Aman design

Aman design I produce and sell some cloth design works

አንድ ጊዜ አንድ ባልና ሚስት ወደ ባንክ በመሄድ ላይ ሳሉ፣ በአንድ ጥግ ላይ ምግብ በመስረቁ ምክንያት በሰዎች ተደብድቦ የወደቀ ህፃን ተመለከቱ። ሰውነቱ ቆስሎና ደክሞ ያዩት ይህ ህፃን አንጀ...
05/12/2025

አንድ ጊዜ አንድ ባልና ሚስት ወደ ባንክ በመሄድ ላይ ሳሉ፣ በአንድ ጥግ ላይ ምግብ በመስረቁ ምክንያት በሰዎች ተደብድቦ የወደቀ ህፃን ተመለከቱ። ሰውነቱ ቆስሎና ደክሞ ያዩት ይህ ህፃን አንጀታቸውን በላው።

በሁኔታው በጣም ስለደነገጡ በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ወሰዱት። የህክምና ወጪውንም ሙሉ ለሙሉ ከፍለው፣ ህፃኑን ወደ ቤታቸው በመውሰድ ተንከባከቡት። "ሉክ" የተባለው ይህ ህፃን ከህመሙ አገግሞ ሲነቃ የልቡን እውነት አወጣላቸው። በሚንቀጠቀጥና ዝቅተኛ ድምፅ፣ "ሁሌም ዶክተር መሆን ነበር ህልሜ፤ ነገር ግን ወላጆቼ በመኪና አደጋ ከሞቱ በኋላ ጎዳና ላይ ወደቅሁ። ህይወቴን ለማትረፍ ስል ምግብ ለመስረቅ ተገደድኩ" አላቸው። ባልና ሚስቱም በልጁ ታሪክ ልባቸው ተነካ፤ እንደ ልጃቸው አድርገው ሊያሳድጉትና ሊያስተምሩት ወሰኑ።

ነገር ግን ነገሮች እነሱ እንዳሰቡት አልሆኑም። የገዛ ልጃቸው ወላጆቹ ለሉክ በሚያሳዩት ፍቅርና እንክብካቤ በቅናት እሳት ተቃጠለ። አንድ ቀን ወላጆቹን አስጠራና፣ "ይህን የጎዳና ልጅ እዚህ ቤት ካስቀራችሁት ራሴን አጠፋለሁ! ወይ እኔን ምረጡ ወይም እሱን!" ሲል አስፈራራቸው።

ባልና ሚስቱ በህይወታቸው ገጥሟቸው የማያውቅ ከባድ ፈተና ውስጥ ወደቁ። የገዛ ልጃቸው ህይወት አደጋ ውስጥ እንዳይገባ በመስጋት፣ የማይቻል የሚመስል ውሳኔ ወሰኑ። ሉክን ጠሩትና የነበራቸውን ጥሪትና የቆጠቡትን ገንዘብ ሰጥተው፣ አይኖቻቸው በእንባ እየረጠበ መረቁት። ሉክም ውለታቸውን አስቦ፣ እያዘነ ተሰናበታቸው።

ከዚያ ጊዜ በኋላ አስር አመታት አለፉ። የተምበሸበሸው ልጃቸው ግን እንደጠበቁት አልሆነም። ምግባረ ብልሹ፣ ሱሰኛና ቁማርተኛ ሆነ። ወላጆቹ ከእሱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማቋረጥ ሲፈልጉ፣ ይባስ ብሎ ያለችቸውን ቤት ሽጦ ከገዛ ቤታቸው አባረራቸው። እነዚያ አዛውንቶችም ሜዳ ላይ ቀሩ።

አንድ ቀን አዛውንቱ ሰውዬ የዕለት ጉርሳቸውን ለማግኘት ፕላስቲክ ሲለቅሙ፣ በከፍተኛ ፍጥነት ይጓዝ የነበረ መኪና ገጫቸው። በሰዎች እርዳታ ወደ ሆስፒታል ቢወሰዱም ሁኔታቸው አሳሳቢ ነበር። ዶክተሩ ወደ ሚስትየው መጣና፣ "ባለቤትዎ አስቸኳይ ቀዶ ጥገና ያስፈልገዋል፤ አለበለዚያ ህይወታቸው ያልፋል። ነገር ግን መጀመሪያ ክፍያ መፈጸም አለባችሁ" አላቸው።

