
01/30/2022
ሰበር - ያልተጠበቀው ሆኖል ግራ አጋቢ ነው | ህዝቡ አደባባይ ወጣ ሰላማዊ ሰልፍ | የኮንደሚኒየም ጉዳይ
Join this channel to get access to perks:https://www.youtube.com/channel/UC3bEbnuoR3UPeh1xYQyMviw/joinWelcome to my channel I'm Abel Birhanu from Ethiopia i...
Daily Ethiopian news shared from all media outlets. One Stop Shop for all your wireless, computers and electronics needs
Operating as usual
Join this channel to get access to perks:https://www.youtube.com/channel/UC3bEbnuoR3UPeh1xYQyMviw/joinWelcome to my channel I'm Abel Birhanu from Ethiopia i...
Part 1 of 3: the role of economic policies and international institutions in the 'underdevelopment' of Africa.Howard Nicholas is senior lecturer of economics...
The Weeknd runs pop music. There has been a lot of noise in recent weeks surrounding The Weeknd's most recent album Dawn FM. Released on Jan. 7, the album was wildly successful on streaming, but could not secure the No. 1 spot on the Billboard 200 chart, losing a nail-biter to Gunna's DS4EVER. The W...
ጠላት አፈረ በሰላም ተጠናቀቀ II ግብጽ የላከችው ቢሊዮን ዶላር በኤርትራ ታገተ
Photos from ጎልጉል Ethiopian Daily News's post
Join this channel to get access to perks:https://www.youtube.com/channel/UC3bEbnuoR3UPeh1xYQyMviw/joinWelcome to my channel I'm Abel Birhanu from Ethiopia i...
እንቶ ፈንቶ
ደጅ አዝማቹ በዝቶ
ዘጠኝ እልፍኝ ሰርቶ
ቀዳሽ እና አራሽ አዝማሪና ተኳሽ
እዛም እዚም ነጋሽ ★★
ምስለኔው ሲጠፋ
አንዱ እየነቀለ አንዱ እየገፋ ★
ጭቃ ሽሙ ሆነ ቀዶ የሚሰፋ
FIND OUT THE MISSING NUMBER
።።። ።። የደም ገንቦ።።።።።።።
በአንድ በሬ ስቦ ,,,,
በ አንድ እጅ አጨብጭቦ ,,
። ወ ስብአት ለኪ....ኪዳኑን አቅርቦ
የደረቀን ላንቃ በዜማ አርጥቦ
የልጅነት መልኬ ገርጥቶ ወይቦ ,,,
። ዛሬም ልብ የለኝም
።። አመንኩሽ ደግሜ.
በይሉኝታ ግዚት አፌን ተለጉሜ።
ፍቅርሽ ነው የጎዳኝ =ፈትጎ ያሰጣኝ
አልቆረቆረኝም አልጋሽ ዙሪያው ረግቦ ...
"ደም ግባትሽ ይሆን ? አንቺ የደም ገንቦ "
ምነው የኔ እና አንቺ =ነገሩ ፈጠጠ ,,,,,
አሁንስ ታከተኝ ,,,,,,,
እንደ ቄብ እንቁላል ወርዶ በፈረጠ ፣፣
ምላስ ከሚገርፈን እያገላበጠ !!!
የአክሱም የዛጉዬ የዳሞት አሻራ
የፈለገ ግዮን የሰው ዘር አዝመራ ,,,,
ጎንደር አባጃሌ ,,,,ወሎ ገራገሩ
የዜማ መቁጠርያ ክታብ ነው ምስጢሩ
ሸዋ ሰርገኛ ነው አይቆለፍ በሩ ,,,,,,,
ቀብቶ ያወጣል ከልፍኝ ከመንበሩ ,,
የተያዘው ቅኝት ሎሚን መወርወሩ
ሎሚ ተራ ተራ ሎሚ ተራ ተራ ,,,,,,,
እኔስ ይበቃኛል ልቤን አልሰጥሽም
"አምኜሽ ባደራ "
ይረክብሽ እንጂ ፍቅርን የተራበ ደግሞ ባለሳምንት በተራ በተራ,
ምነው አለሰማ አለሽኝ ብጣራ ብጣራ ፤፤
ያንችስ አይደለም ወይ ??። ጎጆአችን የጋራ።
Ethiopia News - Feta Daily News | Ethiopian Airlines | Abiy Ahmed Ali | Tewelede Gebremariam | EU on Ethiopia | Sileshi Bekele Tigrai | general Abebaw Tades...
