25/05/2022
ይሄ ትውልድ እና ዘመን እንዴት በአዳም ተረታ?
1. አዝማሪው ባህሩ ቀኜ፡፡ "በሽተኛው በዛ መድኃኒት አነሠው" የሚል ስንኝ አላቸው፡፡
የኔ ዘመን እና ትውልድን ለመግለፅ ምቹ ነው የባህል አርበኛው ንግግር፡፡
አዳም ረታ ዘመኑ እና ትውልዱ "በእንከን የተሞላ በመኾኑ" ሊተወን አልወደደም፡፡ እንጀራ የተባለ ትዕምርት አነሳ ፤ እንጀራ የተባለ ትርክት ተዋሰ ከድርብ ፤ ድርብርብ ኑሮአችን፡፡ (Surplus life)
እንጀራንም በአይኑ ÷ በክብነቱ ÷ በየትየለሌ የጤፍ እድሜ እና ስልጣኔ ውስጥ (Geez and teff civilization) የዚህ ዘመን "መድኃኒት" ሊያደርገው ወኔ ሰነቀ፡፡ (Cultural elite literary courage and critical internal journey ነው፡፡
እንጀራ አንድምታ hegemonic understanding ውስጥ አልነበረም፡፡ የተጣጣለ ፤ የተነወረ የኑረታችን መንገድ ነበር፡፡ ወይ አለማወቅ፡፡
አዳም ታዲያ ሊቀ ሊቃውንት ነውና "እንጀራን ከተነወረበት አነሳ ፤ ጤፍን ደቃቅነቷን አከበራት" የእንጀራውን ዓይን ማያ አደረገው፡፡ ባለ ብዙ እይታ ሠራበት፡፡ ወንድ እንጀራ ጋጋሪ ሆነልን፡፡
ዘመኑ እና ትውልዱ በ Meta narrative አብዷል፡፡ በ hegemonic notion ከስሯል፡፡
አዳም ግን ሌላ ነው፡፡ እንጀራ በአገራዊ ውክልናችን ውስጥ ዳረኛ ነው፡፡ አገሩ እና ህዝቡ የገናናው እሳቦት ብቻ ሳይሆን ÷ የ non state actor ነው አለ፡፡ አገር እና ባለ አገር የሁሉም ውክልናዎች Space politics ነው ብሎ በረታ፡፡ ኢትዮጵያንም ከአገራዊ ብሔርተኞች እና ከንዑስ ብሔርተኞች አታሞ ሊያድን እና ከ linear notion አፋታ፡፡ እንጀራ መታረቂያችን ፤ ነገን መስሪያ ትዕምርት ፤ ምሳሌያችን ነው አለ፡፡ Centripetalism ሊሠራበት ቀደመ፡፡
ይሄ ትውልድ ዘረኛ ፤ ጦረኛ ፤ ብሔርተኛ ኾኖ አዳም እወዳለው ሲል፡፡ አዳም የወል ሲኾን እደነግጣለሁ፡፡ እኛ የእሱን አዲስ ተረክ ፤ የእሱን አይነ ኅሊና እንደተጋራን አላየሁም እና ÷
2. እንጀራ ÷ የጋራ ትዝታችን የተሰራበት ፤ የተጋገረበት አውድ ነው፡፡ የጋራ ትዝታ ያለው አገር እና ትውልድ ደግሞ "ሰው አለ ተብሎ ይፈታል ወይ ትዳር" አይከናወንበትም ነበር፡፡
ፅድቁን ፤ እንጀራውን ጠብቆ ያሳይ ነበር፡፡ አዳም እንጀራን ለትናንት ትዝታ ብቻ ሳይሆን ፤ ለነገ ትዝታም ማዘመኛ ዘይቤው ነው፡፡ ይህ ዘመን እና ትውልድ የራሱ እውቀትን የማያውቅ ÷ የአለሙን ጥበብ ያልተረዳ ነው፡፡ በራሱ ላይ ያመፅ ፤ ምን መሆን እንደሚፈልግ በአግባቡ ያልተረዳ ነው፡፡Lack of epistemic autonomy አጋጥሞታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከእንጀራ ተምኔት ይልቅ ፤ በሌላኛው ዓለም አለባበስ ÷ ምሳሌ እና ህልም ሰክሯል፡፡ የበላበትን ወጪት ሰባሪ ኹናል፡፡ (Political destitution and cognitive oppression) እያሰቃየው ነው፡፡
እንደ አዳም ረታ እንጀራውን ተውሶ እውቀቱን አልፈከረም፡፡ ከአዳም የእንጀራ ፍልስፍና ውስጥ የእንሰት ÷ የገዳ ÷ የሽምግልና ÷ የእቁብ ÷ የቅዳሴ/የአዛን/ ትዕምርቶችን አላስፋፋም፡፡ ወደ Dead end እየተጋዘ ነው፡፡
እንደምን ታዲያ የአዳም ረታ ደቂቅ ነኝ ሊል ደፈረ ትውልዱ እና ዘመኑ?