ሚስትየው ተስፋ በቆረጠ ስሜት አለቀሰች። "ምንም የለንም፤ የሚረዳንም ሰው የለም፣ እባካችሁ!" እያለች ተንሰፈሰፈች።

በዚያው ቅፅበት አንዲት ነርስ አንድ ፖስታ ይዛ መጣች። "ዶክተሩ ይህንን እንድሰጥዎት ነግሮኛል" አለቻት። ሚስትየው ፖስታውን ተቀበለች፤ ፖስታው ላይ "ለእማማ" የሚል ጽሑፍ ሰፍሯል።

"እማማ? አይሆንም... የኔ ልጅ ጨካኝ ነው፤ እሱ ዶክተር ሊሆን አይችልም፣ ማን ሊሆን ይችላል?" ስትል በሀሳብ ተዋጠች። እየተንቀጠቀጡ ባሉ ጣቶቿ ደብዳቤውን ከፈተችው። ቃላቶቹን ስታነብ ግን በድንጋጤ ደርቃ ቀረች። ደብዳቤው እንዲህ ይላል፡-

"እኔ ነኝ፣ ሉክ። ከአስር አመት በፊት ያዳናችሁኝ ያ ቤት አልባ ልጅ። ዛሬ የዚህ ሆስፒታል ዋና ሃላፊ ዶክተር እኔ ነኝ። የአባዬን ቀዶ ጥገና ክፍያ ሙሉ ለሙሉ ከፍያለሁ፤ አባዬ በጥሩ እጆች ላይ ነው ያለውና አትስጉ። እንዲሁም አንድ ቀን ፈጣሪ ያገናኘናል በሚል ተስፋ ለሁለታችሁ የሚሆን ቤት ገዝቼ አስቀምጫለሁ። እባካችሁ ወደ ቤታችሁ ኑ።"

ሚስትየው የደብዳቤውን መልእክት ስትጨርስ ከንፈሮቿ ተንቀጠቀጡ። የአስር አመት የናፍቆት፣ የህመም እና የሃዘን ስሜቷ በደስታ እንባ ታጥቦ ጠፋ።
.... ......... ..........

ደግነት የዘራነው ዘር ነው። ዛሬ መልካም ብናደርግ፣ ነገ ወይም ከነገ ወዲያ እጥፍ ሆኖ ወደ እኛ ይመለሳል።
# በጎነት አይከሽፍም!

06/11/2025

1. አንድን ሰው (እንደሰማህ እያወቅክ) በተከታታይ ከሁለት ጊዜ በላይ አትጥራው፡፡ መልስ ካልሰጠህ ምናልባት የሆነ እየሰራው ያለው ነገር ሊኖር እንደሚችል ወይም በራሱ ምክንያት መልስ ሊሰጥህ እንዳልፈለገ ይግባህ፡፡

2. የተበደርከውን ገንዘብ አበዳሪህ ከመጠየቁ በፊት መልስ፡፡ ምን ያህል ለቃልህ ታማኝና ሃላፊነት የሚሰማህ ሰው እንደሆንክ ማረጋገጫው እሱ ነው፡፡በአንጻሩ የተበደርከውን ጃንጥላም ቢሆን እስክሪፕቶ ሳትጠየቅ መመለስ ቁምነገረኝነትህን ያሳያል፡፡

3. ማንም ሰው ሊጋብዝህ ወደሆቴል ቢወስድህ ከሜኑው ውስጥ ውድ ዋጋ የሚያወጣውን ምግብ አትዘዝ፡፡ሰዎች ምን ደግ ቢሆኑ ይሉኝታ የሌለው ሰውን መታዘባቸው እንደማይቀር አትርሳ፡፡