Zehabesha | Ethiopia News | Zehabesha 4 | Zehabesha Extra | Zehabesha Official Zehabesha 4 News goes deep beneath the surface, providing the key stories fro...
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር የስልክ ውይይት አደረጉ
ጥር 2 ቀን 2014 (ኢዜአ)ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ግልፅ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ።
ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በተለይም በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ጠቁመዋል።
ውይይቱ ሁለቱ አገራት በጋራ መከባበር ላይ የተመሰረተ ገንቢ ተሳትፎ በማድረግ ትብብራቸውን ለማጠናከር ትልቅ ጥቅም እንዳለው "ሁለታችንም ተስማምተናል "ብለዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
መረጃዎቻችንን በዩቲዩብ፡- https://www.youtube.com/channel/UCSjaw-eGJSkvcXHyTpQyT1Q
በቴሌግራም፡- https://t.me/EthiopianNewsA
በድረገጽ፡- https://www.ena.et/
በትዊተር፡- https://twitter.com/ethiopiannewsa?lang=en
በአፋን ኦሮሞ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/TajaajilaOduuItoophiyaa/ አድራሻዎቻችን ያገኟቸዋል።
ሰበር ዜና
መንግስት አቶ ስብሃት ነጋ፣ ጃዋር መሐመድና እስክንድር ነጋን ጨምሮ እሥረኞችን ዛሬ በምሕረት ከእሥር ፈታ
ታህሳስ 29 ቀን 2014 (ኢዜአ) መንግስት አቶ ስብሃት ነጋ፣ ጃዋር መሐመድና እስክንድር ነጋን ጨምሮ እሥረኞችን ዛሬ በምሕረት ከእሥር መፍታቱ ተገለጸ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ባወጣው መግለጫ “በሕዝብ ይሁንታ የተመረጠ መንግሥት፣ አካታች ሀገራዊ ምክክር እንዲሳካ ከሚጠበቅበት ሞራላዊ ግዴታዎች አንዱ ምሕረት በመሆኑ ለተሻለ ፖለቲካዊ ምኅዳር ሲባል የተወሰኑ እሥረኞችን መንግሥት ዛሬ በምሕረት ከእሥር ፈትቷል” ብሏል።
ምሕረቱ ከዚህ በፊት በተፈጸመ ጥፋት የታሠሩትንም ሆነ በቅርቡ ከተፈጠረው ጦርነት ጋር በተያያዘ የታሠሩትን እንደሚጨምር ጠቁሟል።
“መንግሥት ይሄንን ውሳኔ ሲወስን ዓላማው የኢትዮጵያን ችግሮች ሰላማዊ በሆነ፣ ከእልክና ከመጠፋፋት በራቀ ሁኔታ፣ በሀገራዊ ምክክር በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል መንገድ ለመክፈት ነው” ብሏል።
በተጨማሪም የሕዝብን ጥያቄዎች ከግምት በማስገባትና ምንጊዜም ለሰላማዊ ፖለቲካ መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት ለማሳየት እንደሆነ ገልጿል።
በዚህም መሰረት ከእሥር በምሕረት እንዲፈቱ የተወሰነላቸው
1. አቶ ስብሐት ነጋ
2. ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ
3. አቶ ዓባይ ወልዱ
4. አቶ አባዲ ዘሙ
5. ወይዘሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር
6. ወ/ሮ ኪሮስ ሐጎስ
7. አቶ ጁሐር መሐመድና በእርሱ መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ
