BBE-News

BBE-News ቻናላችን፦ ትኩስ ዜናዎችን፣ ስፖርትና በርካታ መረጃዎችን በ?

瑜伽服飾🧘‍♀️超!級!顯!瘦!彈性瑜珈褲誰說一定要運動或瑜伽才能穿拿來當內裡穿搭也是有型今天正夯的鯊魚褲就是這麼甜甜價又實穿🥰準備好現貨隨時出貨✨ #現貨 #瑜伽褲  #緊身褲 #內搭褲 #鯊魚褲
21/09/2022

瑜伽服飾🧘‍♀️
超!級!顯!瘦!
彈性瑜珈褲
誰說一定要運動或瑜伽才能穿
拿來當內裡穿搭也是有型
今天正夯的鯊魚褲
就是這麼甜甜價又實穿🥰
準備好現貨隨時出貨✨
#現貨
#瑜伽褲

#緊身褲
#內搭褲
#鯊魚褲

በአማራ ክልል 2 ሺህ 705 ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገላቸው፡፡ በልዩ ልዩ ወንጀሎች እስራት ተፈርዶባቸው በአማራ ክልል በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ለሚገኙና የይቅርታ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ታራሚዎች ...
29/04/2021

በአማራ ክልል 2 ሺህ 705 ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገላቸው፡፡

በልዩ ልዩ ወንጀሎች እስራት ተፈርዶባቸው በአማራ ክልል በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ለሚገኙና የይቅርታ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ታራሚዎች ይቅርታ እንዲደረግ የክልሉ ይቅርታ ቦርድ ወስኗል፡፡

የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እንዳስታወቀው 56 ሴት እና 2 ሺህ 649 በድምሩ 2 ሺህ 705 ታራሚዎች ከዛሬ ጀምሮ በይቅርታ መለቀቃቸውን የጠቅላይ አቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ አለምሸት ምሕረቴ በተለይ ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡

አቶ አለምሸት እንዳሉት በተለያዩ ወንጀሎች እስራት ተፈርዶባቸው አንድ ሦስተኛ የእስራት ጊዜያቸውን የጨረሱ እና በማረሚያ ቤት የሥነ ምግባር ለውጥ ማሳየታቸው የተረጋገጠላቸው ታራሚዎች ናቸው በይቅርታ እንዲለቀቁ የተወሰነው፡፡ ሕጻን ይዘው የታሰሩ ሴቶችና ነብሰ ጡር እስረኞች ከሆኑ ደግሞ ከተፈረደባቸው የእስራት ጊዜ አንድ አምስተኛውን ካጠናቀቁ የይቅርታው ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

የዕድሜ ልክ እስራት ከተፈረደባቸው መካከል 60 ዓመት የሞላቸው ወንዶች 12 ዓመታት በእስራት ከቆዩ፣ ሴቶች ከሆኑ ደግሞ 55 ዓመት ሆኗቸው 10 ዓመታት ከታሠሩ የይቅርታው ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ይሁን እንጂ ይቅርታው ከ15 ዓመት በታች የሆነች ልጃገረድ አስገድዶ የደፈረ፣ ፍጻሜ ባገኘ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ፍጻሜ ባገኘ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እንዲሁም በሙስና ወንጀል 10 ዓመትና ከዚያ በላይ እስራት የተፈረደባቸውን ታራሚዎች አያካትትም ነው ያሉት፡፡ ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች ከዛሬ ጀምሮ መውጣት መጀመራቸውንም የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊው አስታውቀዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

👇


👉 https://t.me/bbe_newss አግኙን

👇
👉 https://www.facebook.com/107793534680780 ተከታተሉን።

👉 .

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ* የ19 ሰዎች ህይወት አልፏል* 945 ሰዎች በጽኑ ታመዋል * ተጨማሪ  1 ሺህ 130 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል 👇    👉 https://t.me/bb...
29/04/2021

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ

* የ19 ሰዎች ህይወት አልፏል
* 945 ሰዎች በጽኑ ታመዋል
* ተጨማሪ 1 ሺህ 130 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል

👇


👉 https://t.me/bbe_newss አግኙን

👇
👉 https://www.facebook.com/107793534680780 ተከታተሉን።

👉

የባንኮች መነሻ ካፒታል ከ500 ሚሊየን ብር ወደ 5 ቢሊየን ብር ሊያድግ ነው ተባለ፡፡በብሄራዊ ባንክ የባንክ ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር ፍሬዘር አያኔው ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ባንኮች ለምስረ...
14/04/2021

