Be patient .

Be patient . This page is about Islam and to show how is Islam in Ethiopia
ኣላማችን በአገራችን ውስጥ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ለኢትዮጲያ ሕዝብ ማሣወቅ ነው
አላህ ይርዳን

18/04/2026

ሱረቱል አንቢያ (87-90)
​87. የዓሣውንም ባለቤት (ዩኑስን) ተቆጥቶ በሄደ ጊዜ፤ (ከዓሣ ሆድ በማውጣት) በእርሱ ላይ ፈጽሞ የማንፈርድበት መሆናችንን በጠረጠረ ጊዜ፤ (አስታውስ)። በጨለማዎችም ውስጥ ሆኖ «ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ጥራት ይገባህ፤ እኔ በእርግጥ ከበዳዮች ነበርኩ» በማለት ተጣራ።
​88. ለእርሱም ጥሪውን መለስንለት፤ ከጭንቅም አዳንነው፤ እንደዚሁም አማኞችን እናድናለን።
​89. ዘካርያስንም «ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ፤ አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ» በማለት ጌታውን በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)።
​90. ለእርሱም ጥሪውን መለስንለት፤ ለእርሱም የሕያን ሰጠነው፤ ሚስቱንም (መካን የነበረችውን) አበጀንለት (እንድትወልድ አደረግን)። እነርሱ (ነቢያቱ) በበጎ ሥራዎች የሚቻኮሉ፣ ከጅለውና ፈርተውም የሚለምኑን ነበሩ፤ ለእኛም ትሑቶች ነበሩ።
​ይህ የቁርአን አንቀጽ በተለይ በችግርና በጭንቅ ጊዜ ወደ ፈጣሪ መመለስንና እርሱም ጸሎትን ሰሚ መሆኑን የሚያሳይ ጥልቅ መልዕክት አለው።

18/04/2026

«ጌታህም እንዲህ ሲል አዘዘ፦ እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፤ በወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ፤ ከሁለቱ አንዱ ወይም ሁለቱም በአንተ ዘንድ እርጅናን ቢደርሱ «ኡፍ» አትበላቸው፤ አትገላምጣቸውም፤ ለእነርሱም መልካምን ቃል ተናገራቸው።» (ሱረቱል ኢስራእ፡ 23)
​«ለእነርሱም ከእዝነትህ የመዋረድን ክንፍ ዝቅ አድርግላቸው፤ «ጌታዬ ሆይ! በሕፃንነቴ እንዳሳደጉኝ እዘንላቸው» በልም።» (ሱረቱል ኢስራእ፡ 24)
​ዋና ዋና ነጥቦች
​አላህን በብቸኝነት ማምለክ፦ ከአላህ ሌላ የሚመለክ አምላክ እንደሌለ ያረጋግጣል።
​ለወላጆች መልካም መሆን፦ ከእምነት ቀጥሎ ወላጆችን መንከባከብ ትልቅ ትዕዛዝ መሆኑን ያሳያል።
​በትሕትና መያዝ፦ በተለይ በዕድሜ ሲገፉ በፍቅር እና በትሕትና ልንይዛቸው እንደሚገባ ያስገነዝባል።
​ዱዓ (ጸሎት) ማድረግ፦ ወላጆች ላደረጉልን ውለታ አምላክ እዝነቱን እንዲያወርድላቸው መለመን እንዳለብን ያስተምራል።
​ይህ አንቀፅ በኢስላም ውስጥ ለወላጆች የሚሰጠውን ከፍተኛ ቦታ እና ክብር በግልጽ ያሳያል።

25/04/2025

11/04/2025

አስቸኳይ አስቸኳይይህ የወንድማችን ዘይኑ መኪና አሁን 11:15 ላይ ከስራ ቦታ ከሆነው አዲስ ሰፈር አስኮ አፍናን ካፌ በር ላይ በሌቦች ተወስዶበታል። የታርጋ ቁጥር አአ 29921 ኮድ 3   ...
26/06/2024

አስቸኳይ አስቸኳይ

ይህ የወንድማችን ዘይኑ መኪና አሁን 11:15 ላይ ከስራ ቦታ ከሆነው አዲስ ሰፈር አስኮ አፍናን ካፌ በር ላይ በሌቦች ተወስዶበታል። የታርጋ ቁጥር አአ 29921 ኮድ 3
ሲልቨር ከለር ዶልፊን አይናማው

ማንኛውም መረጃ ያላችሁ፤ 0911958452/0911715649 ላይ ደውላችሁ አሳውቁት።

14/06/2024

ነገን በፆም ፣ በኢስቲግፋር ፣ በኢባዳ ፣ በመልካም ተግባር እናሳልፍ

የአላህ መልእክተኛ ”ﷺ” ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦

«ያለፈውንና የመጪውን አመት ወንጀል ያስምራል፡፡»(ሙስሊም ዘግበውታል: 1162)

