Ethio Online

Ethio Online ማንኛውንም እቃ በትዛዝ እናቀርባለን ቤት፣ መኪና፣ የንግድ፣ ቦታ እናሸሽጣለን

10ሩ በሲቪዎ (CV) ላይ ሊያደርጓቸውና ሊያስወግዷቸው የሚገቡ ነጥቦች #ቢዝነስሚዲያ / ​1) ሙያዊ ያልሆነ የኢሜይል አድራሻ (Professional Email)​ስህተት፦ super.man2024...
24/12/2025

10ሩ በሲቪዎ (CV) ላይ ሊያደርጓቸውና ሊያስወግዷቸው የሚገቡ ነጥቦች

#ቢዝነስሚዲያ / ​1) ሙያዊ ያልሆነ የኢሜይል አድራሻ (Professional Email)
​ስህተት፦ [email protected]
​ትክክል፦ [email protected]

​2) ከስራው ጋር የማይገናኙ የትርፍ ጊዜ ፍላጎቶች (Relevant Hobbies)
​ስህተት፦ ፊልም ማየት (Watching movies) ❌
​ትክክል፦ ስልታዊ ጨዋታዎች (Strategic games/Chess) ✅

​3) በጣም ዝርዝር የሆነ አድራሻ (Minimal Address)
​ስህተት፦ አዲስ አበባ፣ የካ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 07፣ የቤት ቁጥር 123 ❌
​ትክክል፦ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ (Addis Ababa, Ethiopia) ✅

​4) አላስፈላጊ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች (Professional Social Media)
​ስህተት፦ TikTok, Snapchat ❌
​ትክክል፦ LinkedIn, GitHub (ለቴክኖሎጂ ስራዎች) ✅

​5) የሲቪ የጀርባ ቀለምና ዲዛይን (CV Background Color)
​ስህተት፦ ደማቅ ቀለሞች ወይም ጥቁር ዳራ ❌
​ትክክል፦ ንጹህ ነጭ (White background) ✅

​6) የሙያ ማጠቃለያ ግልጽነት (Clear Professional Summary)
​ስህተት፦ "ስራ ፈልጋለሁ" (Seeking any job) ❌
​ትክክል፦ "ባለኝ የ5 ዓመት ልምድ ድርጅቱን መጥቀም እችላለሁ" (The right fit for the role) ✅

​7) የፊደል አጻጻፍ ስታይል (Simple Fonts)
​ስህተት፦ ለማንበብ የሚከብዱ ጌጣጌጥ የበዛባቸው ፊደላት (Fancy fonts) ❌
​ትክክል፦ ግልጽና ቀላል ፊደላት (Arial, Calibri) ✅

​8) የትምህርት ደረጃ አቀራረብ (Education Focus)
​ስህተት፦ የ8ኛ ወይም የ10ኛ ክፍል ውጤት መጥቀስ ❌
​ትክክል፦ የመጨረሻው የተመረቁበት ከፍተኛ ትምህርት (Degree/Diploma) ✅

​9) አላስፈላጊ የግል መረጃዎች (Personal Information)
​ስህተት፦ የጋብቻ ሁኔታ፣ ሃይማኖት፣ የፖለቲካ አመለካከት ❌
​ትክክል፦ ስም፣ ስልክ ቁጥር እና የሙያ ብቃት ብቻ ✅

​10) ተያያዥነት የሌለው የሥራ ልምድ (Relevant Work History)
​ስህተት፦ ለሂሳብ ሹምነት ስራ እያመለከቱ ስለ ሹፌርነት ልምድ መጥቀስ ❌
​ትክክል፦ ከሚያመለክቱበት ዘርፍ ጋር የሚሄድ ልምድ (Relevant Experience) ✅

28/11/2025

#አባየ #እማየ

28/11/2025


😂😂😂😂

29/10/2025

ፌስቡክና ቢዝነስ ❗️

#ቢዝነስሚዲያ l ( ፌስቡክን እንዴት የገቢ ምንጭ እናድርገው? )

📌 ፌስቡክ ብዙዎች የገቢ ምንጭ ፣ ደንበኛ ማግኛ ካደረጉት ቆይቷል !

~ የተለያዩ ፖስቶችን ስለ Facebook በ አቅርበንላችኋል ዛሬ አንድ የተለየ ነገር እንገራችሁ !

