GAMBY PLC

Call Website Contact the business

GAMBY PLC Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from GAMBY PLC, Wholesale & Supply Store, Near Textile – Bahir Dar, Gambella.

GAMBY is involved in health care provision, in retailing pharmaceuticals, in wholesale of pharmaceuticals, medical supplies and equipment and in health, medical and business education.

13/10/2026

The tourist expressed her appreciation for the service she observed at GAMBY Teaching General Hospital.

08/10/2026

Bahirdar, Ethiopia

የክረምቱ መውጣት እና የወባ በሽታ ስጋት፦ መረጃ ለጤናዎ! ​የክረምቱ ወራት አብቅቶ ፀሐያማውና ደረቁ የበጋ ወቅት ሲተካ፣ አብረው ከሚከሰቱ ዋና ዋና የጤና ስጋቶች አንዱ የወባ (Malaria)...
05/10/2026

የክረምቱ መውጣት እና የወባ በሽታ ስጋት፦ መረጃ ለጤናዎ!
​የክረምቱ ወራት አብቅቶ ፀሐያማውና ደረቁ የበጋ ወቅት ሲተካ፣ አብረው ከሚከሰቱ ዋና ዋና የጤና ስጋቶች አንዱ የወባ (Malaria) በሽታ ነው።
​ የወባ በሽታ በክረምት ማብቂያ ላይ ለምን ይበዛል?
​በክረምቱ ወቅት የጣለው ዝናብ ቦታ ቦታ ላይ ተቋጥሮ የሚቀር በመሆኑ፣ ለወባ አስተላላፊ ትንኞች መራቢያና ማፊያ በጣም ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል። ወቅቱ ሲለወጥና ሙቀት ሲጨምር ደግሞ የትንኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚጨምር የበሽታው ስርጭት ይፋጠናል።
በሽታውን ለመከላከል ማድረግ የሚገቡን ዋና ዋና ጥንቃቄዎች ​የቆሙ ውኃዎችን ማቃናት/ማድረቅ፦ በግቢያችንና በአካባቢያችን የሚገኙ የቆሙ ውኃዎችን በማስወገድ የትንኝ መራቢያ ቦታዎችን ማጥፋት።
​አልጋ ላይ አውታር (አልጋ መረብ) መጠቀም፦ በፀረ-ትንኝ ኬሚካል የተነከረ የወባ መረብ ዘወትር ማ ማ ማደር።
​የሰውነት ክፍሎችን የሚሸፍኑ አልባሳትን መልበስ፦ በተለይ ምሽትና ማለዳ አካባቢ ረጅም እጅ ያላቸውን አልባሳት መጠቀም።
​የፀረ-ትንኝ ቅባቶችን መጠቀም፦ በቆዳ ላይ የሚቀቡ የትንኝ ማባረሪያዎችን (Insect repellents) መጠቀም።
​የቤትን በሮችና መስኮቶች ቀድሞ መዝጋት፦ ትንኞች ወደ ቤት የሚገቡበትን መንገድ ምሽት ላይ መዝጋት።
​ ከታመሙ ወይም ምልክቶች ካዩ ወዴት መሄድ አለብዎት?
​የወባ በሽታ እንደ ከፍተኛ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ራስ ምታት፣ የጡንቻና የመገጣጠሚያ ህመም፣ ማስመለስ እና ድካም ያሉ ምልክቶች አሉት። እነዚህን ምልክቶች ሲያዩ ወደ ህክምና ተቋም በፍጥነት መሄድ አስፈላጊ ነው።
​ጋምቢ ቲችንግ አጠቃላይ ሆስፒታል ለዚህ አስተማማኝ መፍትሔ ይዞልዎታል!
​✨ በጋምቢ ሆስፒታል ለምን ይታከማሉ?
​በጣም ዘመናዊና የተሟላ ላቦራቶሪ፦ የወባ ጥገኛ ተህዋስያንን በአጭር ጊዜ ውስጥ በጥራትና በትክክል ለመለየት የሚያስችሉ ዘመናዊ የላቦራቶሪ መሣሪያዎች አሉት።
​ፈጣንና ትክክለኛ ምርመራ፦ ትክክለኛ የደም ምርመራ ውጤት በማግኘት ተገቢውን ሕክምና ሳይዘገዩ እንዲያገኙ ይረዳዎታል።
​ባለሙያ የህክምና ቡድን፦ በክህሎታቸው የዳበሩ የህክምና ባለሙያዎችና ስፔሻሊስቶች ተገቢውን ክትትልና እንክብካቤ ያደርጉልዎታል።
​ወባን ቀድሞ በመከላከልና ወቅታዊ ምርመራ በማድረግ ጤናዎንና የቤተሰብዎን ደህንነት ይጠብቁ!
​📍 ጋምቢ ቲችንግ አጠቃላይ ሆስፒታል
📞 ለበለጠ መረጃና ቀጠሮ፦ +251918143195
💬 ጤንነትዎን መጠበቅ ቅድሚያ ተግባራችን ነው!
​ #ጋምቢሆስፒታል #የወባበሽታ #የጤናመረጃ #ጤናዎበእጅዎ