8. አቶ እስክንድር ነጋና በእርሱ መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ ከእስር መለቀቃቸው ተገልጿል።
ሰበር ዜና
ኢትዮጵያ ለዘላቂ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት የትኛውንም መሥዋዕትነት ትከፍላለች
የኢትዮጵያ ችግሮችን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ መፍታት እንደሚገባ መንግሥት በጽኑ ያምናል። ይሄንንም ከለውጡ መጀመሪያ ጀምሮ በግልጽ ሲገልጥ ቆይቷል፡፡ አንድን ሕመም ለማዳን እንደሚወሰዱ የተለያዩ መድኃኒቶች፣ አንድን ሀገራዊ ችግርም በሁሉም የመፍትሔ መንገዶች እንዳይመለሱ አድርጎ መፍታት ይገባል። ኢትዮጵያ ከየአቅጣጫው የተከፈቱባትን ጥቃት በጀግኖች ልጆቿ እየመከተች ነው።
በዓለም አቀፍ መድረክ ሊገዳደሩን ያሰቡትን በሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ድምጽና ዲፕሎማሲያዊ ተጋድሎ ረትተናል። ዘመን ተሻጋሪ ፖለቲካዊ ችግሮችን በአካታች ሀገራዊ ምክክር ለመፍታት እንዲቻል መንግሥት ገለልተኛ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እንዲቋቋም የሚጠበቅበትን እየተወጣ ይገኛል። በሁሉም መስክ ኢትዮጵያ እያሸነፈች የለውጥ ጉዞዋን እንደቀጠለች ነው፡፡
በሕዝብ ይሁንታ የተመረጠ መንግሥት፣ አካታች ሀገራዊ ምክክር እንዲሳካ ከሚጠበቅበት ሞራላዊ ግዴታዎች አንዱ ምሕረት በመሆኑ ለተሻለ ፖለቲካዊ ምኅዳር ሲባል የተወሰኑ እሥረኞችን መንግሥት ዛሬ በምሕረት ከእሥር ፈትቷል። ይህ ምሕረት ከዚህ በፊት በተፈጸመ ጥፋት የታሠሩትንም ሆነ በቅርቡ ከተፈጠረው ጦርነት ጋር በተያያዘ የታሠሩትን ይጨምራል። መንግሥት ይሄንን ውሳኔ ሲወስን ዓላማው የኢትዮጵያን ችግሮች ሰላማዊ በሆነ፣ ከእልክና ከመጠፋፋት በራቀ ሁኔታ፣ በሀገራዊ ምክክር በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል መንገድ ለመክፈት ነው። በተጨማሪም የሕዝብን ጥያቄዎች ከግምት በማስገባትና ምንጊዜም ለሰላማዊ ፖለቲካ መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት ለማሳየት ነው።
የፖለቲካ ምኅዳሩን ለማስፋትና ለአካታች ሀገራዊ ምክክር ሲል መንግሥት በምሕረት የፈታቸው አካላትም፣ ካለፈው የጥፋት መንገድ ተምረው፣ የተሻለ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ አስተዋጽዖ በማድረግ፣ ሀገራቸውንና ሕዝባቸዉን ይክሳሉ ብሎ መንግሥት ያምናል። ከግጭትና ከከፋፋይ መንገዶች ይልቅ ለሰላማዊ ፖለቲካ የበኩላቸውን እንደሚያደርጉም መንግሥት ተስፋ ያደርጋል። መንግሥት ይሄንን ውሳኔ በአንድ በኩል ሲወስን በሌላ በኩል ደግሞ ያለፉ ዋጋ አስከፋይና ግጭት ጠማቂ አካሄዶች በጭራሽ እንዲደገሙ አይፈቅድም። ፍትሕና ምሕረትም በየሚዛናቸው እንዲጓዙ መንግሥት ይፈልጋል። በሂደቱ የተጎዱ ወገኖች እንደሚኖሩ መንግሥት ያምናል። የእነዚህ ተጎጂ ዜጎች ቁስል በሽግግር ፍትሕ የሚካስ ይሆናል። እነዚህ ተጎጂ ዜጎች ሕመማቸው ለኢትዮጵያ የከፈሉት ዋጋ በመሆኑ ሸክማቸውን መንግሥትና ሕዝብ በጋራ እንሸከምላቸዋለን። ከእሥር የተፈቱ ወገኖችም ጭምር የተጎጂዎችን ሸክም የመሸከም ዕዳ አለባቸው።