- ስለ ፌስቡክ እንዴት እንደሚከፍል ከ አሁን በፊት የፃፍነውን ተመልከቱ ዛሬ መረጃ ልንሰጥ የፈለገው ጉዳይ ግን ከስር አለ ፦

ፌስቡክ የገቢ ምንጭ ለማድረግ እነዚህን መረጃ ተመልከቱ

1) የራሳችሁ ሙያ ፣ ምርጥ(እቃ) ወይም service ካላችሁ Facebook ጥሩ platform ነው ። ለሰው የምታቀርቡትን ነገር በመፖሰት ከሰዎች ጋር በመተዋወቅ የናንተን የ ፌስቡክ ደንበኛ የናንተ እቃ ፣ service ገዢ ማድረግ ትችላላችሁ !

በጣም አዋጭ መንገድ ነው ተጠቀሙበት Facebook ተጠቃሚ ብቻ አትሁኑ የገቢ ምንጭም አድርጉት ።

2) አጫጭር ቪዶ በመልቀቅ ከ Facebook ገንዘብ መስራት ።

ቪዶ ሞልቷል አነሱን በመሰብሰብ (copyright ) ያልሆነ እናንተም ቪዶ ምሰሩ ከሆነ አሪፍ ገቢ በወር ይገኛል ።

የምትሉቁት በ reels መልክ ሲሆን የ ፌስቡክ ህግ ስታሟሉ በዶላር በወር የሰራችሁትን ታገኛላችሁ !

(አዲስ ነገር ልንገራችሁ ) ያልነው ከዚህ ቀጥሎ ያለው ሃሳብ ነው !

Facebook Ethiopia ውስጥ ላለ ሰው አይከፍልም ይታወቃል ምክንያቱም Ethiopia eligible ስላልሆነች ነው ።
ለዚህም ከውጭ ሀገር አንድ ሰው ያስፈልጋችኋል ብለን ነበር ካለ ጥሩ ነው ከለለ ግን አሁን ያመጠናውን Method ተጠቀሙ VPN በመጠቀም !

📌 የምትጠቀሙት Facebook በ VPN መጠቀም አለባችሁ አንድ ቋሚ ሀገር መርጣችሁ !

📍ሁሌም data ስታበሩ ና Facebook ን ስትጠቀሙ VPN ካበራችሁ Facebook የናንተን location ከሀገር ውጭ እንደሆነ ነው የሚያስብ በዚህ መሰረት የ monetization ሂደት ስትጨርሱ payment ነገር ደግሞ ትንሽ ያስቸግራል ግን እሱን እኛ እንተባበራችኋለን !

ማስታወሻ :-

📍 ይህን የፃፍነው የ አንድን ወንድማችን video የሚለቅ page በማስተዳደር Monetization ሂደት አስጨርሰን በወር ከ 12 ቀን $46 ዶላር ስለሰራ ነው !(በትንሹ) ብሩንም በራሳችል የ Paypal account አውጥተን ሰተነዋል !

📍 monetization ስታደርጉ አንዳንድ skill (ያስፈልጋል) በአጭር ጊዚ ለመጨረስ እናዛን መንገድ ተጠቀሙ በፍፁም copyright የሆነ ፣ የ Facebook ህግን የሚጥስ ነገር አትልቁቁ አላስፈላጊ ሃሽታግ አትጠቀሙ !

📍 የፌስቡክ አልጎሪዝም በ አብዛኛው ስለተቀየረ በአጭር ጊዜ መስራት ትችላላችሁ ሞክሩ ስሩ ተማሩ !

ጥያቄ ካለ we are active for 10 minutes (comment) እንመልሳለን !

30 ለማመን የሚከብዱ የአለም እውነታዋች1★ ወፎች አይሸኑም2★ጉንዳኖች ፈፅሞ አይተኙም፤ሳንባ የላቸውም፤ሰራተኛ ጉንዳን እስከ 7 ዓመት ሊኖር ይችላል ንግስቶ ግን እስከ 15 ዓመት ልትኖር ትች...
11/08/2025

