25/05/2026
የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት አስቸኳይ ስብሰባ በማካሄድ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ !
/ግንቦት 17/2018 ዓ.ም/ የባሕርዳር ከተማ አስተዳድር ከንቲባ ኮሚቴ ግንቦት 17/2018 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
ከእነዚህ ውሣኔዎች አንዱ የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራት የተመለከተ ነው። ቅድመ ሁኔታዎን አሟልተው የቅድመ ቁጠባ ያጠናቀቁ እና እውቅና የተሰጣቸው 789 የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራት የመሬት ካሳ ክፍያ በተመለከተ ውሳኔ አስተላልፏል።
አንድ በቤት ማህበር የተደራጀ አባል 220,000 ( ሁለት መቶ ሀያ ሽህ ብር ) ለካሣ ክፍያ መክፈል የሚጠበቅበት መሆኑን ወስኗል። ነገር ግን የከተማ አስተዳሩ ከንቲባ ኮሚቴ የዝቅተኛና የመካከለኛ ነዋሪዎችን የመቆጠብ አቅም ግምት ውስጥ በማስገባት እንዲሁም ዜጎችን የቤት ማህበር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በማሰብ ለቅድመ ቁጠባ የከፈሉትን 120,000 (አንድ መቶ ሀያ ሽህ ብር ) የካሳ ክፍያው አካል እንዲሆን በሙሉ ድምጽ ተወስኗል።
በመሆኑም 120,000. 00 (አንድ መቶ ሃያ ሸህ ብር) የቆጠበ የማህበር አባል ለካሣ ክፍያ የሚጠበቅበት ተጨማሪውን 100,000.00 (አንድ መቶ ሸህ ብር) በባንክ እንዲከፍል ተደርጎ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ተጠቃሚ ይሆናል በማለት ከንቲባ ኮሚቴው ኃላፊነት የተሞላበት ፍፁም ህዝባዊ ወገንተኝነቱን በተግባር ያርጋገጠ ውሳኔ አስተላልፏል
በመጨረሻም ከንቲባ ከሚቴው ይህ ውሣኔ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ የየማህበሩ አባላት በተፈቀደው አጭር ቀናት ከላይ የተገለፀውን ክፍያ በባንክ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ።
ለእድሉ ተጠቃሚዎች በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ!!!