Kelifa ibn kedir

Kelifa ibn kedir Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kelifa ibn kedir, Shopping & retail, 0937450482, Addis Ababa.

28/04/2025

ከስልጤ ዞን አስተዳደር የተሰጠ የሀዘን መግለጫ

የቀድሞው የስልጤ ዞን አስተዳዳሪና በአሁኑ ሰዓት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ የነበሩት አቶ አሊ ከድር በዛሬው እለት ማለትም ሚያዚያ 20/2017 ኦሮሚያ ክልል ሞጆ የፍጥነት መንገድ ላይ በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል።

አቶ አሊ ከድር ከስልጤ ዞን ምስረታ በኋላ ዞኑን የመሩ ስምንተኛው አስተዳዳሪ የነበሩ ሲሆን በዚህም ከህዳር 2012 እስከ ሀምሌ 2016 ዞኑን በዋና አስተዳዳሪነት መምራታቸው ይታወቃል።

ከሀምሌ 2016 ጀምሮ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ የነበሩት አቶ አሊ በዛሬው እለት በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ህይወታቸው በማለፉ የዞኑ አስተዳዳር ጥልቅ ሀዘን የተሰማው መሆኑን እየገለጸ ለዞኑ ህዝብ፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ልባዊ መጽናናትን ይመኛል።

23/04/2025

ምግብ ሳይበሉ ለ3 ሳምንታት ገደል ውስጥ ወድቀው በህይወት የተገኙት ወይዘሮ ብዙዎችን አስገርመዋል ።

ከ3 ሳምንታት በፊት ወይዘሮ ባርመጌ በስልጤ ዞን ምእራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ሙጎ ቀበሌ ልዩ ስሙ ዶዮ ተብሎ በሚጠራ ሰፈር ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ከሌሊቱ 10 ሰአት ወጥተው ይጠፋሉ ።

ቤተሰቦቻቸው እና መላው የአከባቢው ህዝብ ወይዘሮ ባርመጌን እግሩ እስኪቀጥን ድረስ ቢፈልጋቸው ሊያገኛቸው አልቻለም ። ወይዘሮ ባርመጌ በቅርብ ጊዜ በቤተሰብ ውስጥ በተፈጠረ አለመግባባት ከልክ በላይ ተጨንቀው የነበረ ሲሆን ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ በመግባታቸው የአዕምሮ እክል እንደገጠማቸው የተነገረ ሲሆን በአከባቢው በሚገኙ ከተማዎች እና የገጠር ቀበሌዎች ያልተፈለጉበት አልነበረም ይሁን እንጂ ሊገኙ አልቻሉም ።

ሳይገኙ ከ3 ሳምንት መሻገሩ ተከትሎ ቤተሰቦቻቸው እና የአከባቢው ህብረተሰብ ይገኛሉ የሚል ተስፋ አልነበራቸውም ። ይሁን እንጂ ባልተሰበ መልኩ እረኞች ጦጣዎችን እያባረሩ በወደቁበት አገኙዋቸው ።

ወይዘሮ በርመጌ ሰውነታቸው ከስቶ በረሃብ ብዛት እራሳቸውን ስተው ወድቀው ተገኙ ይሁን እንጂ ህይወታቸው አላለፈም ነበረ ። ወይዘሮዋ በአሁኑ ሰአት በወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል

ትረፊ ያለት ነፍስ ይሉታል ይህ ነው!

08/04/2025

ከአዲስ አበባ - ቡታጅራ መስመር የደረሰን ጥቆማ!
የአዲስ አበባ-ቡኢ-ቡታጅራ መስመር የስርዐት አልበኞች መጫወቻ ሆኗል። 133ኪሎ ሜትር መንገድ ለመሄድ እንዴት ተብሎ ነው 500 ብር የሚከፈለው? አስባችሁታል 500 ብር።