30 ለማመን የሚከብዱ የአለም እውነታዋች
1★ ወፎች አይሸኑም
2★ጉንዳኖች ፈፅሞ አይተኙም፤ሳንባ የላቸውም፤ሰራተኛ ጉንዳን እስከ 7 ዓመት ሊኖር ይችላል ንግስቶ ግን እስከ 15 ዓመት ልትኖር ትችላለች::
3★ሻርክ ብቸኛው የማይታመም እንሰሳ ነው ምንም አይነት በሽታ አያጠቃውም ካንሰርን ጨምሮ::
4★ፈረሶች እና ላሞች ቁመው ነው እሚያንቀላፉት::
5★የማር ንብ ሁለት ሆድ ሲኖራቸው አንዱ ለማር ሲሆን ሁለተኛው ለሚመገቡት ምግብ ማስቀመጫ ያገለግላቸዋል::
6★ትልቁ ነጭ ሻርክ ከሶስት ወር በላይ ሳይበላ መጎዝ ይችላል::
7★አብዛኞቹ ዝሆኖች በክብደት ከስማያዊ አሳነባሪ(Blue whale) ምላስ ያንሳሉ::
8★በረሮ በርሀብ እስኪሞት ድረስ ለሳምንት ያህል ጭንቅላቱ ተቆርጦ በሂወት መቆየት ይችላል::
9★የአህያ አይን አቀማመጥ በአንድ ግዜ አራቱንም እግሮች ማይት ያስችሉታል::
10★ዶልፊን ውሀ ውስጥ ከ24ኪ.ሚ ርቀት ያለ ድምፅ በቀላሉ መስማት ይችላል::
11★የወባ ትንኝ(Mosquito) 47 ጥርስ አላት::
12★ማንኛውም ሁለት የሚዳ አህያ(zebra) እንድ አይነት መስመር አይኖራቸውም::
13★ቢራቢሮ የሚቀምሱት(taste) በሆላ እግራቸው ነው::
14★የወንድ ሸረሪት የወሲብ አካል በአንዱ የእግሩ ጫፍ ላይ ይገኛል::
15★ንቦች አምስት አይን አላቸው::
16★አሳማ በተፈጥሮ(physical) ወደ ሰማይ ማየት አያስችለውም::
17★አይጥ ከተራበች የራሶን ጅራት ትበላለች
18★ ለሚስቱ ታማኝ የሆነ እንስሳ ቀበሮ ብቻ ነው
18★ሰማያዊ አሳነባሪ (Blue whale) በመጠን እስካሁን በአለማችን ከነበሩ እና ካሉ እንሰሳዎች ትልቁ ነው::
20★ የለሌት ወፍ ብቸኛዋ ከአጥቢዎች መብረር የምትችል ሲሆን የእግር አጥንቶቾ ከመቅጠናቸው የተነሳ መብረር እንጂ መራመድ አትችልም::
21★የለሌት ወፍ ምንግዚም ከዋሻ ሲወጡ ወደ ግራ ይበራሉ::
22★እባብ አይኖቹ ቢከደኑም በአይኖቹ ቆብ ማየት ይችላል::
23★ወንድ የወባ ትንኝ አይናደፍም ሴቶ ብቻ ናት መናደፍ
የምትችለው:: /femal Anofiles mosqto/
24★ የዱር አይጥ (Rat) በፍጥነት መራባት የሚችሉ ሲሆን በ18 ወራት ብቻ 2 አይጦች 1 ሚሊዮን ዘመዶችን ማፍራት ይችላሉ::
25★አንድ ንብ አንድ የሾርባ ማንኪያ ማር ለማዘጋጀት ከ 4000 በላይ አበቦችን መጎብኝት አለባት ::
26★ቀንድ አውጣ ለ3 አመት መተኛት ይችላል::
27★ አንድ ላይ የተያያዘ የሸረሪት ድር ተመሳሳይ ወፍረት ካለው አንድ ላይ ከተያያዘ የብረት ሺቦ ይጠነክራል::
28★ዝሆኖች ከ3ማይል ላይ ያለ ውሀ ማሺተት ይችላሉ::
29★ኦይሰትር(Oyster) የተባለ የአሳ ዝርያ ከአንዱ ፆታ ወደ ሊላኛው እንዲሁም ወደ ነበረበት ለወሲብ በሚመቸው ፆታውን መቀየር ይችላል::
30★በየአመቱ 1/3 የሚሆነው የአለማችን ሰብል በተባይ/ነብሳት ይወድማል::
=>ስንት ቁጥር አግራሞትን ፈጠርባችሁ ??
የተመቸው ሼር፣ላይክ እንዳይርሳ
online

