥብ አስተወል።ወደ ተግባር ከመሄድህ በፊት አልችለውም የሚለውን ሀሳብህን ከአእምሮህ ውስጥ በቅድሚያ ለማጥፋት ስራ።

↪️ አእምሮህ ጥሩ ጓደኛህም መጥፎ ጠላትህም መሆን ይችላል።አእምሮህን በፈለግከው አቅጣጫ ለመምራት ስልጡንና ታዛዥ ነው።ይህን የሰላ አእርምሮህን በመጠቀም ሕይወትህ በእውቀት የመጠቀ በሀብት የበለጸገ ማድረግ አልያም ለጥፋት በማጀገን ለእርኩሰት በማመቻቸት ድንዙዝና መናኛ በማድረግ ርባናቢስ ሕይወት እንዲኖርህ ልታደርግ ትችላለህ።

↪️ማልዶ ከእንቅልፍ መነሳት የስኬት ልምድ ነው።ስኬታማ ሰዎች ማልደው በመነሳት ያነባሉ የእለታዊ ስራዎቻቸው ያዘጋጃሉ፣ያደራጃሉ በወረቀት ላይም ቀድመው ያሰፍራሉ ያቅዳሉ።ብዙዎቹ ይህን በአብዛኛው ለማድረግ ሲቸገሩ ይስተዋላል።ቶማስ ጅፈርሰን "ፀሀይ አልጋዬ ውስጥ እያለሁ አትወጣም"።ይል ነበር።

↪️በሕይወት ውስጥ ሁለት ጊዜያቶች አሉ።ትናንትና እና ነገ።ዛሬ አሁናዊ ሁነታዎቻችን ይማዳምጥበት ሲሆን ትናንት እንዴት እንደነበርም የማሰብ አልያም ነጋችን ምን ሊሆን እንደሚችል በመገመት መካከል ራሳችንን ልናገኝ የምንችልበት ነው።ዛሬ ልንቀይረው በማንችለው ትናትናችን ላይ በመቆም ወይም በእኛ ቁጥጥር ውስጥ ስላለው ነጋችን በመገመት ላይ ወሳኝ ሆኖ እናገኛታለን።

↪️ብዙ ሰዎች ነጋቸው ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ ትላንታቸው ላይ በተፈጠሩ ጠባሳዎች ዛሬ ላይ ቆመን በንዴት ሲበሽቁ ይገኛሉ።ይህ ከትናንት የወረሱት አሉታዊ ስሜታቸው ዛሬያቸውን ጨምሮ እንደነጠቃቸው በፍጹም አይገነዘቡም።

ዛሬ ላይ ትናትናቸውን ሲያማርሩና ሲወቅሱ ሲገረሙ ነጋቸው ላይ ልዩነት መፍጠር የሚችለውን የዛሬ ማንነታቸውን በቅሬታ ገመድ ጠፍረው እንደያዙት አይረዱም።

↪️በህይወትህ ስኬታማ ያልሆንክበት ነገር ምንድነው?ለአለመሳካቱ ተጠያቂ የደረግከው በየጊዜውስ የምትወቅሰው ማንነው?መልስህ ምንም ይሁን ምን ከዛሬ ጀምሮ ችግሩ የኔ ነበር ብለህ ሃላፊነቱን ውሰድና የስኬት መንገድህን ጀምር።ባለፈ ሕይወትህ ላይ እክል ለገጠሙህ ሰዎች ሁሉ ይቅርታ የምታደርገው ዛሬ ነው።

እነሱም ይሂዱ አንተም ወደፊት ተጓዝ

Address

Addis Ababa
9484

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Change your life posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share