ከታሪፍ ውጪ አልከፍልም ያለ ተሳፋሪ ገና ከመናኸሪያ ነግረው ስለሚጭኑ ካልተስማማህ ውረድ አልጭንም ይለዋል። ከፍሎ ሲያበቃ ትራፊክ ያለበት ሲደርስ ሲከስ እንኳን ሰሚ የለም።

በጣም አስገራሚው ነገር ደግሞ ተሳፋሪው መብቱን ላስከብር ቢል እራሱ እዛ መስመር ያለው የሾፌርና የትራፊክ ወዳጅነት ነው።

ከመሀል ቡታጅራ በጠራራ ፀሐይ 500 ብር ጭነው ሲወጡ ማንም ከልካይ የላቸውም በዛ ላይ በአንድ ዶልፊን 20 ሰው ነው የሚጭኑት "20" ሰው ይታያችሁ።

እንግዲህ በዚህ አይነት መንገድ ለተሳፋሪ ክብር በሚነካ መልኩ ወንበር ከሚችለው በላይ ጠጋ በል አምስት ሰው ነው የሚይዘው እየተባለ አልጠጋም ካለም ውረድና ሌላ ሰው ልጫንበት እየተባለ እየተንጓጠጠ እየተንገላታ ነው የሚጫነው።

እዛ መስመር ትራፊክ የሚቆመው ለዝርፊያ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ሾፌርና ረዳት ይሄ ሁሉ የተሳፋሪ ክብር እየነሱ ከታሪፍ በላይ እጥፍ እያስከፈሉና 5 እና 6 ሰው ትርፍ እየጫኑ ህዝቡን የሚያጉላሉት ያ ትርፍ የተጫነበት ብር ከትራፊኮች ጋር በጋራ ለመብላት ነው።

አንድ ሚኒባስ ከአዲስ አበባ ቡታጅራ እስኪደርስ በአማካይ ከ20 ጊዜ በላይ በትራፊክ ፖሊሶች እንዲቆም ይደረጋል ይሁን እንጅ ሰው በሰው ላይ ጭነው የሚጓዙ መኪኖች ትራፊክ ተብዬው ሾፌር ወርዶ ገንዘብ በወረቀት ከማስጨበጥ ውጭ ምንም አይነት የትራፊክ ቁጥጥር አይደረግም። እዛ መስመር ትራፊ መለዮ ለብሶ የሚቆመው ከእያንዳንዱ መኪና ብር ለመቀበል ብቻ ነው።

ይሄ ደግሞ ለመኪኖች እንዳሻቸው ሰው በሰው ጠቅጥቀው 100 እና 50 ብር እያስጨበጡ ማለፍ ቀላል ሆኖላቸዋል።

በዛ ላይ ምንም ለማይሰሩት ነገር ተሳፋሪው ይሄ ሁሉ እንግልትና የኪስ ብዝበዛ ከደረሰበት በኋላ በመለዮ ሰበብ እያስቆሙ በጊዜ ቤቱ እንዳይገባ እያስቆሙ የሚያንገላቱት ነገርስ? መንግስት ሰራ አጥቶላቸው ይሁን አላውቅም እንደ አሸን በየጥጋጥጉ ለዝርፊያ የሚያሰማራቸው።

ሾፌርና ረዳት ሲጠየቁ ትርፍ ካልጫንንና ገንዘብ ካልሰጠን ትራፊክ አያሰራንም ነው እያሉ ያሉት።

ለመሆኑ እነዚህን ኪሳቸው የደለበ ትራፊክ ተብዬዎች መቼ ነው በቃኝ የሚሉት? መንግስት ያንን መስመር ሰርዐት ማስያዝ እንዴት ተሳነው? እናውቃለን በሁለት የተለያዩ ክልል ትራፊኮች እንደሚተዳደር አንደኛው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ስር ነው። በሁለቱም በኩል ያሉ የትራፊክ ፖሊሶች ተመሳሳይ የዝርፊያ ሰራ ነው የተያያዙት።

ህዝቡን ማን ይታደገው? ታሪፍ በሰው ልክ ከአዲስ አበባ ቡታጅራ 268 ብር ሆኖ እያለ 500ብር መንግስትና ህግ ባለበት ሀገር? ያሳዝናል🤔

ለዚም መፍትሔ ይፈልጋል ህዝቡ

07/03/2025

ለትዉልዱ ቂም አናዉርስ!