4. ማንንም ሰው “ለምን እስካሁን አላገባህም/ሽም?" አይነት የግል ጥያቄዎችን አትጠይቅ። ወይም "ለምን ልጅ አልወለድክም/ሽም " አትበል፡፡ ይህ የነርሱ እንጂ ያንተ ጉዳይ አይደለም፡፡ እንዲህ አይነት ጥያቄ ሰዎችን ያሳቅቃል፡፡

5. በር ከፍተህ ስትገባ ከኋላህ ወንድም ሆነ ሴት፣ ትልቅም ሆነ ትንሽ ሰው ቢኖር በሩ በላያቸው እንዳይዘጋ ያዝላቸው፡፡ ለሰዎች ትህትና ማሳየት አንተን ያስከብርህ ይሆናል እንጂ ትንሽ አያደርግህም፡፡

6. ከጓደኛህ ጋር ታክሲ ተሳፍረህ ስትሄድ እሱ ከከፈለ ሌላ ቀን ደግሞ ራስህ ክፈል፡፡ ፈቅዶ ካልሆነ በቀር በይሉኝታ ማንም ሰው ያንተን ወጪ የመካፈል ግዴታ የለበትም፡፡

7. ሁሌም እኔ ብቻ ልክ ነኝ አትበል፡፡ ላንተ 6 ቁጥር የሚመስለው ለሌላው ሰው 9 ቁጥር ሊሆን ይችላል፡፡ ትክክልነት ካለህበት አንጻር የሚታይ አንጻራዊነት ነው፡፡ ካንተ የተለየ አስተያየት ማግኘት ይጠቅምሃል እንጂ አይጎዳህም፡፡

8. ሰው ሲናገር እስኪጨርስ ጠብቅ እንጂ አታቋርጥ፡፡ አንድ ሰው ለማለት የሚፈልገውን ሳይጨርስ አስተያየት መስጠት ወደስህተት ሊመራህ ይችላል፡፡

9. በሰዎች ላይ በቀልድ አታሹፍ፡፡ በተለይ ሹፈቱን ካልወደዱት ወዲያውኑ አቁም፡፡ እንዲህ ያለውን ነገር አለመድገም ለሰዎች ስሜት ምን ያህል እንደምትጠነቀቅ ማሳያ ነው፡፡

10. ሁሌም ሰዎች በጥያቄህ መሰረት ከረዱህ በኋላ “አመሰግናለሁ” ማለት ይልመድብህ፡፡

11. ሰዎችን በአደባባይ አመስግን፡፡ የሚታረም ነገር ካላቸውም ቀስ ብለህ በግላቸው ንገራቸው እንጂ በሰው ፊት አታሳጣቸው፡፡ ለመሻሻል የሚጠቅማቸው ይህንን ማድረግህ ነው፡፡

12. ማንንም ሰው ክብደቱን በተመለከተ አስተያየት አትስጥ፡፡ ምናልባት ጥሩ ለብሶ/ሳ ካየህ “ዛሬ ዘንጠሃል ወይም በጣም ታምሪያለሽ” ብቻ በል፡፡ሰዎች ስለውፍረታቸውና ስለቅጥነታቸው ከፈለጉ ራሳቸው ይናገሩ እንጂ ያንተ አስተያየት ሊያበሳጫቸው ይችላል፡፡

13. ሰዎች በስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ሲሰጡህ ያሳዩህን ብቻ አይተህ መልስ፡፡ ሳይፈቀድልህ ወደቀጣዩ ፎቶ አትሂድ፡፡ በድንገት የግል እና ማንም እንዲያየው የማይፈልጉትን ፎቶ አይተህ ቅር ልታሰኛቸው ትችላለህ፡፡

14. አንድ የሥራ ባልደረባህ ሃኪም ጋር ቀጠሮ አለኝ ካለህ “ምንህን አሞህ ነው?” ብለህ አትጠይቅ፡፡ "ደህና እንደሆንክ ተስፋ አደርጋለሁ" ብቻ በል፡፡ የሰዎችን ግላዊነት አክብር፡፡