05/10/2026

ምዝገባ ላይ ነን 🎓

30/09/2026

የሰመመን ሕክምና በጋምቢ ሆስፒታል

ለመላው የክርስትና እምነት ተከተዮች!​እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!​በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የምሕረት እንዲሆንልዎ ጋምቢ ቲችንግ ጠቅላላ ሆስፒታል ይመኛል።​✨ መልካም...
26/09/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከተዮች!
​እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!
​በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የምሕረት እንዲሆንልዎ ጋምቢ ቲችንግ ጠቅላላ ሆስፒታል ይመኛል።
​✨ መልካም የደመራና የመስቀል በዓል! ✨
​📍 አድራሻ፡ ባሕርዳር
📞 ስልክ ቁጥር፡ 0918143195 / 058-2-264303

22/09/2026
22/09/2026

ዘመናዊው ላቦራቶሪ ክፍል እና ፓቶሎጅ

(ዶ/ር በሃይሉ ይዘንጋው የሕፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት )የጨቅላ ህፃናት ቢጫ መሆን በሽታ (neonatal jaundice) ✅የጨቅላ ህፃን ቢጫ መሆን የሚከሰተው በህፃኑ ደም ውስጥ ቢሊሩቢን(Bi...
17/09/2026

(ዶ/ር በሃይሉ ይዘንጋው የሕፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት )
የጨቅላ ህፃናት ቢጫ መሆን በሽታ (neonatal jaundice)
✅የጨቅላ ህፃን ቢጫ መሆን የሚከሰተው በህፃኑ ደም ውስጥ ቢሊሩቢን(Bilirubin) የሚባል ኬሚካል ከመጠን በላይ ሲጠራቀም ነው።
✅ቢሊሩቢን(bilirubin) ጤነኛ ሰዉ ላይ ቀይ የደም ህዋሳት ሲሰባበሩ የሚፈጠር ሲሆን ፤ በጉበት እና ኩላሊት በመታገዝ ከሰዉነታችን በሰገራ እና በሽንት ዉስጥ ይወገዳል።
✅ይህ ክስተት ልጆች በተወለዱ በአንድ ሳምንት ዉስጥ 80% የሚሆኑ ያለቀናቸዉ የተወለዱ ልጆች ላይ የሚታይ ሲሆን ፤ በቀናቸዉ ከተወለዱት ውስጥ 60% የሚሆኑት ላይ የመከሰት እድል አለዉ።
✅የሚከሰትበት ዋና ዋና ምክንያቶች ውስጥ:-
-የእናትና የጨቅላው ህፃን የደም አይነት ልዩነት ካለ በተለይ RH incompatibility(ሾተላይ ካለ) ወይም ABO incompatibility (የእናት ደም አይነት O ከሆነ አና የህፃኑ የደም አይነት ከ O ውጭ ከሆነ)
- የጨቅላ ህፃናት ኢንፌክሽን ካለ(neonatal sepsis)
-በጨቅላ ህፃናት ጭንቅላት ላይ የደም መጠራቀም(subgaleal hemorrhage ,cephalhematoma)
- በቂ የእናት ጡት በደንብ አለመጥባት
-ሲወለዱ ከሚጠበቀዉ በታች የሆነ ክብደት ሲኖራቸው ወይም ያለቀናቸው ሲወለዱ
