03/02/2023
#ይቅርታ #የተደረገልህን #ጊዜ #አስታውስ!
ከሰው ልጅ አስገራሚ ባህሪይ አንዱ ለእርሱ እንዲደረግለት ሲፈልግ መድፈሩ፣ የእርሱ ተራ ሲደርስ ደግሞ "ማፈሩ" ነው። መንገድ ተዘግቶብን ስንጨነቅ ያኛው ሹፌር ቆሞ እንዲያሳልፈን እንጠብቃለን። መንገድ ለቅቀን ማሳለፍ ያለብን እኛ ስንሆን እንዳላየ እንሆናለን። መለስ በልና ከልጅነትህ ጀምሮ የነበረህን ሕይወት ማስታወስ የምትችለውን ያህል ለማስታወስ ሞክር። ብዙ ጊዜ ሁለተኛ እድል፣ አንዳንዴም ከሶስተኛ እድል በላይ የተሰጠህ ሰው ነህ። ላጠፋሃቸው ጥፋቶች ሁሉ የሚገባህን አላገኘህም። ከዚህ በፊት "የእግዚአብሔርን ተው" የእርሱማ ቁጥር የለም። ቢያንስ አንድ ሰው አንድን ስህተትህን እያየ እንዳላየ፣ እያወቀ እንዳላወቀ አልፎሃል። ዛሬ ዳግሞ የአንተ ተራ ነው።