ታላቅ የዳዕዋ ጥሪ ኳታር ለምትገኙ ኢትዮጵያውያንበተወዳጁ ኡስታዝ በድሩ ሁሴን Engr/Ustaz Bedru Hussein - በድሩ ሁሴን  በኳታር ፋውንዴሽን መስጂድዛሬ ቅዳሜ  march 02 ምሽ...
02/03/2024

ታላቅ የዳዕዋ ጥሪ ኳታር ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን

በተወዳጁ ኡስታዝ በድሩ ሁሴን Engr/Ustaz Bedru Hussein - በድሩ ሁሴን

በኳታር ፋውንዴሽን መስጂድ

ዛሬ ቅዳሜ march 02 ምሽት ከኢሻ ሰላት ቡኃላ

ቢላል የኢትዮጵያ ሙስሊም ኮሚውኒቲ

ኪታባቸውን ተንተርሰው ወደቁ ❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️በሳኡዲ የሸህ ኡሰይሚን ደረሳ የነበሩ፤ሱደይስን ተጅሪድ ያቀሩ  ታላቁ ዓሊም ሀገር ውስጥ ከገቡ በኋላ በርካቶችን እያስተማሩ ነበር።...
07/01/2024

ኪታባቸውን ተንተርሰው ወደቁ
❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️

በሳኡዲ የሸህ ኡሰይሚን ደረሳ የነበሩ፤ሱደይስን ተጅሪድ ያቀሩ ታላቁ ዓሊም ሀገር ውስጥ ከገቡ በኋላ በርካቶችን እያስተማሩ ነበር። አሁን አስኮ በድር መስጅድ ኸጢብ ከመሆናቸው በፊት አፍንጮ በር የሚገኘው አቅሷ መስጅድ ያቀሩ እንደነበር የሚታወቁት በነሲሀ ቲቪም ሲያስተምሩ ይታወቃሉ።

ትናንት ምሽት ኪታባቸውን ተንተርሰው ለልጃቸው የገዙትን ዳቦ በትነው የወደቁበት ቦታ ላይ የዳቦው ፌስታል በደም ጨቅይቶ አየነው። ከጀርባቸው ሲመቱ አይነ በሲሩን አረቡን ቤቱ እየሸኙት ነበር።

ወደ አረቡ ቤት አቅንተን የሆነው ሁሉ ሲቃ እየተናነቀው አጫወተን። አረቡ እንደነገረን ከመግሪብ እስከ ኢሻ ተፍሲር ሲያቀሩ አመሹ። ለዚያውም ሱረቱል ዙመርን ሲያብራሩ አመሹ።

ሁሌም እንደሚያደርጉት መስጅድ በር ላይ ሲዋክ የሚሸጠውን አይነ በሲሩን አረቡን ለመሸት ጠበቁት። አረቡ ሁሌ እንደሚያደርገው «ኡስታዝ አይጠብቁኝ ይሂዱ» ይላቸዋል። እሳቸው እሽ አይሉም። ከኢሻ በኋላ ለአረቡ ምርኩዝ ናቸው። እንጀራ አይበላም ለሚሉት ለልጃቸው ዳቦ ገዝተው አረቡን ቤቱ እየመሩ አስገብተው ነው ወደቤታቸው የሚገቡት።

ትናንትም አይነ በሲሩን አረቡን እየመሩ ወደቤታቸው ሲሄዱ መታጠፊያ አሳቻ ቦታ ላይ ከቅርብ ርቀት በተተኮሰ ሽጉጥ ከጀርባቸው በኩል ተመተው የወደቁ ሲሆን በወቅቱ አረቡም ራሱን ስቶ አብሮ ወድቆ ነበር። በተመቱበት ሰዓት በአካባቢው መብራት ጠፍቶ እንደነበርና ከወደቁ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ መብራት መምጣቱን የአካባቢው ሰዎች ነግረውናል።

እዳ ያስጭንቃቸው እንደነበር እና በሽማግሌዎችም የተሰጣቸው ጊዜ አጭር በመሆኑ ያሳስባቸው እንደነበር የተወሰነውን ተበድረው ከፍለው ቀሪውን ለመክፈል ቤታቸውን ለመሸጥ እንዳሰቡ ነገር ግን የበድር መስጅድ ጀመዓዎች ቤቱ ከመሸጡ በፊት ትላንት ፈጅር ላይ ለመስጅድ ጀመአ ዛሬ እሁድ ገቢ ለማሰባሰብ እቅድ ተይዞ እንደነበር ነገሩን።