3. ህፅናዊነትን እና አዳም አገራችን እና ሰው የነጠላ አስተሳሰብ ÷ የባለ አንድ መልክ የዝማሬ ፤ የቋንቋ ውጤት እንዳልሆኑ ያምናሉ፡፡ አገራችን እና ዓለማችን በተለያዩ ፅንሠ አሳቦች ÷ የዓለም አተያይ አረዳዶች እንደፀኑ ያምናሉ፡፡ በአባቶቻችን እና እናቶቻችን የቀደመ እውቀት አነጋገር "አገራችን የአንድምታ ውጤት ነች ይላሉ፡፡" Fusions of horizons ይሉታል፡፡
ህፅናዊነት Complex of web connection ነው፡፡ አዳምም አንድንም ታሪክ ብቻውን አድርጎ አያውቅም፡፡ ዘመድ ፤ አዝማድ ፈልጎለታል፡፡ መነሻውን ÷ መጋዣውን እና ማረፊያውን ይሰፋዋል፡፡ ከነጠላ ትርጉም ይልቅ ፤ የምስጥር ትርጉም ውስጥ ያጠምቀዋል፡፡ በሚሼል ፉኮ አነጋገር Deform የኾነውን ተረክ ወደ መዳኛው ይስበዋል፡፡ ያም ህፅናዊነት ነው፡፡ አይነተ ብዙኃነት የኾነ እውቀት ፤ ጥበብ እና መላ እንደኾነ ያሳየናል፡፡ (Emancipator common good)
ይሄ ዘመን ታዲያ እንዴት አዳም በሁለንተናዊነት ውስጥ እንኑር ሲል እንዴት ብቻ ለብቻ ነው የምንቆም እያለ እንዴት ለአዳም ረታ እልልታ አደረገ?
4. አዳም ለቃል ትልቅ ዋጋ አለው፡፡ አባቶቻችን ፤ እናቶቻችን ልሳን ይሉታል፡፡ የአዳም ረታ ልሳን ÷ ምናብ ጥልቅ ፍከራ አለው፡፡ ትርክትህን ÷ ትልምህን ÷ ኑረት ÷ ፍካሬ ÷ ፍልሱፍህን ያተመበት ነው፡፡ አዳም በጣም ቀላል ፤ ገላጭ በኾነ መንገዶች ቃላቱን ይሰራቸዋል፡፡ የቃል ፈጣሪ ነው፡፡ የእኔ እና የአንተን የተበላሸ አለም ለመስራት ቃል ይወልዳል፡፡ ይተቻል ፤ ይወያያል ፤ ይደማመጣል አዳም፡፡ (Trans critique and dialogical critical dialogue)
ዘመኑ እንደምታውቀው ነው፡፡
የስድብ ፤ የጥላቻ ፤ የልዩነት ፤ ነገን የመስበር ቃላቶች የሚመረቱበት ነው፡፡ መወያየት መልካም የተባለውን ወርቅ አሳብ ቀብሮታል፡፡ ቀልብ ÷ ልብ እና ኅሊና የፈረሱበት ናቸው፡፡ (one directional narrative)
እና ይህ ትውልድ አዳምን እወዳለሁ ሲል ንፍጡን እየቀባው ይሆን?