መንግሥት ይሄንን ውሳኔ የወሰነው በዋናነት ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ነው። ኢትዮጵያ የመሐሪነቷን ዋጋ እንድታገኝ፣ የኢትዮጵያን ምሕረት ያገኙት አካላት፣ ምሕረቱን ያገኙበትን ዋጋ ይረዱታል ብሎ መንግሥት ያምናል። የኢትዮጵያ ነባር ችግሮች የሚፈቱት በሰላማዊ ፖለቲካዊ ተዋሥኦ፣ በሆደ ሰፊነትና አዎንታዊ ሚናን በመጫወት ነው። ለዚህ ደግሞ መንግሥት ዋጋ ከፍሎም ቢሆን ቅድምናውን ይወስዳል። ዛሬም ለዘላቂ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትና ሰላም ሲል መንግሥት የተወሰኑ እሥረኞችን በምሕረት ፈትቷል፡፡
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Zehabesha | Ethiopia News | Zehabesha 4 | Zehabesha Extra | Lalibela | Azeb Mesfin Shukshukta | Abebe Balcha Shukshukta | TPLF | Tekeste sebhat Nega | Gener...
Daniel Tessema Organizer & Social Justice Advocate speaks from Ethiopia
Daniel Kore Organizer & Social Justice Advocate speaks from Ethiopia
Photos from Abiy Ahmed Ali's post
ከ4ወራት ከ16 ቀናት መከራ በኋላ ከአሸባሪዎች ነጻ የወጣችው ላሊበላ የገና ዋዜማ ሕይወት
በፎቶ
ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
መረጃዎቻችንን በዩቲዩብ፡- https://www.youtube.com/channel/UCSjaw-eGJSkvcXHyTpQyT1Q
በቴሌግራም፡- https://t.me/EthiopianNewsA
በድረገጽ፡- https://www.ena.et/
በትዊተር፡- https://twitter.com/ethiopiannewsa?lang=en
በአፋን ኦሮሞ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/TajaajilaOduuItoophiyaa/ አድራሻዎቻችን ያገኟቸዋል።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋን ዪ የአፍሪካ ጉብኝት ቀጥሏል
ታኅሣሥ 28 ቀን 2014 (ኢዜአ) የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋን ዪ የአፍሪካ ጉብኝት እንደቀጠለ ነው።
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኤርትራ አስመራ ያካሄዱት የሁለት ቀናት ጉብኝት አጠናቀው ትናንት ማምሻውን ናይሮቢ ኬንያ ገብተዋል።
ዋን ዪ በአስመራ ቆይታቸው ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዑስማን ሣልህ ጋር በሁለትዮሽ፣ ስትራቴጂያዊ አጋርነት እና በቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አካሂደዋል።
ሁለቱ አገራት የምጽዋ እና ዓሰብ ወደቦችን ለማልማት እንዲሁም በማዕድን ዘርፍ ልማት በጋራ ለመስራት ከሥምምነት ላይ ደርሰዋል።
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋን ዪ በኤርትራ ላይ የአንድ ወገን እና ‘ሕገ-ወጥ’ ያሉትን ማዕቀብ ቻይና እንደማትቀበል አረጋግጠዋል።
በተጨማሪም ቻይና የ15 ነጥብ 7 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ለኤርትራ እንደምታደርግ አስታውቀዋል።
በጉብኝታቸው ማብቂያ ላይም ከኤርትራው አቻቸው ጋር በመሆን ባለ አራት ነጥብ የጋራ የአቋም መግለጫ ይፋ አድርገዋል።