እናንተ የአላህ ባሮች ኢማማችንን ሸኻችንን ከየቲም ልጆቻቸው ጋር እና ከእዳቸው ጋር ለኛ ትተው ተገድለዋል።

ከቀብራቸው በፊት እዳ ለመክፈል እየተንቀሳቀሱ ያሉ ኮሚቴዎች አካውንት የከፈቱና የገለጹ ስለሆነ ፖሊስ ገዳዩን አጣርቶ ለህዝብ ይፋ እስኪያደርግ የመስጅድ ኢማም እንደመሆናቸው መጠን መጅሊስ በቅርብ ርቀት ዜናው ከተሰማበት አንስቶ ከሚመለከተው አካል ጋር ሲከታተል እንደነበረው ሁሉ ማህበረሰቡም ደግሞ እዳውን እንዲከፍል ጥሪ ቀርቧል።

የኢማማችን ባለቤት በቅርብ ጊዜ ወደ አኸራ የተሻገሩ በመሆኑ የቤቱ አስተዳዳሪ አባት ሸይኽ አላህ ይዘንላቸው ያለውን ክፍተት እንሙላ።

አስተባባሪ ኮሚቴ ስም የተከፈለ የሂሳብ አካውንት
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

የአካውንት ስም:- ጀሚል ሁሴን ፣ ሲሩ ሀሰን እና አብዱ ዑስማን
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:- 1000592716309

28/10/2023

የመጨረሻው የመስጂደል አቅሳ ጠባቂ  Mahi mahisho    ይህንን ታሪክ ስተረጉም ዕንባ እየተናነቀ የራሴ ልብ ሰላም ነስቶ በብረት ክንድ ይደልቀኛል። የዕንባ ከረጢቴ ዘለላ ዘለላ ዕንባን ...
21/10/2023

የመጨረሻው የመስጂደል አቅሳ ጠባቂ

Mahi mahisho

ይህንን ታሪክ ስተረጉም ዕንባ እየተናነቀ የራሴ ልብ ሰላም ነስቶ በብረት ክንድ ይደልቀኛል። የዕንባ ከረጢቴ ዘለላ ዘለላ ዕንባን እያረገፈ ሆድ ያስብሰኛል። እንዲህ ዓይነት የኢስላም ዘቦች ማለፋቸው እያስገረመ ያስለቅሰኛል። ቁጭት፣ ብሶት፣ ንዴትና ሀዘን ተፈራርቀው እኔስ ለኢስላም ምን አበረከትኩ ያስብለኛል።

እርሱ ኢየሩሳሌምን ለቆ ወደ ሀገሩ ቱርክ እንዲመለስ በታዘዘ ጊዜ “በይተል መቅዲስ ከሁሉ ነገሬ በላይ ነች ሦስተኛውን ቅዱስ ስፍራ ትቼ ብሄድ ረሱል ያዝኑብኛልና ፈፅሞ ይህን ቦታ ለቅቄ አልሄድም" ነበር ያለው።

“ኢልሃን በርዳክጂ” የተሰኘ የቱርክ ጋዜጠኛ “አቅሳ መስጂድ ግቢ ውስጥ አውቀዋለሁ” በሚል ርዕስ ታሪኩን እንዲህ ሲል ያካፍለናል:-
“አየሩ ሞቃታማ ነበር ሰውነቴ በላብ ተዘፍቋል። ፎቶግራፍ እያነሳሁ ወደ ላይኛው አደባባይ ወደ አስራ ሁለት ሺህ ሻማዎች ግቢ ወጣሁ፡፡ ከመግቢያው በራፍ አካባቢ በዘጠናዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኝ አንድን ሰው ተመለከትኩ። ልብሶቹ ቆሽሸዋል። ስጋ የለውም በአጥንቱ ቀርቷል። ማደሪያ የለው እዚያው ግርግዳውን ተደግፎ አረፍ ይላል። ከርሃብ መፈራረቅ ብዛት ሆዱ ከጀርባው ጋር ሊጣበቅ ተቃርቧል። ያደፉ ልብሶችን ያጠለቀ ፀጉሩና ፂሙ የተንጨባረሩ ጥቁርቁር ያለ ፊት ድህነት አጎሳቅሎ ያጠወለገው ሰው ይታያል።

አጠገቤ ከነበሩት ሰዎች አንዱን ጠርቼ ይህ ሰው ማነው? በማለት ጠየቅኩት "እብድ ነው እዚህ እንደ ሃውልት ቆሞ ለዓመታት ኖሯል። ማንንም አያናግርም። እሱ የሚመለከተው መስጂዱን ብቻ ነው" የሚል መልስ ቸረኝ።