የባንኮች መነሻ ካፒታል ከ500 ሚሊየን ብር ወደ 5 ቢሊየን ብር ሊያድግ ነው ተባለ፡፡

በብሄራዊ ባንክ የባንክ ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር ፍሬዘር አያኔው ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ባንኮች ለምስረታ የሚያስፈልጋቸው ካፒታል ወደ 5 ቢሊየን እንዲያሳድጉ የሚጠይቅ መመሪያ ተዘጋጅቶ ከዛሬ መጋቢት 6 ጀምሮ ለባንኮች እየተላከ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ባንኮች የካፒታል አቅማቸው የተጠናከረ እና የዳበረ እንዲሁም ተወደዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል የተሻሻለው ይህ መመሪያ ለነባር ባንኮች እስከ 5 ዓመት እና ለአዳዲስ ባንኮች እስከ 7 ዓመት ጊዜ መሰጠቱን ፍሬዘር ተናግረዋል፡፡Addis Maleda @ yenetub

👇


👉 https://t.me/bbe_newss አግኙን

👇
👉 https://www.facebook.com/107793534680780 ተከታተሉን።

👉

በህዋሓት ቡድን  ግፊት ወደ በርሃ የወሰዳቸው ወጣቶች ወደ ኑሯቸው እየተመለሱ ነው,።         - መከላከያ ሠራዊት በህዋሓት ቡድን  ግፊት ወደ በርሃ የወሰዳቸው ወጣቶች ወደ ኑሯቸው እየተ...
14/04/2021

በህዋሓት ቡድን ግፊት ወደ በርሃ የወሰዳቸው ወጣቶች ወደ ኑሯቸው እየተመለሱ ነው,።
- መከላከያ ሠራዊት

በህዋሓት ቡድን ግፊት ወደ በርሃ የወሰዳቸው ወጣቶች ወደ ኑሯቸው እየተመለሱ እንደሆነ የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ ገለጹ፡፡

የደቡብ ዕዝ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ከአዲቀይህና አካባቢው ነዋሪ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጄር ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ ፣ ጁንታው በሀሰት ፕሮፓጋንዳ እያታለላቸው ወደ በረሃ የወሰዳቸው ወጣቶች የራሳችንን ኑሮ መኖር ይሻለናል በማለት ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነው ብለዋል።

በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ወደ በረሃ የገቡ ቀሪ ልጆቹን የአዲቀይህ ህዝብ ወደየቤታቸው እንዲመለሱ ማድረግ አለበት ሲሉም በአፅንኦት ተናግረዋል።

"ከየትኛውም ወገን ይሁን ሰው መሞት የለበትም" ያሉት ጄኔራል መኮንኑ ጁንታው እያታለለም ሆነ እያስገደደ የወሰዳቸው የታጠቀም ይሁን ያልታጠቀ ሃይል በሰላም ትጥቁን እንዲያስረክብና ኑሮውን እንዲቀጥል አሳስበዋል።

ብ/ጄ ናስር አባዲጋ በበኩላቸው ፣ ጁንታው የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ሲፈፅም ለትግራይ ህዝብ የነገረው መረጃ ሁሉ ውሸትና ጦርነቱንም እራሱ ሠራዊቱ ላይ ከህደት በመፈፀም የጀመረው መሆኑን ለተሰብሳቢው አስረድተዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲቀይህ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችም "መከላከያ የየትኛውም ድርጅትና ክልል አለመሆኑን ፣ ለመላው ኢትዮጵያ የቆመ ሰራዊት መሆኑን ጥርጥር የለንም" በማለት ገልፀዋል።

"እኛ ከመከላከያ ጎን በሆናችን በጁንታው የብልፅግና ደጋፊ እየተባልን ነው" ያሉት ተሳታፊዎች "መከላከያ ከእኛ ጋር አብሮ ከሰራ አካባቢያችንን መጠበቅ የታጠቀውን ሃይልም መያዝ አያቅተንም" ሲሉ ተናግረዋል።
ምንጭ፡ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት @ ደሬቴድ