በዚህም ኤርትራና ቻይና ስትራቴጂያዊ አጋርነታቸውን በቀጣይ ለማጠናከር መስማማታቸውን ገልጸዋል።
በዴሞክራሲ እና በሰብዓዊ መብት ሰበብ በሌሎች አገራት የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚደረገውን ጣልቃገብነትና ጠቅላይነትን እንደሚቃወሙም ይፋ አድርገዋል።
ሁለቱም ወገኖች በቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም እና በስትራቴጂያዊ አጋርነት ማዕቀፍ ዙሪያ በተለያዩ መስኮች በጋራ ለመስራትም ተስማምተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋን ዪ የኤርትራ ቆይታቸውን አጠናቀው ትናንት ማምሻውን ናይሮቢ ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በኬንያ አቻቸው ሬይሼል ኦማሞ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በናይሮቢ ቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር እንደሚነጋገሩ የተገለጸ ሲሆን ጉብኝታቸውም የሁለቱን አገራት ግንኙነት ይበልጥ ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል።
በኤርትራ የተጀመረው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሦስት የአፍሪካ አገራት ጉብኝት ወደ ኮሞሮስ በማቅናት እንደሚጠናቀቅ ከዘስታንዳርድና ሲጂቲኤን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በቅርቡ የሴኔጋል መዲና ዳካር ባስተናገደችው 8ኛው የቻይና-አፍሪካ የትብብር ፎረም (ፎካክ) ጉባዔ ተሳትፎ መልስ ዋን ዪ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸው ይታወሳል።
በአዲስ አበባ ቆይታቸውም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በሁለትዮሽና ሌሎች የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ መነጋገራቸው ይታወቃል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
መረጃዎቻችንን በዩቲዩብ፡- https://www.youtube.com/channel/UCSjaw-eGJSkvcXHyTpQyT1Q
በቴሌግራም፡- https://t.me/EthiopianNewsA
በድረገጽ፡- https://www.ena.et/
በትዊተር፡- https://twitter.com/ethiopiannewsa?lang=en
በአፋን ኦሮሞ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/TajaajilaOduuItoophiyaa/ አድራሻዎቻችን ያገኟቸዋል።
"የዘንድሮውን የልደት በዓል የምናከብረው የመከራችን ዘመን እያከተመ፣ የችግራችን ቋጠሮ እየተፈታ፣ የሰቆቃችን ምንጭ ላይመለስ እየደረቀ ባለበት ወቅት ነው"-ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ
የዘንድሮውን የልደት በዓል የምናከብረው የመከራችን ዘመን እያከተመ፣ የችግራችን ቋጠሮ እየተፈታ፣ የሰቆቃችን ምንጭ ላይመለስ እየደረቀ ባለበት ወቅት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፤
-----------------------------------------------
እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!