ተጠጋሁትና ሰላምታ አቀረብኩለት። ዞረና ተመለከተኝ ዓይኖቹን ወደ መስጂዱ አቅጣጫ እየመለሰ "ሰላም ላንተ ይሁን" አለኝ። ይበልጥ ተጠጋሁትና ስለ ማንነቱ ጠየቅኩት፡፡ ሐዘን ባጠወለገው ፊቱ ጥርሱን ፈልቅቆ እንዲህ ሲል ታሪኩን አጫወተኝ
"እኔ የአስራ አንደኛው የመሣሪያ ጥበቃ ቡድን መሪ ስምንተኛው ሻለቃ የኦቶማን ጦር ስድስተኛው አምድ ኮረኔል ሐሰን አልግህዳርሊ ነኝ"

"ኦቶማን ኢምፓየር እየተጠቃ በነበረበት በዛን ወቅት በይተል መቅዲስ እንዳይዘረፍ ሰራዊታችን ተመደበ፡፡ የእንግሊዝ ጦር መስጂደል አቅሳን እንደተቆጣጠረ እኔም ጓደኞቼም ተይዘን በአንድ ክፍል ታጎርን"

ወደ ሀገሬ እንድመለስ ትዕዛዝ ሲሰጠኝ የካፒቴን ሙስጠፋ ንግግር ትዝ አለኝ
"ኢስላማዊው መንግስት በመፈረካከስ ላይ ነው። የተከበረው ሰራዊታችንም እየሸሸ ነው። አመራሩ ወደ ኢስታንቡል እንድመጣ ጠርቶኛል። በይተል መቅዲስ የሱልጣን ሰሊም አደራ ነው። ኢየሩሳሌምን ሸሽቶ የሄደ የመጀመሪያው ጦር እንዳንሆን ተጠንቀቁ፡፡ አደራ የእስልምናን ክብር ከእግራችሁ በታች እንዳታስቀምጡት"

ይህ ቃል ታወሰኝ በፍልስጤም ያሉ ወንድሞቻችን ኢስላማዊው ጦር ኦቶማን ኢምፓየር ጥሎን ሄደ እንዳይሉና እርዳታን የነፈግናቸው እንዳይመስላቸው በማሰብ ብቻዬን እዚያው ቆየሁ፡፡ ከአራት መቶ ዓመታት በኋላ የአል-አቅሳ መስጂድ እንዳያነባ ሰጋሁ። በዚህ ሁኔታ ዓመታቶች እንደ ዐይን ብልጭታ አለፉ። ሃምሳ ሶስት ነበርን። ጠላቶቻችንን ተጋፍጦ ማሸነፍ ሳይቻለን ቀርቶ የሁሉም ጓደኞቹ እጣ ፈንታ ሸሂድነት ሆነ"

ዓይኖቹ በዕንባ ተሞልተው ዕንባው ግንባሩ ላይ ከሚወጣው ላብ ጋር ተቀላቀለ።
"ልጄ እባክህ ስትመለስ ወደ ሳንጃክ ቶካት መንደር አቅና። የካፒቴን ሙስጠፋ መኖርያ እዚያ ነው፡፡ አማናውን የተቀበልኩት ከርሱ ነው። ስታገኘው እጆቹን ሳምልኝና እንዲህም በለው። አንድ ወታደርህ ባስቀመጥከው እዚያ ቦታ መስጂደል አቅሳን እየጠበቀ ነው በትዕዛዝህ መሠረት ካስቀመጥከው ቦታ አልተነቃነቀም። መስጂደል አቅሳን ከመጠበቅ ስራው ለአፍታም ተዘናግቶ አያውቅም ዱዓህን ይከጅላል በለው"

ጋዜጠኛው ንግግሩን ይቀጥላል
"ቱርክ እንደተመለስኩ ወደ ሳንጃክ ቶካት መንደር አመራሁ ከብዙ ጥረት በኋላ የአለቃውን አድራሻ አገኘሁ፡፡ ከብዙ ዓመታት በፊት መሞቱ ተነገረኝ።
የተመቻቸውን የትውልድ ሀገሩን ኑሮ ትቶ አል-አቅሳ መስጂድን እየጠበቀ ዓይኑን ከመስጂዱ ላይ ሳይነቅል እዚያው በተቀመጠበት እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ1982 ወደ አኼራ ነጎደ፡፡

ለአመታት ፀሐይና ብርዱ እየተፈራረቀብን ለኢስላም ዘበኛ ልንሆን ይቅርና በታዘዝነው የኢስላም ህግጋት ላይ ቀጥ ያልን ስንቶቻችን ነን የተመቻቸ ኑሮውን ትቶ ተቦሳቁሎና ተርቦ ለኢስላም ዘብ የቆመን ፈልጋችሁ አምጡልኝ።
በታሪክ መዝገብ ላይ በጥሩ ተዘከር

Address

Addis Ababa
12

Telephone

+201148118432

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Be patient . posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share