👇


👉 https://t.me/bbe_newss አግኙን

👇
👉 https://www.facebook.com/107793534680780 ተከታተሉን።

👉

"... ከእነሱ ጋር ጦርነት አንፈልግም ፤ ነገር ግን ዝግጁ አይደለንም ማለት አይደለም"              - ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ትለንት በሰጡት መግለጫ ፥ ኢትዮጵያ...
14/04/2021

"... ከእነሱ ጋር ጦርነት አንፈልግም ፤ ነገር ግን ዝግጁ አይደለንም ማለት አይደለም"
- ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ

ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ትለንት በሰጡት መግለጫ ፥ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ጦርነት እንደማታደርግ ፥ ጦርነት ማድረጉ ምንም እነደማያደርግ ተናግረዋል።

ሌ/ጄነራሉ አሁን ሱዳኖች ያያዙትን መሬት በንግግር መጨረስ ይቻላል ፥ እምነታችንም እሱ ነው ብለዋል።

ስንት ጊዜ ነው በመሬት ችግር ዘራፍ ብለን ተዋግተን ወጣቶችን የምናስጨርሰው ? ብለው የጠየቁት ሌ/ጄነራሉ ፥ የመሬቱን ጉዳይ በቀላሉ ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ መፍታት ይቻላል ፤ ግፋ ቢል በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት መፍታት ይቻላል ሲሉ ተደምጠዋል።

በሱዳን እና በኢትዮጵያ ወንድማማቾች መካከል የገባ ሶስተኛ ወገን አለ ፤ ከሱዳን ወንድሞቻችን ጋር በጋራ ሆነን ይሄን ሶስተኛ ወገን ለማውጣት ጥረት ይደረጋል ሲሉ ተናግረዋል።

ሌ/ጄነራል ባጫ ፥ "ከእነሱ ጋር ጦርነት አንፈልግም ነገር ግን ዝግጅ አይደለንም ማለት አይደለም፤ ኢትዮጵያን ለመከላከል እኛ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ምን ጊዜም ዝግጁ ነን" ሲሉ ገልፀዋል

👇


👉 https://t.me/bbe_newss አግኙን

👇
👉 https://www.facebook.com/107793534680780 ተከታተሉን።

👉

14/04/2021

የማህበር ቤት ምዝገባ ለተጨማሪ አስር ቀናት መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ የሚታየውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍ በተለያዩ የቤት ልማት ፕሮግራሞች ቤቶችን በመገንባት ለተጠቃሚዎች ያስተላለፈ እና ተጨማሪ ቤቶችንም በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

የነዋሪዎችን የቤት ፍላጐት ፍላጎትም ለማርካት ሌሎች አማራጮችን መተግበር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በ2005 ዓ.ም የ20/80 እና የ40/60 ከተመዘገቡት ቤት ፈላጊዎች አቅም እና ፍላጎት ያላቸው በጋራ ሕንፃ መኖሪያ ቤት የህብረት ሥራ ማህበር ተደራጅተው ገንዘባቸውን፣ እውቀታቸውን ፣ ጉልበታቸውን እና ጊዜያቸውን በማቀናጀት የቤት ችግሮቻቸውን በጋራ ጥረት ሊፈቱ የሚችሉበትን መንገድ በማመቻቸት ተጠቃሚ ለማድረግ የፍላጎት ምዝገባ መጀመሩ ይታወቃል፡፡

ምዝገባውም ከመጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ለተከታታይ 15 ቀናት ሲካሄድ የቆየ ሲሆን በዚህም ከ8 ሺህ 500 በላይ የማህበር ቤት ፈላጊዎች ተመዝግበዋል፡፡

የምዝገባ ጊዜው ሚያዝያ 5 ቀን 2013 ዓ.ም የተጠናቀቀ ቢሆንም ከተጠቃሚው ወደ ቢሮው በሚመጡ ጥያቄዎች በመነሳት ምዝገባው ለተጨማሪ 10 ቀናት መራዘሙን ቢሮው አስታውቋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ለመመዝገብ እየፈለጉ በሲስተም መጨናነቅ ምክንያት ላልተመዘገቡ ፤ ከመረጃው መዳረስ አንጻር ተጠቃሚው በቂ ግንዛቤ ባለመያዙ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያት ያልሰሙ የአማራጭ ቤት ልማት ፕሮግራሙን ፈላጊዎች በመኖራቸው ተጨማሪ እድል ለመስጠት ሲባል የምዝገባ ጊዜውን ማራዘም ቢሮው ገልጿል ፡፡