-በዘር የሚተላለፉ በጉበት ዉስጥ ያሉ “ቢሉሪቢንን” ለማስወገድ የሚረዱ ኬሚካሎች እጥረት
- የአንዳንድ የጡት ወተት ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች
- በጉበት እና የሀሞት ከረጢት ላይ ያሉ የአፈጣጠር ችግሮች
✅ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
ይህ ችግር ያጋጠማቸው ጨቅላ ህፃናት ከሚታይባቸው ምልክቶች ዋና ዋናዎቹ የሚባሉት :-
- የአይናቸው ነጩ ክፍል ቢጫ መሆን
- የህፃኑ ቆዳ ቢጫ መሆን
-ጡት መጥባት መቀነስ
- ህፃኑ ሲያለቅስ በጣም የመረረ እና ድምፁ በጣም ከተለወጠ
- መነጫነጭና በደንብ አለመተኛት
- የህመሙ መጠን ሲጠነክር እና “ቢሉሪቢን” ወደ አዕምሮ በመሄድ መጠራቀም ሲጀምር እንደ ሰዉነትን ማንቀጥቀጥ ፣ መዝለፍለፍ ፣ የንቃት መቀነስ እስከ እራስን መሳት ሊያደርስ ይችላል።
-የሽንት ቀለም መጥቆር
-የሰገራ ቀለም መንጣት
✳️ህክምናው ምንድነው?
✅ህክምናው እንደ በሽታው ምክንያት እና እንደ ደረጃዎቹ የሚሰጥ ሲሆን።
✅ቀላል ለሚባሉት ፀሀይ ማሞቅ እና በቂ የእናት ጠት ማጥባት በቂ ሊሆን ይችላል።
✅የጨረር ህክምና(Phototherapy) :-ይህ ህፃናትን የተለያየ ቀለም እና ሀይል ባለቸዉ የብርሀን ጨረር ላይ በማድረግ በሰዉነታቸዉ ዉስጥ የተከማቸዉን “ቢሊሩቢን” በቀላሉ መወገድ ወደሚችል አይነት መቀየር ነዉ።

✅ነገር ግን የ ቢሊሩቢን(bilirubin) መጠኑ በጣም ከፍ ያለ ከሆነ ወይም ህፃኑ ጋር የጭንቅላትት መጎዳት ምልክት(bilirubin encephalopathy )ከታየ በቶሎ ደሙ ሙሉ በሙሉ መቀየር አለበት(exchange transfusion) ይታከማል ፡፡
✅ሌላዉ ይህንን ህመም ያመጣዉን ዋናውን መንስዔ ማከም ነው።
✳️የጨቅላ ህፃናት ቢጫ መሆን በሰአቱ ካልታከመ እስከ ሞት ሊያበቃ ይችላል።
✳️በረጅም ጊዜም የሚከሰተው መዘዝ መራመድ አለመቻል እና የአዕምሮ እድገት ውስንነት እስከ የመስማት ችሎታን ማጣት ሊያደርስ ይችላል።
መከላከያ መንገዶች
✳️እናቶች ከወለዱ እለት ጀምሮ በቂ ብርሃን ባለበት ቦታ ላይ የልጆቻቸውን አይን እና ሰውነት ቆዳ ቀለም መከታተል እና ቢጫ መሆን ካስተዋሉ ተሎ ወደ ህክምና መውሰድ
✳️ጨቅላ ህፃናት እንደተወለዱ በቂ የሆነ ወተት እንዲያገኙ ማድረግ የ”ቢሊሩቢንን” ከሰዉነት መወገድ ማፉጠን ይቻላል።


Address

Near Textile – Bahir Dar
Gambella
290

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GAMBY PLC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to GAMBY PLC:

Shortcuts

Share