በራስ መተማመንን (Self Confidence) ለማሳደግ የሚረዱ (10) ሙያዊ ምክሮች===========ለራስዎ ያለዎት ከፍ ያለ ግምት ሌሎች እርስዎን የሚያዩበት መንገድ ጥሩ እንዲሆን ከፍተኛ ...
09/06/2025

በራስ መተማመንን (Self Confidence) ለማሳደግ የሚረዱ (10) ሙያዊ ምክሮች
===========

ለራስዎ ያለዎት ከፍ ያለ ግምት ሌሎች እርስዎን የሚያዩበት መንገድ ጥሩ እንዲሆን ከፍተኛ ሚና አለው። በራስ የመተማመን ስሜት ሲኖርዎትም በተሰማሩበት ሥራ ላይ የበለጠ ስኬታማ እንዲሆኑ ከፍተኛ እርዳታ አለው።
ምንም እንኳን በራስ መተማመን ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩት ምክንያቶች ብዙዎቹ ከእርስዎ ቁጥጥር ውጭ ቢሆኑም፣ በራስ መተማመንን ለመገንባት የሚረዱ ብዙ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ። እነዚህን 10 ስትራቴጂዎች በመጠቀም ያልዎትን በራስ መተማመን ከፍ አድርገው ችሎታዎን በትክክለኛው ሁኔታ ሥራ ላይ ማዋል ይችላሉ።

1. አለባበስዎ ጥሩ ይሁን (Dress sharp)

የእርስዎ አካላዊ ገጽታ እና አለባበስ ላይ ከማንም ሰው በላይ እርስዎ የቀረበ እይታ እና ግንዛቤ አለዎት። ስለሆነም፣ ጥሩ ሆነው እንደማይታዩ በሚሰማዎት ጊዜ፣ ከሌሎች ጋር የሚያደርጉት የሃሳብ ልውውጥ ሂደት ውስጥ ምቾት እንዳይሰማዎት ያደርጋል። ስለራስዎ ገፅታ ግን መልካም አመለካከት ሲኖርዎ ምቾትዎ ይጠበቅና ከሰዎች ጋር የሚያደርጉዋቸው ግንኙነቶች ላይ ልበ ሙል ይሆናል። የራስ ገፅታን ጥሩ ለማድረግ የሰውነትን እና የገላን ንፅህና መጠበቅ፣ ፀጉርን እና ፂምን በቅጡ መከርከም እንዲሁም በወቅቱ ተቀባይ የሆኑ ፋሺኖችን በማዎቅ እና አቅም በፈቀደ መልኩ መከተል ይረዳል። ይህ ማለት በልብስ ላይ ብዙ ገንዘብ ማውጣት አለብዎት ማለት አይደለም። ነገር ግን፣ ብዙ ርካሽ ልብሶችን ከመግዛት ይልቅ፣ ጥቂት የተመረጡ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች መግዛት አለባበስን ጥሩ ለማድረግ ከመርዳታቸውም በላይ ለረጅም ጊዜ ዘመናዊ ሆነው እንዲቆዩ ስለሚያደርጉ ረዘም ላለ ጊዜ ወጪን ይቀንሳሉ።

2. ሲራመዱ ፍጥነት በተሞላበት ሁኔታ ይራመዱ (Walk faster)

አንድ ሰው ስለ ራሱ ያለውን ስሜት ለማወቅ ብዙዎች ከሚጠቀሙባቸው ቀላል መንገዶች ውስጥ አንዱ አረማመዱን መመርመር ነው። ዝግ ብሎ የሚራመድ ነው? ሲራመድ ድካም ይታይበታል? ወይስ ሃይል የተሞላ እና አላማ ያለው አካሄድ አለው? በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎች በፍጥነት ይራመዳሉ። አፋጣኝ የሆነ ጉዳይ ባይኖርብዎትም እንኳ ፈጠን ብለው በመራመድ የራስዎን መተማመን ከፍ ማድረግ ይችላሉ።

3. ሁሌም ጥሩ የሰውነት አቋም ያሳዩ (Have a good posture)

