25/01/2014
ለጋዳፊ ሆስተስነት ምልመላ
"....እንዳይደርስ የለም ሰዓቱ ደረሰ፡፤ከምሽቱ ሶስት ሰአት ላይ 35 የምንሆን ቆነጃጅት ሸራተን ተገኘን። አብረውን ሶስት ሴት ጋዜጠኞች ነበሩ።ከኔ ጋር የነበሩት ተመልማዮች አብዛኞቹ ከገጽታቸው የኮሌጅና የዩኒቨርሲቲ ትምህርት የቀሰሙ ይመስላሉ።ሴቶቹ ከዚህ በላይ እንዳይበዙ በልቤ ተመኘሁ።ጥቂት በኔ ደረጃ ውብ የሆኑ ሴቶችንም ብ እርቀት ተመልክቻለሁ።ኩሪፍቱ ገስት ሀውስ ውስጥ ከነበርነው ሴቶች ውስጥ ክልሷ ልጅ ስትቀር ሁሉንም አየኋቸው።ሶስና በጥግ በኩል ተቀምጣለች።ሲበዛ ሜካፕ ተለቅልቃለች።የምር ቆንጆ ቆንጆ ልጆች ተመልምለው መጥተዋል።ይህንን ሁሉ ምልመላ ያካሄደው ኡስማን ብቻ ነው ብዬ ለማለት ከበደኝ።ብዙም ሳንቆይ አንዲት ሴት እየመራች ጋዳፊ ወዳረፉበት ቪላ ወሰደችን።ሴትየዋን የሆነ ቦታ አውቃታለሁ።ሆኖም ግን ማስታወስ አቃተኝ።በኋላ ላይ ሸራተን ሎቢ ውስጥ ጄነራሉን ስጠብቀው መጥታ ያናገረችኝ ሊቢያዊት እንደሆነች አስታወስኩ።ዛሬ የወታደር መለዮ ለብሳለች።ገዘፍ ያለች ሆና ጠየም ያለች አረብ ናት፤አብራት የሆነሽ ጠብደል ጥቁር ሴት አለች።ይቺ ደግሞ ያው ጋዳፊ እንደ ቻድ ካሉ የአፍሪካ ሃገራት አመቷት ድንግል አጃቢያቸው ትሆናለች ብዬ አሰብኩ።እንግሊዘኛዋ ሲበዛ ቀሽም የሚባል አይነት ነው፤በቅርብ ርቀት ጋዳፊ ካረፉበት ቪላ(Deluxe room/Luxury Villa) የሊቢያ ሰንደቅ አላማ (ባንዲራ) ተሰቅሎ ሳይ ባለሁለት ፎቁ ቪላው ውስጥ ጋዳፊ ያረፉበት መሆኑን ለማረጋገጥ ቻልኩ።"
"...... ቪላው በራፍ ግ ስንደርስ የተወሰኑት የጋዳፊ ደናግላን ሴት አጃቢዎቹ ተከፋፍለው ፈተሹን፤ሁሉም ከወታደራዊው ቆባቸው፣ሚሊተሪ የደንብ ልብሳቸው እና ጉልበታቸው ድረስ የሚደርስ ቡትስ ጫማቸው ጋር ያስፈራሉ።ድንግል መሆናቸውን ሳስብ ግን ሳቄ መጣ።ወደ ውስጥ ዘለቅን፤ሁለቱ ፕሮቶኮሎች ተከፋፍለው 17 የምንሆነውን ወደ አንድ ክፍል ወሰዱን።ወደ መኝታ ክፍል ነበር የሚወስዱን እጅግ ውብ ነው።የጋዳፊ መኝታ ሊሆን እንደሚችል ጠረጠርኩ፣ሁላችንም ደንግጠናል፣በውስጣችን ብዙ ጥያቄዎች ይርመሰመሳሉ፣አንዷ ልጅ በግልጽ በአማርኛ ቅሬታዋን ገለፀች።"
"......ጋዳፊ ወዳለንበት ድንኳን ዘለቁ።ነጭ ጀለቢያና ጥቁር ባለቆዳ ስሊፐር ተጫምተዋል።ጥቁር የበደዊን ጎሳ ይጭንቅላት ጥምጣማቸው እንዳለ ነው። በቴሌቪዢን ከማውቃቸው የበለጠ ገዝፈው ታዩኝ።መጠበቅ ሰልችቶን የተቀመጥን ሁላ ልክ እሳቸው ሲገቡ ተነሳን፤........."
"...ጋዳፊ ሰኞና ሐሙስ በግል ክፍላቸው ውስጥ የተገለጠችን ሴት አያናግሩም፤ሂጃብ ልበሺ!ማስቲካ የምታኝክ ሴት ይጸየፋሉ...ማስቲካ ከያዝሽ ካሁኑ ጣይው...እሳቸው ሳይፈቅዱ እጃቸውን ለመጨበጥ እንዳትሞክሪ.. ምናልባት ካስነጠሰሽ አፍሽን በመሐረብ ሸፍኚ፣ምግብ ከቀረብ እሳቸው ሳይጀምሩ እንዳትጀምሪ... ሺ ማስጠኝቀቂያዎችን ዘረዘረችልኝ።ፈራሁ።..."
ሮዛ ይድነቃቸው