የቤት መፍረስ የቤተሰብና የማህበረሰብ መፍረስ መሆኑ አስረጂ አያስፈልገዉም። ዜጎች ሕገወጥ ከሆኑ ሕጋዊ ማድረግ ሞራላዊ ልዕልና ነዉ። በሕገ ወጥ ሽፋን ቤቶችን አፍርሶ ማባረር ለትዉልድ መጥፎ ነዉ።

ቤት የፈረሰባቸዉ እናትና አባት ለልጆቻቸው ምን የሚሏቸዉ ይመስላችኀል? "ሕገ ወጥ ስለሆንን ፈረሰብን?" እንዲህ ይሏችኀል? በፍጹም! እነ እከሌ እየተባለ በሕፃን ልጅ አዕምሮ ላይ ጥላቻና ቂም እንዲታተም ይደረጋል። ጊዜ በሰዎች ላይ ተለዋዋጭ መሆኑ የተፈጥሮ ሕግ ነዉ። ከዚያ አንደኛዉ ትዉልድ በሌላኛዉ ላይ ቂሙን እንዲወጣ በር እየከፈትን መሆኑ እንዴት ጠፋን?

ቂምና ጥላቻ እንዳይጎለብትና ለትዉልድ እንዳይተላለፍ በብዙ ሁኔታዎች መስራት ይገባናል። የተበደለን በመካስ፣ የተጣመመን በማቅናት፣ የተጎዳን በማከም...የፍቅርና የሕብረትን ድልድይ መገንባት የሁላችንም ድርሻ ሊሆን ይገባል። ከማፍረስ ይልቅ ሕጋዊ ማድረግ ይቅደም!

30/10/2024

የእምነቷን ትዕዛዝ አደቡን አክብራ ትምህርቷን ብትማር ኒቃቡ ከራሷ አስራ ምኑ ላይ ነው ነውሩ!
ምንድነው ችግሩ?!
በሷ ኒቃብ ማጥለቅ ተማሪው ታወከ? ወይስ መምህሩ?
እስኪ የሚያሳምን አንድ ምክንያት ጥሩ!
ከሌላችሁ በቀር ሌላ ሴራና እቅድ ኒቃቡ ብቻውን በፍፁም አይችልም ትምህርትን ሊያሳግድ።

ለሚመለከተው አድርሱልኝ

16/06/2023

🚩ተመሳሳይ ፆታ ጋብቻና መዘዙ ❗️
🇺🇸 በአሜሪካ እድሜ ጠገቡ ቸርች በመብረቅ ተመታ

በአሜሪካ ሀገር ቦስተን ከተማ የ116 ዓመት እድሜ ያለው " first Congressional Church of Spencer" የሚባለው ቸርች በመብረቅ ተመቶ ሙሉ ለሙሉ ወደመ

ይህ ቸርች በመብረቅ ሲመታ ምንም አይነት ሰው ውስጥ ያልነበረ ሲሆን

ቸርቹ ግን ሙሉ ለሙሉ ወድሟል

#ቸርቹ

* የተመሳሳይ ፃታ መጋባትን የሚደግፍ ና
* ብዙ ጊዜ በፌስቡክ ፔጁም ድጋፍ የሚሰጥ
ቸርች እንደሆነ ታውቋል::

ቸርቹ በመብረቅ ሲመታ

ሌሎች ቸርቹ አጠገብ ያሉ ፎቆ ና ቤቶች ግን ምንም ችግር እንዳልገጥማቸውም ታውቋል::

እስቲ የተሰማችሁን ብቻ ኮሜንት ???

Justice is primary concepts of fairness     Fitih legunchre muslim ehtoch
28/04/2023

Justice is primary concepts of fairness
Fitih legunchre muslim ehtoch

Address

0937450482
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kelifa ibn kedir posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share