15. በመስሪያ ቤትህ ስራ አስፈጻሚም ይሁን ጽዳት ሰራተኛ ሁሉንም ሰው በአክብሮት ጥራ፡፡ ብዙዎች “ለሁሉ ትሁት ነው” የሚሉትን ሰው አብልጠው እንደሚወዱና እንደሚያቀርቡ እወቅ፡፡

16. ከሰው ጋር እያወራህ ሳለ በፍጹም ስልክህን አትመልከት፡፡ ይህ ለሰውየው ያለህን ንቀት ማሳያ ነውና ይቀየምሃል፡፡

17. ለሰው ምክር መስጠት ያለብህ ከጠየቀህ ወይም ከፈለገ ብቻ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች አብዝቶ የሚመክራቸ

06/11/2025

አስገራሚ የእንሰሳት እውነታዎች!

1. ቀበሮ በሂወት ዘመኑ አንዴ ብቻ ነው ፍቅረኛ ሚኖረው። ምን አልባት ሚስቱ ከሞተች ቀሪ ሂወቱን ብቻውን ነው የሚያሳልፈው! ምስኪን ታማኝ!!
2. የጂብ እድሜ ጣራ 80 ዓመት ነው!
3. አይጦች የራሳቸውን ያልሆነ ልጅ አጥብተው ያሳድጋሉ!
4. የወባ ትንኝ 47 ጥርሶች አላት!!!!
5. ፍየሎች ሴቷን ፋየል ለማማለል ሲሉ እርስበእርስ ይዋጋሉ!!!!!
6. ድመት በሂወት ዘመኗ እስከ 100 ግልገሎች መውለድ ትችላለች!!!!
7. እንደ ሰው ህልም ማየት ሚችለው አንስሳ ፈረስ ብቻ ነው!!!!
8. ዳክየ እንቁላል የምትጥለው ጧት ጧት ብቻ ነው!!!
9. የሌሊት ወፍ ጆረዋ ከተደፈነ መብረር አትችልም!!!!
10. ጊንጥ 12 አይኖች አላት!!!!
11. አዞ ምላሱን ወደውጭ ማውጣት አይችልም!!!
12. ሴት ካንጋሮ ከወንዱ ምትለየው በደረቷ ባለው ከረጢት ነው!!!
13. አይጥ ያለምግብ 14 ቀን መቆየት ትችላለች!!
14. አለም ላይ የመጀመሪያው ለማዳ እንስሳ ውሻ ነው!!
15 .የጊንጥ መርዝ ጊንጥን ሲገድል የእባብ መርዝ ግን እባብን አይገድልም!!!
16. በአንድ ጉንዳን መንጋ ውስጥ እስከ ግማሽ ሚሊየን ጉንዳኖች ሊኖሩ ይችላሉ!!!
17. ማንኛውም ስጋ በል እንስሳ በመብረቅ ተመትቶ የሞተን እንሰሳ አይበላም!!!
18. ቢራቢሮ 12, 000 አይኖች አሏት!!!
19. የመሬት ትል 5 ልቦች አሏት!!!

