04/05/2025
ለVAR በየአመቱ 1.5 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ።
በተለይ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ላይ የዳኞች አጋዥ ሆኖ የሚያገለግለው VAR ን ስናስብ ፡ ለአብዛኛዎቻችን የሚመስለን ፡ ዳኛው ሄዶ የተቀረፀውን ቪዲዮ አይቶ የሚመጣ ብቻ እንጂ ፡ VAR ን ለመጠቀም ከፍተኛ ወጭና ፡ ቴክኖሎጂ የሚያስፈልግ ነገር አይመስለንም ።.
ሆኖም VAR ን ( Video Assistant Referee ) በተግባር ላይ ለማዋል ፡ በሰውና በራሳቸው የሚቀርፁ ከ33 በላይ እስከ 4 K የምስል ጥራት ያላቸው ካሜራዎች ያስፈልጋሉ ።..
ከነዚህ መሀከልም የአንዱ ዋጋ ከ84 ሺህ ዶላር በላይ የሚያወጣው Sony HDC-F5500 ካሜራና ፡ በሰከንድ 120 ፍሬም የሚያነሳ ፡ አልትራ slow motion ካሜራዎች ይገኙበታል ።...
የሰው ሀይልን በተመለከተም ይህንን ምስል ተቀብለው የሚቆጣጠሩና ፡ ከዳኛው ጋር በራዲዮ የሚገኛኑ ሰወችንና ካሜራ ማኖችን ጨምሮ አንድን VAR ለማሰራት ፡ እስከ 15 ሰወች የሚያስፈልጉ ሲሆን ፡ በአጠቃላይ VAR የካሜራዎቹንና ሌሎች እቃዎችን ዋጋ ሳይጨምር. . በየአመቱ ከ1.5 ሚሊየን ዶላር በላይ ወይም ከ200 ሚሊየን ብር በላይ በየአመቱ ወጭ የሚጠይቅ ነገር ነው ።