የዘንድሮውን የልደት በዓል የምናከብረው የመከራችን ዘመን እያከተመ፣ የችግራችን ቋጠሮ እየተፈታ፣ የሰቆቃችን ምንጭ ላይመለስ እየደረቀ ባለበት ወቅት ነው። መከራችንን ከኋላችን ጥለን ተስፋችንን አሻግረን እያየን የምናከብረው በዓል ነው።
የክርስቶስ ልደት የአዲስ ተስፋ ጅማሬ የብሩህ ዘመን ማብሠሪያ ነው። የጭንቁ ጊዜ እያለፈ መሆኑ፣ የመከራው ዘመን እየተገባደደ መምጣቱ፣ ጨለማው በብርሃን መሸነፉ፣ የኃጢአት እሥር አብቅቶ ነጻነት መቅረቡ የተበሠረበት ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወለዱ በፊት የነበረው ዘመን ዓመተ ፍዳ ነበር። ሰው የፈጣሪውን መመሪያ ተላልፎ የተከለከለውን በመፈጸሙ ምክንያት፣ ርግማን ወርዶበት ከገነት ተባርሮ የኖራቸው እነዚያ ዘመናት፣ በድቅድቅ ጨለማ የተሞሉ ነበሩ። ጊዜው ደርሶ ክርስቶስ በቤተልሔም ሲወለድ፣ የኩነኔው ዘመን በሥርየት ተለውጦ የምሕረት ዘመን ተብሏል።
የሰው ልጅ ድኅነት በጽንሰት ተጀመረ፣ በልደት ተበሠረ፣ በስቅለት ተፈጸመ፤ በትንሣኤ ተደመደመ። እያንዳንዱ ምእራፍ በፈተናና በደስታ ነበር የታለፈው። የክርስቶስ ልደት የምሕረት ጊዜ መቅረቡን እንጂ ሁሉም ነገር መጠናቀቁን አላበሠረንም። ዕለተ ስቅለቱ ደርሶ አዳም ከዲያብሎስ ባርነት፣ ከኃጢአት ቀንበር ነጻ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ፣ በመንገዱ ብዙ ውጣ ውረዶች አጋጥመዋል። የሄሮድስ የሞት ዐዋጅ፣ ስደት፣ እንግልት፣ ረሃብ፣ ጥማት፣ ነበረ።
ጠላታችን ዲያብሎስ በማይታክት ተንኮሉ አዳምን እስከ መጨረሻው ከፈጣሪው አቆራርጦ ለማኖር ከጽንሰቱ እስከ ስቅለቱ ያልፈነቀለው ድንጋይ፣ ያልፈጸመው ሤራ አልነበረም። ጭፍራዎቹን አሠማርቶ ብዙዎች ከእውነት ጋር እንዳይቆሙ አድርጓል። ሐሰትን እየፈበረከ የክርስቶስን ስም እንዲያጠፉ አድርጓል። ብዙዎች ወደ ክርስቶስ እንዳይሄዱ ተከታዮቹን አስፈራርተዋል። ወደ ክርስቶስ የመጡትን ትታችሁ ውጡ ብለዋል። ሐዋርያትን ጭምር በገንዘብ አስክደዋል። የውጭ ጠላቶች ሮማውያን፣ ከውስጥ ባንዳዎች አይሁድ ጋር አንድ ሆነው ክርስቶስን አሳድደዋል።
የኢትዮጵያ ጠላቶችም ሊወለድ ያለውን ተስፋችንን ሊያጨነግፉ ለዓመታት ታግለዋል። ሲጸነስ ሊያጨናግፉት ሞክረው ነበር። መወለዱን ሲያውቁ ያልፈጸሙት የግፍ ዓይነት የለም። ግጭቶችን እየጠመቁ ሕዝብን ከሕዝብ ሲያጋጩ፣ በየደረሱበት ንጹሐንን ሲያፈናቅሉና ከሕጻናት እስከ አዛውንት ያገኙትን ሲያሰቃዩና በጭካኔ ሲገድሉ ነበር። የሀገራችን የመዳንዋ ጊዜ የማይመጣ እስኪመስል ድረስ መከራችን በዝቶ ታይቷል። እንደ ሄሮድስ ያሉ አበጋዞች ብሩህ ተስፋችንን ሊያጨልሙ ባለ በሌለ ጉልበታቸው ታግለዋል። አንድነታችንን ሊንዱ ተባብረዋል፤ ሀገራችንን ሊያፈርሱ እስከ ሲኦል ለመውረድ ምለዋል። ኢትዮጵያ በዚያ ሁሉ መከራ ውስጥ አልፋ እዚህ ደርሳለች። የተረገዘው የለውጥ ጽንስ ተወልዶ እያደገ ነው። ኢትዮጵያም በሚወረወሩባት ፍላጻዎች ድልድዮችን እየገነባች፣ ተስፋዋን ለመፈጸም ከመጓዝ ያገዳት የለም።
