Zamadkun hailu

Zamadkun hailu Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Zamadkun hailu, Shopping & retail, Adis ababa, Addis Ababa.

28/07/2023
      Friends
09/11/2022


Friends

03/06/2022

ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ሥፍራ:የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ መወለዱን የሰማይ መላዕክት መንጎቻቸውን ሲጠብቁ ለነበሩት እረኞች ያበሰሩበት ሥፍራ ነው::እግዚአብሔር አምላክ የተናቁትን ማክበር ልማዱ ነው::ንግሥና ይገባቸዋል ተብለው ከተሰለፉት የእሴይ ልጆች ይልቅ አይገባውም ተብሎ የተረሳውን ብላቴናው ዳዊትን መርጦ በንግሥና ቅባት ያከበረ እግዚአብሔር: በእቃና በእቃ መካከል ቁጭ ብሎ "እኔ የተናቅው ነገድ የነገደ ብንያም ወገን ነኝ :ማንም አይፈልገኝም "እያለ ሲያዝንና የተናቅውን አህያ ሊፈልግ ሰሄድ: በንግሥና ቅባት ቀብቶ ሳኦልን ያነገሰ እግዚአብሔር: ሰውን ለማዳን ሰው ሆኖ በቤተልሄም ዋሻ በተወለደ ጊዜም ምሥጢረ ልደቱን የገለጠው ዓለም ዝቅተኛ ሥፍራ ለምትሰጣቸው ለእረኞች ነው::አየህ ወዳጄ እግዚአብሔር ማለት እናውቃለን ለሚሉ ትዕቢተኞች የተሰወረ:አናውቅም ለሚሉ ትሁታን ግን የተብራራ አምላክ ነው::አየህ ወዳጄ ስለ እግዚአብሔር ማወቅና እግዚአብሔርን ማወቅ ይለያያል:ስለ እግዚአብሔር ማወቅ እውቀት ነው:እግዚአብሔርን ማወቅ ግን ሕይወት ነው::ስለ እግዚአብሔር በማወቅ ብቻ ቢሆን ኖሮ ከአይሁድ በተሻለ የሚያውቅ አልነበረም: ዕውቀታቸው ግን ላወቁት ጌታ አምነው ለመስገድ ሳይሆን ለሄሮድስ ጠቁመው ለማሳረድ ነው::ዕውቀታቸው ግን ቅዱስ መጽሐፍ ይዘው እርኩስ ተግባር ለመፈጸም ነው::ዕውቀታቸው ግን ለእግዚአብሔር ልጅ ቀንተው እግዚአብሔርን ለመስቀል ነው::ዕውቀታቸው ግን ህግን ለመግዧነት እንጂ ለመገዣነት አለመፈለግ ነው::ለዚህም ነው ጌታ በየዋህነትና በቅንነት መንጎቻቸውን ሲጠብቁ ለነበሩ እረኞች ብርሃነ ልደቱን የገለጠው:;

03/06/2022

ይህ የምትመለከቱት ሥፍራ ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ስፍራ ነው::ሰብአ ሰገልን እየመራ የመጣው ኮከብም እዚሁ ቦታ ላይ ነው የቆመው::የሰው ልጅ የእግዚአብሔር ልጅ እንዲሆን የእግዚአብሔር ልጅ የስው ልጅ ሆነ::በአውሮፕላን ውስጥ: በመርከብ ውስጥ:በባቡር ውስጥ:በእስፓርት ሜዳ ውስጥ:ወዘተ...ስለተወለዱ ሰዎች ሰምተናል:: ነገር ግን በበረት ስለተወለዱ ሰዎች አልሰማንም::በበረት መወለዱን የሰማነው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው::መሲሁ በቤተ መንግሥት ይወለዳል ሲባል በበረት ተወለደ:ወርቀዘቦና ግምጃ ይነጠፍለታል ሲባል በጨርቅ ተጠቀለለ:የቤተ መንግሥት ወይዛዝርት እልል ይሉለታል ሲባል እንስሳት እስትንፋሳቸውን ገበሩለት:መሲሁ መኳንንቶች ይከቡታል ሲባል እረኞች ከበቡት:መሲሁ አፈሙዝ ይዞ ወታደር አስከትሎ ይመጣል እስራኤላውያንንም ከሮማውያን ባርነት ነጻ ያወጣል ሲባል ከኃጢአት ባርነት ነጻ የሚያወጣ የዓለሙ ሁሉ ነጻ አውጪ ሆኖ መጣ::ሁሉ የሱ የሆነ ጌታ እራሱን ባዶ አድርጎ ለሌሎች ለመኖር ተገለጠ :በእውነት የጌታ ነገር ይደንቃል :: የተቀመጠበት አህያ የሰው:ፋሲካን ያደረገበት ቤት የሰው:የተቀበረበት መቃብር የሰው:ብቻ.... ከበረት እስከ መስቀል ሞት:ረጅሙን የፍቅር ፍለጋውን አድርጎ :ሰውን ሰው ያደረገ አምላክ የተመሰገነ ይሁን:

Address

Adis Ababa
Addis Ababa
ZAMADKUN

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zamadkun hailu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Zamadkun hailu:

Share