10/08/2025

*🥹❤‍🩹FIND YOUR COUNTRY😜😜

*1🇸🇸 2🇧🇱 3🇧🇶 4🇲🇶 5🇷🇪 6🇹🇫 7🇽🇰 8🇦🇨 9🇦🇩 10🇦🇪 11🇦🇫 12🇦🇬 13🇦🇮 14🇦🇱 15🇦🇲 16🇦🇴 17🇦🇶 18🇦🇷 19🇦🇸 20🇦🇺 21🇦🇼 22🇦🇽 23🇦🇿 24🇧🇦 25🇧🇧 26🇧🇩 27🇧🇪 28🇧🇫 29🇧🇬 30🇧🇭 31🇧🇮 32🇧🇯 33🇧🇲 34🇧🇳 35🇧🇴 36🇧🇷 37🇧🇸 38🇧🇹 39🇧🇼 40🇧🇾 41🇧🇿 42🇨🇦 43🇨🇨 44🇨🇩 45🇨🇫 46🇨🇬 47🇨🇭 48🇨🇮 49🇨🇰 50🇨🇱 51🇨🇲 52🇨🇳 53🇨🇴 54🇨🇷 55🇨🇺 56🇨🇻 57🇨🇼 58🇨🇽 59🇨🇾 60🇨🇿 61🇩🇪 62🇩🇯 63🇩🇰 64🇩🇲 65🇩🇴 66🇩🇿 67🇪🇨 68🇪🇪69🇪🇬 70🇪🇷 71🇪🇸 72🇪🇹 73🇪🇺 74🇫🇮 75🇫🇯 76🇫🇲 77🇫🇴 78🇫🇷 79🇬🇦 80🇬🇧 81🇬🇩 82🇬🇪 83🇬🇬 84🇬🇭 85🇬🇮 86🇬🇱 87🇬🇲 88🇬🇳 89🇬🇶 90🇬🇷 91🇬🇹 92🇬🇺 93🇬🇼 94🇬🇾 94🇭🇰 95🇭🇳 95🇭🇷 96🇭🇹 97🇭🇺 98🇮🇨 99🇮🇩 100🇮🇪 101🇮🇱 102🇮🇲 103🇮🇳 104🇮🇴 105🇮🇶 106🇮🇷 107🇮🇸 108🇮🇹 109🇯🇪 110🇯🇲 112🇯🇴 113🇯🇵 114🇰🇪 115🇰🇬 116🇰🇭 117🇰🇮 118🇰🇲 119🇰🇳 120🇰🇵 121🇰🇷 122🇰🇼 123🇰🇾 124🇰🇿 125🇱🇦 126🇱🇧 127🇱🇨 128🇱🇮129🇱🇰 130🇱🇷 131🇱🇸 132🇱🇹 133🇱🇺 134🇱🇻 135🇱🇾 136🇲🇦 137🇲🇨 138🇲🇩 139🇲🇪 140🇲🇬 141🇲🇭 142🇲🇭 143🇲🇰 144🇲🇱 145🇲🇲 146🇲🇳 147🇲🇴 148🇲🇵 149🇲🇷 150🇲🇸 151🇲🇹 152🇲🇺 153🇲🇻 154🇲🇼 155🇲🇽 156🇲🇾 157🇲🇿 158🇳🇦 159🇳🇪 160🇳🇫 161🇳🇬 162🇳🇮 163🇳🇱 164🇳🇴 165🇳🇵166🇳🇷 167🇳🇺 168🇳🇿 169🇴🇲 170🇵🇦 171🇵🇪 172🇵🇫 173🇵🇬 174🇵🇭 175🇵🇰 176🇵🇱 177🇵🇳 178🇵🇷179🇵🇸 180🇵🇹 181🇵🇼 182🇵🇾 183🇶🇦 184🇷🇴 185🇷🇸 186🇷🇺 187🇷🇼 189🇸🇦 190🇸🇧 191🇸🇨192🇸🇩193🇸🇪 194🇸🇬 195🇸🇭 196🇸🇮 197🇸🇰 198🇸🇱 199🇸🇲 200🇸🇳 201🇸🇴 202 🇸🇷 203🇸🇹 204🇸🇻 205🇸🇽 206🇸🇾 207🇸🇿 208🇹🇦 209🇹🇨 210🇹🇩 211🇹🇬 212🇹🇭 213🇹🇯 214🇹🇰 215🇹🇱 216🇹🇲 217🇹🇳 218🇹🇴 219🇹🇷 220🇹🇹 221🇹🇻 222🇹🇿 223🇺🇦 223🇺🇬 224🇺🇸 225🇺🇾 226🇺🇿 227🇻🇦 228🇻🇨 229🇻🇪 230🇻🇬 231🇻🇮 232🇻🇳 233🇻🇺 234🇼🇸 235🇾🇪 236🇿🇦 237🇿🇲 238🇿🇼*

23/01/2021
22/01/2021
23/12/2020

Design Fashion Show

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Aman design posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Aman design:

Share