ውድ ወገኖቼ፣
ሰው በሕይወቱ እጅግ ወሳኝ ከሆኑ ቀናት መካከል ሁለቱ፣ የተወለደበትና ለምን እንደተወለደ ያወቀበት ቀናት ናቸው ይባላል። ሁላችንም ያለ አንድ ዓላማ አልተፈጠርንም። አንቱ የምንላቸው ቀደምቶቻችን አንቱ ያስባላቸው ጉዳይ ለምን እንደተወለዱ ማወቃቸው ነው። ኢትዮጵያዊ ሆነን መወለዳችን ያለ ምክንያት እንዳልሆነ አስበን ሀገራችንን ከጥገኝነት የሚያላቅቅ፣ ወገናችንን ከድህነት አዙሪት የሚገላግል፣ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና ጎዳና የሚያስገባ፣ ኢትዮጵያ ራሷን በሁሉም ነገር ችላ እንድትቆም የሚያደርግ፣ አንድ ቁም ነገር ሠርተን ማለፍ አለብን።
ለዚህ ደግሞ ከአሁን የተሻለ ጊዜ የለም። አሁን የምንገኝበት ወቅት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሊሸጋገር የሚችል አንጸባራቂ ገድል የሚሠራበት፣ በኩራት የሚነገር ታሪክ የሚጻፍበት ወሳኝ ወቅት ነው።
የኢትዮጵያ ቀን ሊነጋ ጽልመቱን ሰንጥቆ ጉዞ ጀምሯል፣ ጀንበሯ ደምቃ ልትወጣ ከጨለማው ጋር ትግል ላይ ናት። በዚህ ወሳኝ ወቅት ሁላችንም ዐቅማችን የፈቀደውን መሥራት ከቻልን፣ ያለ ጥርጥር የኢትዮጵያ ነገ ብሩህ ይሆናል፤ የመከራ ዘመንዋ እስከ ወዲያኛው ይሸኛል። ኢትዮጵያም የማትደፈር፣ የምትታፈር ሀገር ሆና በዐለት ላይ ትቆማለች።
ኢትዮጵያን ለማገልገል ስንነሣ ልብ ማለት የሚገባን ነገር አለ። የሰነቅነው ዓላማ የቱንም ያህል የገዘፈና የተቀደሰ ቢሆን፣ ትኅትና ካልታከለበት ትርጉም የለውም። ታላላቅ ግቦች ፍጻሜያቸው ብቻ ሳይሆን አፈጻጸማቸውም ታላቅና አስደናቂ ነው። የክርስቶስ ልደትም የሚያስተምረን ይሄን ነው። ዓለምን ለማዳን እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ለታላቅ ዓላማ ሲልከው፣ ከታላላቅ ሰዎች ይልቅ እረኞችን፤ ከታዋቂዎች ይልቅ ከብቶችን፤ በጌጣጌጥ ከተንቆጠቆጡ እልፍኞችና ቤተ መንግሥቶች ይልቅ በረትን መረጠ። ዓለምን ማዳንን ያህል ታላቅ ሥራ በትኅትና ነው የተፈጸመው። ታላላቅ ግቦች በትኅትና ተጀምረው፣ በትኅትና የሚጠናቀቁ መሆናቸውን መድኃኔዓለም ክርስቶስ አስተምሮናል።
ዛሬ በኃይልና በትዕቢት ተወጥረን የምንጀምራቸውና “በእኔ ዐውቅልሃለሁ” ስሜት ተኮፍሰን የምንሠራቸው ሥራዎች ዘላቂ እድሜ ሊኖራቸው አይችልም። ከድሃው ሕዝብ ርቀን፣ በጌጣጌጥ በተንቆጠቆጡ ቢሮዎች ውስጥ ተቆልፈን፣ በዘመናዊ መኪኖች ተንፈላስሰን የምንወጥናቸው ዕቅዶች ቢተገበሩም ቆይተው ይፈርሳሉ። በተቃራኒው ወደ ታች ወርደን ከሕዝቡ ጋር የነደፍናቸው ግቦች፣ ጀምረን ባንጨርሳቸው እንኳን፣ ትውልድ ተረክቦ ከዳር ያደርሳቸዋል።