በመሆኑም መመዝገብ እየፈለጉ በተለያየ ምክንያት ቀኑ ያለፋቸው ተጠቃሚዎች የምዝገባ ጊዜው ከሚያዚያ 6 እስከ ሚያዚያ 15/ 2013 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን አውቀው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ተመዝጋቢዎች ወደ ቢሮ መምጣት ሳያስፈልጋቸው በቀጥታ /Online/ በቢሮው አድራሻ WWW.aahdab.gov.et አማካኝነት ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ቢሮው ማሳወቁን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በምዝገባ ወቅት ችግር የገጠማቸውን የማህበር ቤት ፈላጊዎች ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኃላ ከሚያዚያ 18-20/2013ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ሶስት ቀናት በቢሮው ቀርበው ቅሬታችውን ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን በማህበር ቤት ፕሮግራሙ መካተት አቅሙ እና ፍላጎቱ ለሌላችው ደግሞ ነባሩ የ20/80 እና የ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ግንባታ ስራ በተለመደው አሰራር የሚቀጥል መሆኑን ቢሮው አመልክቷል::

👇


👉 https://t.me/bbe_newss አግኙን

👇
👉 https://www.facebook.com/107793534680780 ተከታተሉን።

👉

በጸጥታ ችግር ምክንያት በ4 ሺህ 126 የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ እንዳልሆነ ተገለጸ።በጸጥታ ችግር ምክንያት በ4 ሺህ 126 የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደባ...
14/04/2021

በጸጥታ ችግር ምክንያት በ4 ሺህ 126 የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ እንዳልሆነ ተገለጸ።

በጸጥታ ችግር ምክንያት በ4 ሺህ 126 የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደባቸው እንዳልሆነ የኢትዮጽያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፖርቲዎች ጋር የመራጮች ምዝገባ ሂደት ያለበት ሆኔታ እና ያጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ ውይይት እየተደረገ ነው።

በመራጮች ምዝገባ ችግሮች አንዳጋጠሙ የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ገልጸዋል።

የትራንስፖርት ችግርና ሌሎች ተጓዳኝ ችግሮችም በመራጮች ምዝገባ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደራቸውንም ተገልጿል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።ደሬቴድ

👇


👉 https://t.me/bbe_newss አግኙን

👇
👉 https://www.facebook.com/107793534680780 ተከታተሉን።

👉

14/04/2021

በአማራ ክልል የተፈናቃዮች ቁጥር እያሻቀበ መምጣቱ ተነገረ፡፡

የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮምሽን እንዳለው፣ ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በተለይም ከኦሮሚያ እና ከቤኒሻንጉል ክልል ተፈናቅለው ወደ ክልሉ የሚመጡ ተፈናቃዮች ቁጥር በየጊዜው በእጅጉ እየጨመረ ነው::

የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮምሽን ኮምሽነር አቶ ዘላለም ልጅአለም እንዳስታወቁት፣ በ አሁኑ ሰዓት በክልሉ 4 መቶ 95 ሺህ የሚሆኑ ተፈናቃዮች ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ተፈናቃዮች በአብዛኛው ኦሮሚያና ቤኒሻንጉልን ጨምሮ ከትግራይ እና ከደቡብ ክልል በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

አብዛኛው ተፈናቃይ ማህረሰቡ ውስጥ አብሮ ይገኛል ያሉን ኮምሽነር ዘላለም፣ በተጨማሪም ቻግኒ፤ሰሜን ወሎ፤ ደቡብ ወሎ እና ጎንደር በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡

እነዚህን ተፈናቃዮች የሚደግፍ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም፣ በማንነታቸው ምክንያት ከቀያቸው ቤት ንብረታቸውን ጥለው የመጡ ዜጎች ወደ ቀደመ ቀያቸው መመለስ እንዳለባቸው ክልሉ እንደሚያምን ነው የተናገሩት፡፡

በተለይም ወደ ቀደመ ቀያቸው እንዲመለሱ የማድረጉ ስራ መንግስትና በተለይም የመጡበት ክልል ከፍተኛ ሃላፊነት ሊወስድና መልክ ማሲያዝ እንዳለበትም አስታውቀዋል፡፡ Ethio FM

👇


👉 https://t.me/bbe_newss አግኙን

👇
👉 https://www.facebook.com/107793534680780 ተከታተሉን።

👉

14/04/2021

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when BBE-News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share