በተመሳሳይ መንገድ፣ አንድ ሰው ሰውነቱን የተሸከመበት መንገድ ሰውየው ስላለው የራስ መተማመን ብዙ ይናግራል። የተጣበቁ ትከሻዎች እና የተልፈሰፈሰ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ሰዎች የራስ መተማመን ማጣትን ያሳያሉ። እራሳቸውን ከፍ አድርገው አይመለከቱትም። ጥሩ አቋም በማሳየት ግን በራስ መተማመን ይሰማዎታል። ቀጥ ያለ ሰውነት ይኑርዎ፣ ጭንቅላትዎን ወደላይ ከፍ ያርጉ፣ ከሌሎች ጋር ሲነጋገሩ የዓይን ለአይን ግንኙነት ያድርጉ። ይህንም ሲያደርጉ ሌሎች ላይ አዎንታዊ ስሜት ያሳድራሉ፣ እናም በፍጥነት የበለጠ ንቃት እና ኃይል ያሰማዎታል።

4. ለራስዎ ስለ ራስዎ ማስታዎቂያ ይስሩ (Do personal commercial)

ጠንካራ ጎኖችዎን እና ግቦችዎን የሚያጎሉ ከ 30-60 ሰከንድ የሚዎስዱ ንግግር ይጻፉ። ከዚያም በራስ የመተማመን ስሜት በሚፈልጉበት ጊዜ በመስታወት ፊት ለፊት በመቆም (ወይም ጭንቅላትዎ ውስጥ በማነብነብ) ለራስዎ ይንገሩ።

5. በምስጋና የተሞሉ ይሁኑ (Have gratitude)

ምስጋና ሊሰማዎት የሚያነሳሳዎትን ነገሮች ሁሉ በአዕምሮዎ ውስጥ በመዘርዘር የሚያስቡበት ጊዜ በየዕለቱ ይመድቡ። ያለፉትን ስኬቶችዎን፣ ልዩ ችሎታዎችዎን፣ ወዳጆችዎን እና አዎንታዊ እንቅስቃሴዎን ያስታውሱ።

 #ሰይጣንን((መናፍስትን)) የሚያሳየው ካሜራ‼️thermal camera ይሉታል በCCD ካሜራ ሊታይ የማይችልውን ሁሉ ልቅም አድርጎ ያሳያል። Behind the image(ከምስሉ ጀርባ) ያለውን...
07/06/2025

#ሰይጣንን((መናፍስትን)) የሚያሳየው ካሜራ‼️

thermal camera ይሉታል በCCD ካሜራ ሊታይ የማይችልውን ሁሉ ልቅም አድርጎ ያሳያል። Behind the image(ከምስሉ ጀርባ) ያለውን ነገር ያሳየናል። #ለምሳሌ በካሜራው ሙከራ ወቅት የተገኙት ምስሎች መካከል፦ ፈስ የሚፈሱ ሰዎች፣ ሰዎች በተኙበት ሰዎችን የሚያፍኑ መናፍስት ጭምር ታይተዋል ድንቅ ግኘት ነው! አለም እንግዲህ ከሚታየው አለም ወደማይታየው አለም ለመግባት እየገሰገሰ ነው!!!

አለም የደረሰችበት የቴክኖሎጂ ብቃት ይገርማል

@ለሰርግ @ለልደት @ለተለያዩ _ፕሮግራሞች ባሉበት እናደርሳለን
20/05/2025

@ለሰርግ
@ለልደት
@ለተለያዩ _ፕሮግራሞች
ባሉበት እናደርሳለን

20/05/2025

#መሳደብ አትችሉም????

17/05/2025

የሱ ታማሚ ነኝ የሱ በሽተኛ

 #ባሏን  #የገደለው  #መርዝ ////ይነበብ////ከእለታት በአንድ ቀን አንዲት ውብ የሆነች ልጃገረድ ባገባች በሁለተኛ ዓመቷ ትዳሯ ምርር ስላላት ባሏን ለመግደል ፈለገች።ይህች ቆንጆ ልጅም ...
28/04/2025

#ባሏን #የገደለው #መርዝ ////ይነበብ////

ከእለታት በአንድ ቀን አንዲት ውብ የሆነች ልጃገረድ ባገባች በሁለተኛ ዓመቷ ትዳሯ ምርር ስላላት ባሏን ለመግደል ፈለገች።
ይህች ቆንጆ ልጅም ወደ እናቷ ቤት በመሄድ "እናቴ የባሌ ነገር አድክሞኛል የሚያደርጋቸው ነገሮች ሰልቺተውኛል፣ለእኔ አያስብልኝም፣ዞር ብሎ እንኳን አያየኝም እኔንጃ ከሌላ ሴት
ጋር የጀመረው ነገር አለ እርሱን ገድዬ መገላገል እፈልጋለሁ በአንድ በኩል ደግሞ ህግ ያስረኛል ብየ እፈራለሁ እና እባክሽ እርጅኝ?አለቻት።