ሌላው የልደት በዓል በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ የእርቅ ምልክት ተደርጎም ይታሰባል። በፈጣሪና በአዳም መካከል የጸብ ግድግዳ የፈረሰው መጀመሪያ በቃሉ ነበር፤ “ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” በሚል ቃል። የክርስቶስ መወለድ ቃሉ ወደ ተግባር መለወጡን፣ የእርቁን አይቀሬነት አሳይቷል። በዲያቢሎስ ገፋፊነት ሕግ የጣሰው፣ በደል የፈጸመው አዳም ሆኖ ሳለ ለእርቅ ልጁን አሳልፎ የሰጠው ግን ፈጣሪ ነው። አዳምን ለማዳን፣ ከሐጥያት ቀንበር ለማላቀቅ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በሥጋ በመወለዱ ክብሩ ጨመረ እንጂ አልቀነሰም።
በየዘመናቱ በሚነሱ የዲያቢሎስ ጭፍሮች አሳሳችነት በሀገራችን ግጭቶች ተፈጥረው ያውቃሉ። ግጭቱን ተከትሎ የሚወረወረው የበደል ሥለት አብረው የሚያኖሩ እሴቶቻችንን ሊበጥስ ታግሏል። ነገር ግን ጨርሶ አልቆረጣቸውም። ማህበራዊ እሴቶቻችን በይቅርታ እየታሹ፣ በእርቀ ሰላም ተጠግነው ወደ ቦታቸው ይመለሳሉ። እስከ አሁንም ሀገር አድርጎ ያቆየን ይሄ ሂደት ነው።
ጁንታው መከላከያ ሠራዊታችን ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የተፈጠረውን ግጭት ጨምሮ በሌሎች ምክንያቶች በሀገራችን የተፈጸሙ መበዳደሎችን ለመሻር በዚህ ሰዓት ሀገራዊ እርቀ ሰላም ያስፈልገናል። አንድነታችንን ለማስጠበቅ ስለሚያስችለን፣ በእርቀ ሰላሙ ኢትዮጵያ አትራፊ እንደምትሆን እሙን ነው። በሰውና በፈጣሪ እርቅ ምክንያት የከሠረው አሳሳቹ ዲያብሎስ እንደሆነው ሁሉ፣ በሀገራችን እርቀ ሰላም ምክንያት የሽብር ቡድኖቹ የሕወሃትና የሸኔ እኩይ ዓላማ፣ እንዲሁም የታሪካዊ ጠላቶቻችን ሕልም ይከሽፋል።
በድጋሚ መልካም የልደት በዓል ይሁንልን።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ታኅሣሥ 28 ቀን 2014 ዓ.ም.
8221 Georgia Avenue
Silver Spring, MD
20910
Be the first to know and let us send you an email when ጎልጉል Ethiopian Daily News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.
Send a message to ጎልጉል Ethiopian Daily News:
https://911ifix.com/ Book online & get $10 off on all your repair
NVCC - Loudoun Campus Bookstore
46432 Logan Way, SterlingDominion High School Holiday & Craft Fair
21326 Augusta Dr, SterlingBrittany's Fancy Events & Catering LLC
21453 Epicerie Plaza, Sterling