5. ፈላስፋው ዘርአያዕቆብ እንዲህ ይላል "we can’t reach truth through the doctrine of men, for all men are liars"
አገሩ ÷ የወንድ ውልድ ነው፡፡ መንገዱ ፤ ብገሩ ፤ ተስፋችን ፤ ምሬታችን በወንድ አዕምሮ የተበለተ ነው፡፡ የማኅበረሰባችን ማህፀን የኾኑት ሴቶችን እርባና ፤ ውለታን ይረሳል፡፡ ያጣጥላል በመዋቅራዊ አወቃቀሩ፡፡
አዳም ውሸታም ከተባሉት ፤ አጭቤዎች ከተሰኙት ወንዶች ይልቅ በሴቶች አማካኝነት ፍካሬውን ፤ ቁስሉን ፤ ሙክረቱን (ኤክስፐርመንቱን) ያጦዛል፡፡ ማኅሌት ÷ እቴሜቴ ሎሚ ሽታ ÷ እንጀራ የሴትነት ተረክ ናቸው፡፡ ማሠቢያ ፤ ማውጠንጠኛዎቹ ናቸው፡፡
የወንዶቹ ስርአት አገሩን እና ትውልዱን ምን እንዳሳጣው ካወቅን፡፡ እስከ መቼ የሴቶቻችንን የገደል እና የአርነት መንገድን ሳንጠቀም እንቆይ የሚል ይመስለኛል አዳም ረታ፡፡ በሴት ዓይነ ኅሊና ÷ በሴት ዝክረ ልቡና ÷ በሴት ማኅፀን አዲስ ኢትዮጵያ ሊወልድ የሚውተረተር ይመስለኛል፡፡
አንተ ወንድ ትውልድ ሆይ ፤ እስከ መቼ ሴት ሳትሆን ትቀራለህ?
ሴት አትሆንም ወይ ወንድነትህን ይዘህ እንደሚለን አምናለሁ፡፡
Rejection of monism, point’s horizon to the silence and blind spot of tradition
6. ሊቀሊቃውንቱ ማዕምር መናዕሰናይ ስለ ኢትዮጵያ እንዲህ ይላሉ "The incompleteness of ethiopia doesn’t lead to dead end, on the contrary it drives Ethiopian reality it is."
አዳም ረታም ኢትዮጵያ ጉድፍ እንዳለባት ያምናል፡፡ ጉድፍ ስላለባት ግን ሊተዋት አልወደደም፡፡ ቀጣዩን ምዕራፍ አብረን እናብጀው ብሎ ለሁላችን ነው ጥሪ የሚያደርገው፡፡ ይህንን ለመስራትም ምናብ እና ሁለንተናዊ ውክልና እና እውቀትን መሳሪያዎቹ ያደረገው፡፡ (Political imagination for the future)
በታሪኮቹ ውስጥ ማለቅ የለም የሚለን ÷ አንባቢን እንዲያስብ ፤ እንዲያሰላስል ፤ ከትርክቶቹ ጋር እንዲነጋገር ሲያደርገው የነገን ምዕራፍ የእኔ ብቻ ሳይሆን ፤ የአንተም ነው በማለት ነው፡፡
የዛሬይቱ እና የነገይቱን ኢትዮጵያ ሊሰራ ሁላችንም አለንበትን በ inter textually ህብረ ቃል ያጣብቀናል ፤ እንዳንለያይ አድርጎ፡፡ ይሄ ነው ኹላችንንም አርነት የሚያወጣን ይላል አዳም በቴክኒኩ፡፡
የኔ ትውልድ ግን ስታፈርስ ነው ያየውህ፤ የኔ ዘመን ግን ስትክድ ነው ያስተዋልኩህ፡፡
…
የኔ ዘመን እና የኔ ትውልድ ሆይ አዳምን ከወደድክ ፤ ደቂቀ አዳም ነኝ ካልህ ፤
ምናቡን ተዋስ ÷ ሁለንተናዊ ትርክቱን አፅናለት ÷ የጋራ የወል ትዝታ እና ፊውቸርህን አስተካክል፡፡
እንከንን ወደ ወርቅነት ቀይር፡፡
ሰው እንኹን፡፡ (Tran’s individual panoptic gaze)
Credit - Habtu Girma