እናቷም:-እሺ እረዳሻለሁ የእኔ ውድ ልጅ ግን መጀመሪያ የምታደርጊያቸው ነገሮች አሉ አለቻት።

ልጅቷም:አንቺ ያልሽኝን ነገሮች በሙሉ እፈጽማለሁ አለች።
እናትየዋም:-ባልሽ ሞቶ አስከሬኑ ከቤት እስኪወጣ ድረስ ከዚህ በታች ያሉትን 6 ነገሮች በጥንቃቄ ፈጽሜያቸው አለች።

1.የገደለችው እርሶ ናት ብለው እንዳይጠረጥሩሽ ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ፍጠሪ።
2.ሁልጊዜ ውበትሽን ጠብቀሽ ወጣትና ውብ ሁነሽ ታይ።
3.በደንብ አድርገሽ ተንከባከቢው ጥሩ ሁኝለት አበርችው።
4.ትዕግስት አድርጊ ብዙም አትቅኚ፣ብዙ ጊዜ አድማጭ ሁኚ በማክበር ታዘዥው።
5.በእጅሽ ያለውን ገንዘብ አንዲችም በለሽ ሳታስቀሪ እርሱን ለማስደሰት አውይው።
6.ማንም ገድላዋለች ብሎ እንዳያስብ የጭቅጭቅ ድምፅ ከአፍሽ እንዳይወጣ ሰላም እና የፍቅር ቃል ከአፍሽ ይውጣ እስክትገላገይው ድረስ ብቻ።

እናትዮዋ:-በድጋሚ ያልኩሽን ነገሮች ሳታዛንፊ ታደርጊለሽ አለቻት?
ልጅቷም እርሱ ሞቶ ይውጣልኝ እንጂ አንድም ሳላስቀር አደርገዋለሁ ብላ መለሰች።

እናትየዋም አንድ ብልቃጥ አውጥታ ይህን መርዝ ያዥውና ሁሌም ከሚበላው ምግብ ጋር እየጨመርሽ ስጭው መርዙም አመንምኖ ይገድለዋል።

ልጅቷም ደስ እያላት ወደ ቤቷ ተመለሰች።

ልጅቷ:-ከአንድ ወር በኋላ ተመልሳ ወይ ጉድ ሰውየው ወሬውን ሳይሰማ አይቀርም መሰለኝ ድሮ አድርጎት የማያውቀውን "ማሬ፣ፍቅሬ፣ወለላዬ፣
ህይወቴ፣ንግስቴ፣በዓለም ላይ አንቺን የምታክል ሴት የለችም ይለኛል እኔ እንጂ ፀባዩ ልውጥውጥ ብሎብኛል።

እናትየዋም:-መርዙን እየሰጠሽው ነው አለቻት?ልጅቷም አይኗ እንባ እያቀረረ
አዎ ግን አሁን ፀባዩ ሸጋ፣አፍቃሪ ባል ኋኖል እና እንዲሞትብኝ አልፈልግም እባክሽ ማርከሻ መድሀኒት ፈልጊልኝ ፀፀቱ ሊገለኝ ነው እማዬ???

እናትየዋም:-ልጄ በብልቃጥ የሰጠሁሽ መርዝ አይደለም የእርድ ዱቄት ነው።ነገር ግን ቀስ በቀስ ፀባዩ መጥፎ ባልሽን የገደልሽው "መርዟ አንቺ ነሽ"ማለቴ እሱን ማፍቀር ፣መታዘዝ ፣መንከባከብ ፣መታገስ
እና ውብ ሁነሽ ስትገኝ ባልሽን መቀየር ትችያለሽ።

አንቺ ያልሰጠሽውን ነገር እንዴት ከሌላ ሰው ትጠብቂያለሽ?ፍቅር ማለት ሰጥቷ መቀበል ነው።

👍 ካነበብኩት!

03/04/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Rozental Woldekidan, Abraham Alemayehu, Meti Nahome

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Online posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share